በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ራስን መወሰን

ራስን መወሰን

ራሳችንን ለይሖዋ አምላክ ለመወሰን ሊያነሳሳን የሚገባው ትክክለኛው የልብ ዝንባሌ ምንድን ነው?

ዘዳ 6:5፤ ሉቃስ 10:25-28፤ ራእይ 4:11

በተጨማሪም ዘፀ 20:5⁠ን ተመልከት

አምላክን ማገልገል የምንፈልግ ከሆነ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

አምላክ እኛን ከኃጢአት ነፃ ስለሚያወጣበት መንገድ ምን አምነን መቀበል ይኖርብናል?

በቀድሞ ሕይወታችን ለፈጸምናቸው መጥፎ ነገሮች ንስሐ መግባት ምን ማድረግ ይጠይቃል?

ሥራ 3:19፤ 26:20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 19:1-10—የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ የሆነው ዘኬዎስ ቀደም ሲል ይፈጽም ከነበረው የማጭበርበር ድርጊት ንስሐ ገብቷል፤ ቀምቶ ለወሰደውም ካሳ ከፍሏል

    • 1ጢሞ 1:12-16—ሐዋርያው ጳውሎስ የቀድሞ መጥፎ አኗኗሩን ሙሉ በሙሉ እንደተወ እንዲሁም በአምላክና በክርስቶስ ምሕረት ይቅርታ እንዳገኘ ተናግሯል

መጥፎ ነገር ማድረጋችንን ከመተው በተጨማሪ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል?

አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ለማምለክ የትኞቹን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች መታዘዝ ይኖርብናል?

1ቆሮ 6:9-11፤ ቆላ 3:5-9 1ጴጥ 1:14, 15፤ 4:3, 4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ቆሮ 5:1-13—ሐዋርያው ጳውሎስ በጉባኤው ውስጥ ዓይን ያወጣ ብልግና የፈጸመን አንድ ሰው ከመካከላቸው እንዲያስወጡት ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መመሪያ ሰጥቷል

    • 2ጢሞ 2:16-19—ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተመረዘ ቁስል ከሚሰራጨው የከሃዲዎች ንግግር እንዲርቅ ጢሞቴዎስን አሳስቦታል

የአምላክ አገልጋዮች ከዚህ ዓለም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምን አቋም ሊኖራቸው ይገባል?

ኢሳ 2:3, 4፤ ዮሐ 15:19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዮሐ 6:10-15—ኢየሱስ በተአምር ብዙ ሕዝብ ከመገበ በኋላ ሕዝቡ ሊያነግሡት ፈለጉ፤ ኢየሱስ ግን ትቷቸው ሄደ

    • ዮሐ 18:33-36—ኢየሱስ መንግሥቱ ከዚህ ዓለም ፖለቲካዊ ጉዳዮች ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ተናግሯል

መንፈስ ቅዱስ አምላክን ለማገልገል የሚረዳን እንዴት ነው?

ዮሐ 16:13፤ ገላ 5:22, 23

በተጨማሪም ሥራ 20:28፤ ኤፌ 5:18⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 15:28, 29—በኢየሩሳሌም ያለው የበላይ አካል ከግርዘት ጋር የተያያዘ ትልቅ ውሳኔ ባደረገበት ወቅት የመንፈስ ቅዱስን አመራር አግኝቷል

ራሳችንን ወስነን ለአምላክ በምናቀርበው አገልግሎት ኢየሱስን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?

ራሳቸውን የወሰኑ ክርስቲያኖች መጠመቅ ያለባቸው ለምንድን ነው?

ማቴ 28:19, 20፤ ሥራ 2:40, 41፤ 8:12፤ 1ጴጥ 3:21

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 3:13-17—ኢየሱስ የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ ራሱን አቅርቧል፤ ይህንንም በጥምቀት አሳይቷል

    • ሥራ 8:26-39—ወደ ይሁዲነት የተለወጠ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውነቱን ሲማር ለመጠመቅ ወሰነ