በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ ክርስቶስ

ኢየሱስ በይሖዋ ዓላማ አፈጻጸም ውስጥ ምን ወሳኝ ድርሻ አለው?

ሥራ 4:12፤ 10:43፤ 2ቆሮ 1:20 ፊልጵ 2:9, 10

በተጨማሪም ምሳሌ 8:22, 23, 30, 31ዮሐ 1:10፤ ራእይ 3:14⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 16:13-17—ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ስለ ኢየሱስ ማንነት ሲናገር ክርስቶስና የአምላክ ልጅ እንደሆነ ገልጿል

    • ማቴ 17:1-9—ኢየሱስ በሦስት ሐዋርያቱ ፊት በተአምራዊ ሁኔታ በተለወጠበት ወቅት ይሖዋ ከሰማይ ልጁ እንደሆነ ተናግሯል

ኢየሱስን ከሌሎች የሰው ልጆች ሁሉ የሚለየው ምንድን ነው?

ዮሐ 8:58፤ 14:9, 10፤ ቆላ 1:15-17፤ 1ጴጥ 2:22

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 21:1-9—ኢየሱስ እንደ ድል አድራጊ ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ፣ በይሖዋ ስለተሾመው መሲሐዊ ንጉሥ የተነገረው ትንቢት ተፈጽሟል

    • ዕብ 7:26-28—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ታላቁ ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ከሌሎቹ ሊቃነ ካህናት ሁሉ የሚለየው እንዴት እንደሆነ አብራርቷል

ኢየሱስ የፈጸማቸው ተአምራት ስለ እሱና ስለ አባቱ ምን ያስተምሩናል?

ዮሐ 3:1, 2፤ 5:36

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 4:23, 24—ኢየሱስ በአጋንንት እንዲሁም በማንኛውም ዓይነት ሕመምና እክል ላይ ኃይል እንዳለው አሳይቷል

    • ማቴ 14:15-21—ኢየሱስ አምስት ዳቦና ሁለት ዓሣ ተጠቅሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በተአምር መግቧል

    • ማቴ 17:24-27—ኢየሱስ የይሖዋን አምልኮ ለመደገፍ እንዲሁም ሌሎችን ላለማሰናከል ሲል ለመዋጮ የሚሆን ገንዘብ በተአምር አስገኝቷል

    • ማር 1:40, 41—ኢየሱስ ለአንድ የሥጋ ደዌ ሕመምተኛ በጣም ስላዘነለት ፈወሰው፤ ይህም ሕመምተኞችን የሚፈውሰው ከልቡ ተነሳስቶ እንደሆነ ያሳያል

    • ማር 4:36-41—ኢየሱስ ኃይለኛ አውሎ ነፋስን ጸጥ አሰኝቷል፤ ይህም አባቱ በተፈጥሮ ኃይሎች ላይም እንኳ ሥልጣን እንደሰጠው ያሳያል

    • ዮሐ 11:11-15, 31-45—ኢየሱስ ወዳጁ አልዓዛር ሲሞት እንባውን አፍስሷል፤ ከዚያም አልዓዛርን ከሞት በማስነሳት ሞትንና በሰው ልጆች ላይ ያደረሰውን ሰቆቃ ምን ያህል እንደሚጠላ አሳይቷል

የኢየሱስ ትምህርት ዋነኛ ጭብጥ ምንድን ነው?

ኢየሱስ ምድር ሳለ የትኞቹን ማራኪ ባሕርያት አሳይቷል? እስቲ አንዳንዶቹን ተመልከት፦

ሩኅሩኅ፤ መሐሪ—ማር 5:25-34፤ ሉቃስ 7:11-15

በቀላሉ የሚቀረብ—ማቴ 13:2፤ ማር 10:13-16፤ ሉቃስ 7:36-50

ታዛዥ—ሉቃስ 2:40, 51, 52፤ ዕብ 5:8

ትሑት—ማቴ 11:29፤ 20:28፤ ዮሐ 13:1-5፤ ፊልጵ 2:7, 8

አፍቃሪ—ዮሐ 13:1፤ 14:31፤ 15:13፤ 1ዮሐ 3:16

ደፋር—ማቴ 4:2-11፤ ዮሐ 2:13-17፤ 18:1-6

ጥበበኛ—ማቴ 12:42፤ 13:54፤ ቆላ 2:3

ኢየሱስ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ የሰጠው ለምንድን ነው? ከዚህስ ምን ጥቅም እናገኛለን?

ኢየሱስ ክርስቶስ በሰማይ ንጉሥ ሆኖ እየገዛ መሆኑ የሚያስደስተን ለምንድን ነው?

መዝ 72:12-14፤ ዳን 2:44፤ 7:13, 14 ራእይ 12:9, 10

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 45:2-7, 16, 17—ይህ መዝሙር አምላክ የመረጠው ንጉሥ ጠላቶቹን ሁሉ ድል እንደሚያደርግ እንዲሁም በእውነት፣ በትሕትናና በጽድቅ እንደሚገዛ ያሳያል

    • ኢሳ 11:1-10—ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ምድርን ሲገዛ ምድር ሰላም የሰፈነባት ገነት ትሆናለች

ኢየሱስ በቅርቡ ምን ያደርጋል?