ማበረታቻ
የአምላክ አገልጋዮች እርስ በርስ መበረታታታቸው አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
ኢሳ 35:3, 4፤ ቆላ 3:16፤ 1ተሰ 5:11፤ ዕብ 3:13
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
2ዜና 32:2-8—ንጉሥ ሕዝቅያስ ኃይለኛ ጠላት ሲመጣባቸው ሕዝቡን አበረታቷል
-
ዳን 10:2, 8-11, 18, 19—አረጋዊው ነቢይ ዳንኤል ኃይሉ በተሟጠጠበት ወቅት አንድ መልአክ አበረታቶታል እንዲሁም አጠናክሮታል
-
ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች ማበረታቻ ከመስጠት ጋር በተያያዘ ምን ግዴታ አለባቸው?
በተጨማሪም ማቴ 11:28-30ን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘዳ 3:28፤ 31:7, 8—ነቢዩ ሙሴ፣ ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ተተኪውን ኢያሱን አበረታቶታል እንዲሁም አደፋፍሮታል
-
ሥራ 11:22-26፤ 14:22—ሐዋርያቱ ጳውሎስና በርናባስ በስደት ወቅት የአንጾኪያ ክርስቲያኖችን አበረታተዋል
-
ማበረታቻ ለመስጠት ከልብ ማመስገን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
መሳ 11:37-40—የእስራኤል ሴቶች የመስፍኑን ዮፍታሔ ልጅ በየዓመቱ እየሄዱ ይጠይቋታል፤ ሕይወቷን ለይሖዋ አገልግሎት በመስጠቷ ያመሰግኗታል
-
ራእይ 2:1-4—ኢየሱስ የኤፌሶን ክርስቲያኖችን ማረም ቢያስፈልገውም መልካም ጎናቸውን ጠቅሶላቸዋል
-
ታማኝ የይሖዋ አገልጋዮች እርስ በርስ መበረታታት የሚችሉት እንዴት ነው?
ምሳሌ 15:23፤ ኤፌ 4:29፤ ፊልጵ 1:13, 14፤ ቆላ 4:6፤ 1ተሰ 5:14
በተጨማሪም 2ቆሮ 7:13, 15, 16ን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ሳሙ 23:16-18—ዮናታን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለውን ዳዊትን ፈልጎ አገኘው፤ እንዲሁም በዕድሜ የሚያንሰውን ወዳጁን አበረታታው
-
ዮሐ 16:33—ኢየሱስ ምሳሌ በመሆን ተከታዮቹን አበረታቷቸዋል፤ የእሱን ምሳሌ ከተከተሉ አሸናፊዎች እንደሚሆኑ አረጋግጦላቸዋል
-
ሥራ 28:14-16—ሐዋርያው ጳውሎስ ይግባኙ እንዲታይለት ወደ ሮም በተጓዘበት ወቅት እሱን ለማግኘትና ለማበረታታት ሩቅ መንገድ ተጉዘው የመጡ ታማኝ ወንድሞቹን ሲያይ ተበረታታ
-
አክብሮት የማጣት ወይም የማጉረምረም መንፈስ እንዳያድርብን መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘኁ 11:10-15—ነቢዩ ሙሴ፣ አሉታዊና ዓመፀኛ በሆነው ሕዝብ የተነሳ ተስፋ ቆርጧል
-
ዘኁ 13:31, 32፤ 14:2-6—አሥሩ ሰላዮች የነዙት መጥፎ ወሬ ሕዝቡን ተስፋ አስቆረጠ፤ ወደ ዓመፅም መራቸው
-
ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ጊዜ ማሳለፍ የሚያበረታታን ለምንድን ነው?
