በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተግሣጽ

ተግሣጽ

መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ የላቀ የተግሣጽ ምንጭ የሆነው ለምንድን ነው?

ሁላችንም መመሪያና እርማት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

ምሳሌ 16:2, 25፤ ኤር 10:23

በተጨማሪም ኤር 17:9⁠ን ተመልከት

የይሖዋ ተግሣጽ ለምን ነገር ማስረጃ ነው?

ምሳሌ 3:11, 12፤ ዕብ 12:7-9

በተጨማሪም ዘዳ 8:5፤ ምሳሌ 13:24ራእይ 3:19⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ሳሙ 12:9-13፤ 1ነገ 15:5፤ ሥራ 13:22—ንጉሥ ዳዊት በጣም ከባድ ኃጢአቶች ቢሠራም ይሖዋ በፍቅር ተግሣጽ ሰጥቶታል እንዲሁም ይቅር ብሎታል

    • ዮናስ 1:1-4, 15-17፤ 3:1-3—ነቢዩ ዮናስ የተሰጠውን ኃላፊነት ላለመወጣት ሸሽቶ በመሄዱ ይሖዋ ገሥጾታል፤ ሆኖም ሁለተኛ ዕድል ሰጥቶታል

የአምላክን ተግሣጽ አቅልለን አለመመልከታችን ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 9:8፤ 12:1፤ 17:10፤ ዕብ 12:5, 6

በተጨማሪም 2ዜና 36:15, 16⁠ን ተመልከት

የአምላክን ተግሣጽ የማይቀበሉ ሰዎች ምን ይገጥማቸዋል?

ምሳሌ 1:24-26፤ 13:18፤ 15:32፤ 29:1

በተጨማሪም ኤር 7:27, 28, 32-34⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኤር 5:3-7—የአምላክ ሕዝቦች ልባቸውን አደነደኑ፤ ተግሣጽ ሲሰጣቸውም ሰምተው ለመለወጥ ፈቃደኛ አልሆኑም፤ በመሆኑም ይሖዋ ይበልጥ ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሰጣቸው

    • ሶፎ 3:1-8—የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለጥፋት ተዳርገዋል

የይሖዋን ተግሣጽ መስማት ምን ጥቅም ያስገኛል?

ምሳሌ 4:13፤ 1ቆሮ 11:32፤ ቲቶ 1:13 ዕብ 12:10, 11

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 30:1-6—ነቢዩ ሙሴ፣ ይሖዋ ለሕዝቡ የሚሰጠውን ተግሣጽ የሚሰሙ ሁሉ ምን በረከት እንደሚያገኙ ትንቢት ተናግሯል

    • 2ዜና 7:13, 14—ይሖዋ፣ መለኮታዊ ተግሣጽ መቀበል ምን ጥሩ ውጤቶች እንዳሉት ለንጉሥ ሰለሞን ነግሮታል

ለሌሎች ከተሰጠ ተግሣጽ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

ሌሎች ከበድ ያለ ተግሣጽ ሲሰጣቸው መደሰት የሌለብን ለምንድን ነው?

አምላክ ከሚሰጠው ተግሣጽና ምክር ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

ኢያሱ 1:8፤ ያዕ 1:25

በተጨማሪም ዘዳ 17:18, 19፤ መዝ 119:97⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ዜና 22:11-13—ንጉሥ ዳዊት፣ ልጁ ሰለሞን የአምላክን መመሪያዎች በጥንቃቄ እስከተከተለ ድረስ በረከት እንደሚያገኝ አስረግጦ ነግሮታል

    • መዝ 1:1-6—ይሖዋ ቃሉን የሚያነብቡና የሚያሰላስሉበት ሰዎች እንደሚባረኩ ቃል ገብቷል

አፍቃሪ ወላጆች ልጆቻቸውን የሚገሥጹት ለምንድን ነው?

ወላጆች” የሚለውን ተመልከት

ልጆች ወላጆቻቸው ተግሣጽ ሲሰጧቸው ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?

ቤተሰብ—ወንዶች እና ሴቶች ልጆች” የሚለውን ተመልከት