በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትዳር

ትዳር

ጋብቻ የጀመረው እንዴት ነው?

አንድ ክርስቲያን የትዳር አጋሩ አድርጎ ሊመርጥ የሚገባው ማንን ነው?

ክርስቲያን ወላጆች፣ የተጠመቀ ወንድ ወይም ሴት ልጃቸው ራሱን ለይሖዋ ወስኖ ካልተጠመቀ ሰው ጋር ትዳር መመሥረቱን የማይደግፉት ለምንድን ነው?

1ቆሮ 7:39፤ 2ቆሮ 6:14, 15

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 24:1-4, 7—አረጋዊው አብርሃም፣ ሌሎች አማልክትን ከሚያመልኩት ከነአናውያን ሴቶች መካከል ለልጁ ለይስሐቅ ሚስት ሊድርለት አልፈለገም፤ ይሖዋን የምታገለግል ሚስት ለልጁ ለማምጣት የሚችለውን ሁሉ አድርጓል

    • ዘፍ 28:1-4—ይስሐቅ፣ ከከነአናውያን ሴቶች መካከል እንዳያገባ ከዚህ ይልቅ ይሖዋን የምታገለግል ሚስት እንዲፈልግ ልጁን ያዕቆብን አዞታል

ይሖዋ የማያምን ሰው ስለሚያገቡ አገልጋዮቹ ምን ይሰማዋል?

ዘዳ 7:3, 4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 11:1-6, 9-11—ንጉሥ ሰለሞን መለኮታዊ ማስጠንቀቂያዎችን ችላ ማለቱ፣ የባዕድ አገር ሴቶችን ማግባቱ እንዲሁም በእነሱ ተጽዕኖ ተሸንፎ ልቡ ከይሖዋ አምልኮ እንዲሸፍት መፍቀዱ ይሖዋን አስቆጥቶታል

    • ነህ 13:23-27—አገረ ገዢው ነህምያ፣ ይሖዋን የማያመልኩ የባዕድ አገር ሴቶችን በማግባታቸው ሕዝቡን ወቅሷቸዋል፤ የነህምያ ቁጣ የይሖዋን የጽድቅ ቁጣ የሚያንጸባርቅ ነው

የትዳር አጋር ስንመርጥ ይሖዋን በታማኝነት የሚያገለግልና ጥሩ ስም ያተረፈ ሰው መፈለጋችን ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?

ምሳሌ 18:22፤ 31:10, 28

በተጨማሪም ኤፌ 5:28-31, 33⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 25:2, 3, 14-17—ናባል ባለጸጋ ቢሆንም ኃይለኛና ምግባረ ብልሹ ሰው ነው፤ ለአቢጋኤል ጥሩ ባል የሚባል ዓይነት ሰው አልነበረም

    • ምሳሌ 21:9—መጥፎ የትዳር ጓደኛ ምርጫ ደስታ ያሳጣል እንዲሁም ሰላም ይነሳል

    • ሮም 7:2—አንዲት ሴት ስታገባ ባሏ በተወሰነ መጠንም ቢሆን በእሷ ላይ ሥልጣን እንደሚኖረው ሐዋርያው ጳውሎስ ተናግሯል፤ በመሆኑም ጥበበኛ ሴት ባሏ የሚሆነውን ሰውን በጥንቃቄ ትመርጣለች

ለትዳር መዘጋጀት

አንድ ወንድ ስለ ትዳር ማሰብ ከመጀመሩ በፊት ቤተሰብ ለማስተዳደር ዝግጁ መሆን ያለበት ለምንድን ነው?

1ጢሞ 5:8

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 24:27—አንድ ወንድ ከማግባቱ ምናልባትም ልጅ ከመውለዱ በፊት ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበት ነገር ለማግኘት ተግቶ መሥራት አለበት

ለጋብቻ የሚጠናኑ ጥንዶች ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር ከሌሎች መጠየቅ ያለባቸው ለምንድን ነው? በመልክ ከመደለል ይልቅ እርስ በርስ በደንብ ለመተዋወቅ ጥረት ማድረግ ያለባቸውስ ለምንድን ነው?