ምሳሌ 27:17፤ ሮም 1:11, 12፤ ዕብ 10:24, 25፤ 12:12
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
2ዜና 20:1-19—ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ታላቅ ሠራዊት ሲመጣበት አንድ ላይ ሆኖ ለመጸለይ ሕዝቡን ሰብስቧል
-
ሥራ 12:1-5, 12-17—ሐዋርያው ያዕቆብ በተገደለበትና ሐዋርያው ጴጥሮስ በታሰረበት ወቅት በኢየሩሳሌም ያለው ጉባኤ አንድ ላይ ተሰብስቦ ጸልዮአል
-
አዎንታዊ አመለካከት አስቸጋሪ ጊዜን በጽናት ለማለፍ ብርታት የሚሰጠን እንዴት ነው?
ሥራ 5:40, 41፤ ሮም 8:35-39፤ 1ቆሮ 4:11-13፤ 2ቆሮ 4:16-18፤ 1ጴጥ 1:6, 7
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፍ 39:19-23፤ 40:1-8—ዮሴፍ በሐሰት ተወንጅሎ በግፍ እስር ቤት ተጥሏል፤ ያም ሆኖ ታማኝነቱን ጠብቋል፤ ሌሎችን መርዳትም ያስደስተው ነበር
-
2ነገ 6:15-17—ነቢዩ ኤልያስ ታላቅ ሠራዊት ሲመጣበት አልፈራም፤ አገልጋዩም የእሱ ዓይነት አመለካከት እንዲኖረው ጸልዮአል
-
ከይሖዋ ቃል ማበረታቻ ማግኘት
ይሖዋ ምን ማረጋገጫ ሰጥቶናል?
በይሖዋ ትዕግሥትና ምሕረት ላይ ማሰላሰላችን የሚያበረታታን እንዴት ነው?
ይሖዋ ጉልበታቸው እንደተሟጠጠ ለሚሰማቸው ሰዎች ምን ሊያደርግላቸው ይችላል?
መዝ 46:1፤ ኢሳ 12:2፤ 40:29-31፤ ፊልጵ 4:13
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ሳሙ 1:10, 11, 17, 18—ይሖዋ በጭንቀትና በምሬት የተዋጠችው ሐና ወደ እሱ ስትጸልይ ሰምቷታል፤ ሥቃይዋ ቀለል እንዲልላትም አድርጓል
-
1ነገ 19:1-19—ነቢዩ ኤልያስ ተስፋ በቆረጠበት ወቅት ይሖዋ ተግባራዊ እርዳታ ሰጥቶታል። ስለ ወደፊቱ ጊዜ ተስፋ በመስጠት አበረታቶታል እንዲሁም አጽናንቶታል
-
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚሰጠው ተስፋ የሚያበረታታን እንዴት ነው?
2ዜና 15:7፤ መዝ 27:13, 14፤ ዕብ 6:17-19፤ 12:2
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ኢዮብ 14:1, 2, 7-9, 13-15—ኢዮብ ስሜቱ እጅግ በተደቆሰበት ወቅትም እንኳ በትንሣኤ ተስፋ ተጽናንቷል
-
ዳን 12:13—ነቢዩ ዳንኤል 100 ዓመት ገደማ ሳለ አንድ መልአክ ስለ ወደፊት ሽልማቱ በመንገር አበረታቶታል
-
ወደ ይሖዋ መጸለይና ስለ እሱ ማሰላሰል የሚያበረታታን ለምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ሳሙ 30:1-9—ንጉሥ ዳዊት ከባድ ችግር በገጠመው ወቅት ወደ ይሖዋ ዘወር በማለት ብርታት አግኝቷል
-
ሉቃስ 22:39-43—ኢየሱስ በምድራዊ ሕይወቱ እጅግ ተፈታታኝ በሆነ ወቅት ላይ አጥብቆ ጸልዮአል፤ ይሖዋም የሚያበረታታው መልአክ በመላክ መልስ ሰጥቶታል
-
ጥሩ ዜና መስማትና ለሌሎች ማጋራት የሚያበረታታን እንዴት ነው?