ስደት
ክርስቲያኖች ስደት እንደሚደርስባቸው መጠበቅ ያለባቸው ለምንድን ነው?
ስደት ሲደርስብን ይሖዋ እንዲደግፈን መለመን ያለብን ለምንድን ነው?
መዝ 55:22፤ 2ቆሮ 12:9, 10፤ 2ጢሞ 4:16-18፤ ዕብ 13:6
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ነገ 19:1-18—ነቢዩ ኤልያስ ስደት ሲደርስበት ልቡን ለይሖዋ አፍስሷል፤ በውጤቱም ማበረታቻና ማጽናኛ አግኝቷል
-
ሥራ 7:9-15—ዮሴፍ በወንድሞቹ ስደት ደርሶበታል፤ ይሖዋ ግን በታማኝነት አብሮት ሆኗል፤ ታድጎታል እንዲሁም ቤተሰቡን ለማዳን ተጠቅሞበታል
-
ስደት በየትኛው መልክ ሊመጣ ይችላል?
ፌዝ፣ ስድብ
2ዜና 36:16፤ ማቴ 5:11፤ ሥራ 19:9፤ 1ጴጥ 4:4
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
2ነገ 18:17-35—የአሦር ንጉሥ መልእክተኛ የሆነው ራብሻቁ ይሖዋን ሰድቧል፤ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይም ተሳልቋል
-
ሉቃስ 22:63-65፤ 23:35-37—ኢየሱስ አልፎ በተሰጠበትና እንጨት ላይ በተሰቀለበት ወቅት አሳዳጆቹ ሰድበውታል እንዲሁም አፊዘውበታል
-
የቤተሰብ ተቃውሞ
እስራትና በባለሥልጣናት ፊት መቅረብ
አካላዊ ጥቃት
የሕዝብ ዓመፅ
ግድያ
ክርስቲያኖች ስደት ሲደርስባቸው ምን ዓይነት ምግባር ሊያሳዩ ይገባል?
ማቴ 5:44፤ ሥራ 16:25፤ 1ቆሮ 4:12, 13፤ 1ጴጥ 2:23
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 7:57–8:1—ደቀ መዝሙሩ እስጢፋኖስ፣ ሆ ብለው በወጡ ተቃዋሚዎች እጅ ሊገደል ሲል አምላክ ለአሳዳጆቹ ምሕረት እንዲያሳያቸው ለምኗል፤ ከአሳዳጆቹ አንዱ የጠርሴሱ ሳኦል ነው
-
ሥራ 16:22-34—ሐዋርያው ጳውሎስ ተደብድቧል እንዲሁም በእግር ግንድ ታስሯል፤ ሆኖም ለእስር ቤት ጠባቂው ደግነት አሳይቶታል፤ በውጤቱም ይህ ሰውና መላ ቤተሰቡ አማኞች ሆነዋል
-
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች ምን ገጥሟቸዋል?
ለስደት ሊኖረን የሚገባው ትክክለኛው አመለካከት ምንድን ነው?
ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተሰጠን ተስፋ በስደት ወቅት የሚያጠናክረን እንዴት ነው?
ስደት እንዲያሸማቅቀን፣ በፍርሃት እንዲያርደን ወይም ተስፋ እንዲያስቆርጠን የማንፈቅደው ለምንድን ነው? ይሖዋን ማገልገላችንን እንዲያስቆመን የማንፈቅደውስ ለምንድን ነው?
መዝ 56:1-4፤ ሥራ 4:18-20፤ 2ጢሞ 1:8, 12
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
2ዜና 32:1-22—ንጉሥ ሰናክሬም ታላቅ ሠራዊት ይዞ በመጣበት ወቅት ንጉሥ ሕዝቅያስ በይሖዋ ታምኗል፤ ሕዝቡን አበርትቷል፤ ይሖዋም አብዝቶ ባርኮታል
-
ዕብ 12:1-3—አሳዳጆች ኢየሱስን ሊያሸማቅቁት ሞክረዋል፤ እሱ ግን ውርደትን ንቋል፤ ተስፋ እንዲያስቆርጠው ፈጽሞ አልፈቀደም
-
ስደት ምን መልካም ውጤት ሊያመጣ ይችላል?
በፈተና መጽናታችን ይሖዋን ያስደስተዋል፤ ለስሙም ክብር ያመጣል
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ኢዮብ 1:6-22፤ 2:1-10—ኢዮብ ከደረሱበት አስከፊ መከራዎች በስተ ጀርባ ያለው ሰይጣን መሆኑን ባያውቅም ለይሖዋ ጀርባውን አልሰጠም፤ በዚህ መንገድ ሰይጣን ውሸታም መሆኑን በማረጋገጥ ይሖዋን አስከብሯል
-
ዳን 1:6, 7፤ 3:8-30—ታማኞቹ ሃናንያህ፣ ሚሳኤልና አዛርያስ (ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ) የይሖዋን ትእዛዝ ከመጣስ ይልቅ በአሰቃቂ ሁኔታ መሞትን መርጠዋል፤ በውጤቱም አረማዊው ንጉሥ ናቡከደነጾር ይሖዋን በይፋ አክብሯል
-
ስደት ተጨማሪ ምሥክርነት እንዲሰጥ መንገድ ሊከፍት ይችላል
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 11:19-21—በስደት ምክንያት ወደተለያዩ ቦታዎች የተበታተኑት ክርስቲያኖች በሄዱበት ሁሉ ምሥራቹን ማሰራጨታቸውን ቀጥለዋል
-
ፊልጵ 1:12, 13—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የእሱ መታሰር ምሥራቹ ይበልጥ እንዲስፋፋ ምክንያት እንደሆነ ማወቁ አስደስቶታል
-
ስደት ሲደርስብን መጽናታችን የእምነት ባልንጀሮቻችንን ሊያበረታቸው ይችላል
የሃይማኖት መሪዎችና ፖለቲከኞች በአምላክ ሕዝቦች ላይ በሚሰነዘረው ስደት እጃቸውን የሚያስገቡት እንዴት ነው?
ኤር 26:11፤ ማር 3:6፤ ዮሐ 11:47, 48, 53፤ ሥራ 25:1-3
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 19:24-29—ኤፌሶን ውስጥ የአርጤምስን ቤተ መቅደስ ምስል የሚሠሩ ሰዎች በክርስቲያኖች ላይ ስደት አድርሰዋል፤ ምክንያቱም ጣዖት አምልኮን የሚያወግዘው የክርስቲያኖች መልእክት ትርፋማ የሆነውን ንግዳቸውን እንደሚነካባቸው ተሰምቷቸዋል
-
ገላ 1:13, 14—ጳውሎስ (ሳኦል) ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት ለአይሁድ እምነት ከፍተኛ ቅንዓት ነበረው፤ በዚህም የተነሳ በጉባኤው ላይ ስደት አድርሷል
-
በይሖዋ አገልጋዮች ላይ ከሚደርሰው ስደት በስተ ጀርባ ያለው ማን ነው?