በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሥራ

ሥራ

በሥራ እና በደስታ መካከል ምን ዝምድና አለ?

ጥራት ያለው ሥራ መሥራትና የተካነ ሠራተኛ መሆን ምን ጥቅሞች አሉት?

ምሳሌ 22:29

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 16:16-23—ወጣቱ ዳዊት የተካነ ሙዚቀኛ ነው የሚል ስም አትርፎ ነበር፤ ይህ ተሰጥኦው ለተረበሸው የእስራኤል ንጉሥ ጠቃሚ አገልግሎት ለመስጠት አስችሎታል

    • 2ዜና 2:13, 14—ኪራምአቢ የተካነ የእጅ ጥበብ ባለሙያ ነበር፤ በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን ባከናወነው ታላቅ የግንባታ ሥራ ጠቃሚ አገልግሎት መስጠት ችሏል

የይሖዋ አገልጋዮች በምን ዓይነት የሥራ ባሕል መታወቅ ይፈልጋሉ?

ኤፌ 4:28፤ ቆላ 3:23

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 24:10-21—ርብቃ የአብርሃም አገልጋይ ከጠየቃት ነገር በላይ አድርጋለች፤ ሌሎችን መርዳት እንደምትፈልግና ታታሪ እንደሆነች አሳይታለች

    • ፊልጵ 2:19-23—ወጣቱ ጢሞቴዎስ በትጋት ለመሥራትና ሌሎችን በትሕትና ለማገልገል ፈቃደኛ ነበር፤ በመሆኑም ሐዋርያው ጳውሎስ ከባድ ኃላፊነት በአደራ ሰጥቶታል

የአምላክ አገልጋዮች ስንፍናን ለማስወገድ የሚጥሩት ለምንድን ነው?

ምሳሌ 13:4፤ 18:9፤ 21:25, 26 መክ 10:18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 6:6-11—ንጉሥ ሰለሞን ጉንዳንን እንደ ምሳሌ አድርጎ በመጠቀም ተግቶ ስለ መሥራትና ስንፍናን ስለ ማስወገድ ትምህርት ሰጥቷል

ራሳችንን ለማስተዳደር ተግተን መሥራት ያለብን ለምንድን ነው?

በእኛ ሥር ያሉ የቤተሰባችንን አባላት ለማስተዳደር ተግተን መሥራት ያለብን ለምንድን ነው?

1ጢሞ 5:8

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሩት 1:16, 17፤ 2:2, 3, 6, 7, 17, 18—ወጣቷ መበለት ሩት፣ አማቷን ናኦሚን ለመንከባከብ በትጋት ሠርታለች

    • ማቴ 15:4-9—ኢየሱስ፣ ወላጆቻቸውን የመጦር ኃላፊነታቸውን ላለመወጣት መንፈሳዊ ነገሮችን ሰበብ የሚያደርጉ ሰዎችን አውግዟል

ክርስቲያኖች ተግተው በመሥራት ያገኙትን ነገር ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

ከሥራችን ለምናገኘው ገቢ ምን ሚዛናዊ አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

ይሖዋ ሥራችንን ጥሩ አድርገን ለማከናወንና በቁሳዊ የሚያስፈልገንን ነገር ለማግኘት እንደሚረዳን እንዴት እናውቃለን?

ማቴ 6:25, 30-32፤ ሉቃስ 11:2, 3 2ቆሮ 9:10

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 31:3-13—ላባ አማቹን ያዕቆብን ቀጥሮ ሲያሠራው አግባብ ያልሆነ ነገር አድርጎበታል፤ ይሖዋን ግን የያዕቆብን ልፋት አይቶ ባርኮታል

    • ዘፍ 39:1-6, 20-23—ዮሴፍ በጶጢፋር ቤት ውስጥ ባሪያ በነበረበት ወቅትም ይሁን ታስሮ ሳለ በትጋት ያከናወነውን ሥራ ይሖዋ ባርኮለታል

ሰብዓዊ ሥራችንን ለአምላክ ከምናቀርበው አገልግሎት ማስቀደም የሌለብን ለምንድን ነው?

መዝ 39:5-7፤ ማቴ 6:33፤ ዮሐ 6:27

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 12:15-21—ኢየሱስ ቁሳዊ ነገሮችን ከመንፈሳዊ ሀብት ማስቀደም ሞኝነት እንደሆነ በምሳሌ አስተምሯል

    • 1ጢሞ 6:17-19—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ሀብታም የሆኑ ክርስቲያኖች እንዳይታበዩ ከዚህ ይልቅ “በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ” አሳስቧል

ሥራ ስንመርጥ በየትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ልንመራ ይገባል?

ለይሖዋ መሥራት

ክርስቲያኖች የሚሳተፉበት ከሁሉ ይበልጥ አስፈላጊው ሥራ ምንድን ነው?

በይሖዋ አገልግሎት ምርጣችንን ለመስጠት የምንፈልገው ለምንድን ነው?

ሁሉም ሰው በይሖዋ አገልግሎት ተመሳሳይ መጠን ያለው ሥራ እንደሚሠራ መጠበቅ የሌለብን ለምንድን ነው?

ገላ 6:3-5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 25:14, 15—ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ እንደሚያሳየው ሁሉም ተከታዮቹ ተመሳሳይ መጠን ያለው ሥራ እንዲያከናውኑ አይጠብቅም

    • ሉቃስ 21:2-4—ኢየሱስ፣ አንዲት ድሃ መበለት ያደረገችው አነስተኛ መዋጮ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ተናግሯል

በይሖዋ አገልግሎት የተሰጠንን ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ብርታት ከየት ማግኘት እንችላለን?

2ቆሮ 4:7፤ ኤፌ 3:20, 21፤ ፊልጵ 4:13

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ጢሞ 4:17—ሐዋርያው ጳውሎስ ኃይል ባስፈለገው ሰዓት የሚያስፈልገውን ኃይል እንዳገኘ ተናግሯል

በይሖዋ አገልግሎት በትጋት መሥራት ደስታ የሚያስገኘው ለምንድን ነው?

መዝ 40:8፤ ዮሐ 13:17፤ ያዕ 1:25

በተጨማሪም ማቴ 25:23⁠ን ተመልከት