የማዕረግ ስሞች
ክርስቲያኖች በሃይማኖታዊ የማዕረግ ስሞች ሊጠሩ ይገባል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሉቃስ 18:18, 19—ኢየሱስ በባሕርይው ጥሩ ቢሆንም “ጥሩ መምህር” በሚለው የማዕረግ ስም መጠራት አልፈለገም፤ ለጥሩነቱ እውቅና ሊሰጠው የሚገባው ይሖዋ ብቻ እንደሆነ ተናግሯል
-
ክርስቲያኖች ሌሎች ሰዎችን እንደ “አባት” ወይም “መሪ” ባሉ ሃይማኖታዊ የማዕረግ ስሞች መጥራት የሌለባቸው ለምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 23:9-12—ኢየሱስ ተከታዮቹ እንደ “አባት” ወይም “መሪ” ያሉ የማዕረግ ስሞችን እንዳይጠቀሙ ከልክሏል
-
1ቆሮ 4:14-17—ሐዋርያው ጳውሎስ ለብዙዎች እንደ አባት ቢሆንም ‘አባ ጳውሎስ’ ተብሎ ወይም በሌላ መሰል መጠሪያ የተጠራበትን ቦታ አናገኝም
-
ክርስቲያኖች አንዳቸው ሌላውን እንደ ወንድም ወይም እህት ማየትና እንደዚያ ብለው መጥራት ያለባቸው ለምንድን ነው?
በተጨማሪም ሥራ 12:17፤ 18:18፤ ሮም 16:1ን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 12:46-50—ኢየሱስ የእምነት አጋሮቹ፣ መንፈሳዊ ወንድሞቹና እህቶቹ እንደሆኑ ተናግሯል
-
ክርስቲያኖች የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ መሪዎችንና ዳኞችን በማዕረግ ስማቸው መጥራታቸው ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 26:1, 2, 25—ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ አግሪጳ እና ፊስጦስ ያሉ ገዢዎችን ሲጠራ የማዕረግ ስማቸውን ተጠቅሟል
-