ማኅበራዊ ልዩነቶች
ዘራችን፣ ከትልቅ ቤተሰብ መወለዳችን ወይም የኢኮኖሚ ደረጃችን በአምላክ ዘንድ ላቅ ያለ ቦታ ያሰጠናል?
ሥራ 17:26, 27፤ ሮም 3:23-27፤ ገላ 2:6፤ 3:28
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዮሐ 8:31-40—አንዳንድ አይሁዳውያን አባታቸው አብርሃም እንደሆነ በመግለጽ ይኩራሩ ነበር፤ ኢየሱስ ግን ድርጊታቸው ከአብርሃም ፈጽሞ የተለየ እንደሆነ በመግለጽ አስተሳሰባቸው የተሳሳተ መሆኑን ነግሯቸዋል
-
ሰዎችን በዘራቸው ወይም በአገራቸው የተነሳ ዝቅ አድርገን የምንመለከትበት ምክንያት ይኖራል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዮናስ 4:1-11—ነቢዩ ዮናስ የሌላ አገር ሕዝቦች ለሆኑት የነነዌ ሰዎች ምሕረት እንዲያሳይ ይሖዋ በትዕግሥት አስተምሮታል
-
ሥራ 10:1-8, 24-29, 34, 35—ሐዋርያው ጴጥሮስ አሕዛብን ርኩስ አድርጎ መመልከት እንደሌለበት ተምሯል፤ በመሆኑም ቆርኔሌዎስንና ቤተሰቡን ክርስቲያኖች እንዲሆኑ ረድቷቸዋል፤ እነዚህ ሰዎች ካልተገረዙ አሕዛብ ወገን የሆኑ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው
-
ሀብታም የሆኑ ክርስቲያኖች ከሌሎች እንደሚበልጡ ሊያስቡ ወይም ከሌሎች የተለየ ነገር እንዲደረግላቸው ሊጠብቁ ይገባል?
በተጨማሪም ዘዳ 8:12-14፤ ኤር 9:23, 24ን ተመልከት
የበላይ ተመልካችነት ኃላፊነት አንድን ሰው ከሌሎች ያስበልጠዋል? ሌሎችን እንዳሻው ለማዘዝስ መብት ይሰጠዋል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘዳ 17:18-20—ይሖዋ፣ የእስራኤል ነገሥታት ራሳቸውን ከወገኖቻቸው ከፍ አድርገው መመልከት እንደሌለባቸው አስጠንቅቋል፤ ተገዢዎቻቸውን እንደ ወንድሞቻቸው አድርገው ማየት ይጠበቅባቸው ነበር
-
ማር 10:35-45—ሐዋርያቱ ሥልጣንና ክብር ከልክ በላይ ያሳስባቸው የነበረ በመሆኑ ኢየሱስ አርሟቸዋል። (በእንግሊዝኛው አዲስ ዓለም ትርጉም፣ ማር 10:42 ላይ “ሥልጣናቸውን እንደሚያሳዩ” ለሚለው ሐሳብ የተዘጋጀውን ለጥናት የሚረዳ መረጃ ተመልከት)
-
አንድን ሰው በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የሚያስገኝለት ነገር ምንድን ነው?
ክርስቲያኖች ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት በሚደረጉ ንቅናቄዎች መካፈል ይኖርባቸዋል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዮሐ 6:14, 15—ሕዝቡ ኢየሱስ ማኅበራዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠብቀው ሊሆን ይችላል፤ ኢየሱስ ግን እንዲያነግሡት አልፈለገም
-