በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከዓለም ጋር መወዳጀት

ከዓለም ጋር መወዳጀት

ከአምላክ የራቀውን ዓለም የሚቆጣጠረው ማን ነው?

ኤፌ 2:2፤ 1ዮሐ 5:19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 4:5-8—ሰይጣን የዓለምን መንግሥታት እንደሚሰጠው ለኢየሱስ ነግሮታል፤ ኢየሱስም ቢሆን ሰይጣን እንዲህ ዓይነት ሥልጣን እንደሌለው አልተናገረም

የዓለም ወዳጅ ለመሆን መፈለግ ከይሖዋ ጋር ያለንን ወዳጅነት የሚነካብን እንዴት ነው?

ያዕ 4:4፤ 1ዮሐ 2:15, 16

በተጨማሪም ያዕ 1:27⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 18:1-3፤ 19:1, 2—ጥሩው ንጉሥ ኢዮሳፍጥ፣ ይሖዋ ክፉ አድርጎ ከቆጠረው ከንጉሥ አክዓብ ጋር ኅብረት በመፍጠሩ ተግሣጽ ተሰጥቶታል

ለዚህ ዓለም የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ማዳበር በጓደኛ ምርጫችን ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

ወዳጅነት” የሚለውን ተመልከት

ዓለም ለቁሳዊ ነገሮች ያለው አመለካከት እንዳይጋባብን መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ፍቅረ ንዋይ” የሚለውን ተመልከት

ዓለም ለመጥፎ የሥጋ ምኞቶች ያለው አመለካከት እንዳይጋባብን መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ክርስቲያኖች ለግለሰቦችም ሆነ ለድርጅቶች አምልኮ አከል ክብር የማይሰጡት ለምንድን ነው?

ማቴ 4:10፤ ሮም 1:25፤ 1ቆሮ 10:14

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 12:21-23—ቀዳማዊ ሄሮድስ አግሪጳ፣ አምልኮ አከል ክብር ሲሰጠው በመቀበሉ ይሖዋ ቀስፎታል

    • ራእይ 22:8, 9—አንድ ኃያል መልአክ፣ ሐዋርያው ዮሐንስ ሊሰግድለት ሲሞክር አልፈቀደለትም፤ አምልኮ የሚገባው ይሖዋ ብቻ እንደሆነ አበክሮ ገልጿል

ክርስቲያኖች ከፖለቲካና ከብሔራዊ ስሜት ገለልተኛ የሆኑት ለምንድን ነው?

ክርስቲያኖች ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ለመቀላቀል ፈቃደኛ የማይሆኑት ለምንድን ነው?

ሃይማኖትን መቀላቀል” የሚለውን ተመልከት

ክርስቲያኖች የይሖዋን መሥፈርቶች መከተልን ለድርድር የማያቀርቡት ለምንድን ነው?

ይህ ዓለም ብዙውን ጊዜ የክርስቶስን ተከታዮች የሚጠላቸውና የሚያሳድዳቸው ለምንድን ነው?

ከዚህ ዓለም ጋር ቁርኝት መፍጠር ሞኝነት የሆነው ለምንድን ነው?

ክርስቲያኖች ይሖዋን ለማያገለግሉ ሰዎች ፍቅርና ደግነት የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ክርስቲያኖች የመንግሥትን ሕጎች፣ መሪዎችንና ባለሥልጣናትን ማክበር ያለባቸው ለምንድን ነው?

ማቴ 22:21፤ ሮም 13:1-7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 25:8፤ 26:2, 25—ሐዋርያው ጳውሎስ የዘመኑ መንግሥት ያወጣቸውን ሕጎች ታዝዟል፤ ለመሪዎችም አክብሮት አሳይቷል