ምሳሌ 13:10፤ 1ጴጥ 3:3-6

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሩት 2:4-7, 10-12—ቦዔዝ የሩትን የሥራ ባሕል በማስተዋል፣ ሌሎች ስለ እሷ የሰጡትን እምነት የሚጣልበት ምሥክርነት በመስማት እንዲሁም ከቤተሰቧ ጋር ያላትን ግንኙነትና መንፈሳዊነቷን በመመልከት ስለ ሩት አውቋል

    • ሩት 2:8, 9, 20—ሩት የቦዔዝን ደግነት፣ ልግስና እንዲሁም ለይሖዋ ያለውን ፍቅር በመመልከት ስለ እሱ አውቃለች

ይሖዋ፣ ጋብቻ የሚያስቡ ጥንዶች በሚጠናኑበት ወቅትም ሆነ ከተጫጩ በኋላ በሥነ ምግባር ንጹሕ እንዲሆኑ የሚጠብቅባቸው ለምንድን ነው?

ገላ 5:19፤ ቆላ 3:5፤ 1ተሰ 4:4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 5:18, 19—አንዳንድ የፍቅር መግለጫዎች የተፈቀዱት በትዳር ውስጥ ብቻ ነው

    • መኃ 1:2፤ 2:6—ሱላማዊቷ ወጣትና እረኛው በሚጠናኑበት ወቅት ተገቢ የሆኑ የፍቅር መግለጫዎችን ተለዋውጠዋል፤ እነዚህ የፍቅር መግለጫዎች ንጹሕ ያልሆነ የፍትወት ስሜት የሚንጸባረቅባቸው አልነበሩም

    • መኃ 4:12፤ 8:8-10—ሱላማዊቷ ወጣት ንጽሕናዋን ጠብቃለች እንዲሁም ራሷን እንደምትገዛ አሳይታለች፤ እንደተቆለፈ የአትክልት ቦታ ነበረች

ጋብቻ የሚያስቡ ጥንዶች መንግሥት በሚያዘው መሠረት ሕጋዊ ጋብቻ መፈጸም ያለባቸው ለምንድን ነው?

የባል ድርሻ

ባል ምን ከባድ ኃላፊነት ተጥሎበታል?

ክርስቲያን ባል የራስነት ሥልጣኑን ሲጠቀም የማንን ምሳሌ መከተል አለበት?

ባል የሚስቱን ሁኔታ ለማስተዋል መሞከሩና እሷን በፍቅር መያዙ ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ቆላ 3:19፤ 1ጴጥ 3:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 21:8-12—አብርሃም የሚስቱ የሣራ ሐሳብ ቅር ቢያሰኘውም እንኳ እንዲሰማት ይሖዋ ነግሮታል

    • ምሳሌ 31:10, 11, 16, 28—በእነዚህ ጥቅሶች ላይ እንደተገለጸው ባለሙያ ሚስት ያለችው ጥበበኛ ባል የሚስቱን እንቅስቃሴ አይቆጣጠርም፤ እንከንም አይፈላልግባትም፤ ከዚህ ይልቅ ሚስቱን ያምናታል እንዲሁም ያወድሳታል

    • ኤፌ 5:33—ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት የጻፈው ሐሳብ ሚስት ባሏ እንደሚወዳት ማወቅ እንደምትፈልግ ይጠቁማል

የሚስት ድርሻ

ይሖዋ ለክርስቲያን ሚስት ምን አስፈላጊ ድርሻ ሰጥቷታል?

ሚስት የተሰጣት ድርሻ ዋጋዋን ዝቅ የሚያደርግ ነው?

ዘፍ 1:26-28, 31፤ 2:18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 1:8፤ 1ቆሮ 7:4—በትዳርና በቤተሰብ ውስጥ አምላክ ለሚስትና ለእናት የተወሰነ ሥልጣን ሰጥቷታል

    • 1ቆሮ 11:3—በይሖዋ ዝግጅት ውስጥ፣ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ በስተቀር በራስነት ሥልጣን ሥር ያልሆነ ማንም እንደሌለ ሐዋርያው ጳውሎስ አስረድቷል

    • ዕብ 13:7, 17—በጉባኤ ውስጥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች፣ አመራር እንዲሰጡ ለተሾሙት ወንድሞች መገዛትና መታዘዝ ይጠበቅባቸዋል

የማያምን ባል ያላት ክርስቲያን ሴት ይሖዋን ማስደሰት የምትችለው እንዴት ነው?

