በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አለመግባባቶችን መፍታት

አለመግባባቶችን መፍታት

አንድ ሰው ቅር ሲያሰኘን በቁጣ እንዳንገነፍል ወይም የበቀል ስሜት እንዳያድርብን መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ምሳሌ 20:22፤ 24:29፤ ሮም 12:17, 18 ያዕ 1:19, 20፤ 1ጴጥ 3:8, 9

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 25:9-13, 23-35—ናባል፣ ዳዊትንና ሰዎቹን ሰደባቸው፤ ስንቅ ሊልክላቸውም ፈቃደኛ አልሆነም፤ በዚህ ጊዜ ዳዊት በመበሳጨቱ እሱንና የቤቱን ወንዶች ለመግደል ተነሳ፤ አቢጋኤል የሰጠችውን ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር መስማቱ ግን ከደም ዕዳ ጠብቆታል

    • ምሳሌ 24:17-20—ንጉሥ ሰለሞን በመንፈስ መሪነት በጻፈው ሐሳብ ላይ የአምላክ ሕዝቦች ጠላታቸው ውድቀት ሲደርስበት ቢደሰቱ ይሖዋ እንደሚያዝን ገልጿል፤ ፍርዱን ለይሖዋ መተዉ የተሻለ ነው

አንድ ክርስቲያን ከሰው ጋር ሲጋጭ ግለሰቡን ቢያኮርፈው ወይም ቂም ቢይዝበት ተገቢ ይሆናል?

ዘሌ 19:17, 18፤ 1ቆሮ 13:4, 5፤ ኤፌ 4:26

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 5:23, 24—አንድ ወንድማችን በእኛ ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር እንዳለ ብናውቅ ሰላም ለመፍጠር የቻልነውን ሁሉ ማድረግ እንዳለብን ኢየሱስ ተናግሯል

ቅር የሚያሰኝ ነገር ሲደረግብን ከሁሉ የተሻለው የፍቅር እርምጃ ምንድን ነው?

አንድ ሰው ደጋግሞ ቢበድለን እንኳ ከልቡ ከተጸጸተ ይቅር ልንለው የሚገባው ለምንድን ነው?

እንደ ስም ማጥፋት ወይም ማጭበርበር ያለ ከባድ በደል ከደረሰብንና ጉዳዩን ትተን ማለፍ ከከበደን የበደለንን ሰው ማነጋገር ያለበት ማን ነው? ይህ የሚደረግበትስ ዓላማ ምንድን ነው?

ማቴ 18:15

በተጨማሪም ያዕ 5:20⁠ን ተመልከት

ስማችንን ያጠፋው ወይም ያጭበረበረን ሰው በግል ስናነጋግረው ምንም ዓይነት የጸጸት ስሜት ከሌለው ምን ማድረግ ይኖርብናል?