ክርስቲያን ሚስት ባሏን ማክበር ያለባት ለምንድን ነው?

ኤፌ 5:33

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 18:12፤ 1ጴጥ 3:5, 6—ሣራ ለባሏ ጥልቅ አክብሮት አሳይታለች፤ በልቧም እንኳ ሳይቀር ‘ጌታዋ’ ማለትም መንፈሳዊ ራሷ አድርጋ ተመልክታዋለች

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ዓይነት ሚስት ተመስግናለች?

ምሳሌ 19:14፤ 31:10, 13-31

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 24:62-67—ርብቃ ባሏ ይስሐቅ ከእናቱ ሞት እንዲጽናና ረድታዋለች

    • 1ሳሙ 25:14-24, 32-38—አቢጋኤል ዳዊትን በትሕትና በመለመን፣ ጅል የሆነውን ባሏንና የቤተሰቧን አባላት አትርፋቸዋለች

    • አስ 4:6-17፤ 5:1-8፤ 7:1-6፤ 8:3-6—ንግሥት አስቴር፣ የአምላክን ሕዝብ ለማትረፍ ስትል ሕይወቷን አደጋ ላይ ጥላለች፤ ንጉሡ የሆነውን ባሏን ለመለመን ስትል ሳትጠራ ሁለት ጊዜ ፊቱ ቀርባለች

አለመግባባቶችን መፍታት

ባለትዳሮች በትዳራቸው ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት የትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዷቸው ይችላሉ?

ባለትዳሮች ለገንዘብ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖራቸው የትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዷቸው ይችላሉ?

ሉቃስ 12:15፤ ፊልጵ 4:5፤ 1ጢሞ 6:9, 10፤ ዕብ 13:5

በተጨማሪም “ገንዘብ” የሚለውን ተመልከት

ባለትዳሮች ከዘመዶች ወይም ከአማቶች ጋር የተፈጠረን ችግር ለመፍታት የትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች ሊረዷቸው ይችላሉ?

ባለትዳሮች ከፆታ ግንኙነት ጋር በተያያዘ በየትኞቹ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመራት ይችላሉ?

በትዳር ጓደኛችን ድክመት ላይ ሳይሆን መልካም ባሕርያቱ ላይ ማተኮራችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ችግሮች ሲፈጠሩ ቂም ይዘን ከመቀመጥ ይልቅ በፍቅርና በአፋጣኝ መፍትሔ መፈለጋችን የሚሻለው ለምንድን ነው?

በቁጣ መገንፈል፣ ጩኸት፣ ስድብና ማንኛውም ዓይነት አካላዊ ጥቃት ለክርስቲያኖች ፈጽሞ የማይገባው ለምንድን ነው?

አለመግባባት ሲፈጠር ባልም ሆነ ሚስት ግባቸው ምን ሊሆን ይገባል?

ይሖዋን መሠረት ያደረገ ትዳር ምን በረከቶች ያስገኛል?

አምላክ ለትዳር ያወጣቸው መሥፈርቶች

ከፆታ ግንኙነትና ከትዳር ጋር በተያያዘ ይሖዋ ምን መሥፈርቶች አውጥቷል?

ክርስቲያኖች ከአንድ በላይ ስለ ማግባት ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?

ትዳር የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ጥምረት ሊሆን እንደሚገባ እንዴት እናውቃለን?

ባለትዳሮች መለያየት የሌለባቸው ለምንድን ነው?

በክርስቲያኖች ዘንድ ለፍቺ መሠረት ሊሆን የሚችለው ብቸኛው ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያት ምንድን ነው?

ይሖዋ ያለበቂ ምክንያት ስለመፋታት ምን ይሰማዋል?

የትዳር ጓደኛው የሞተበት ሰው እንደገና ማግባት ይችላል?