የጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር
ሌሎች እንደጠበቅናቸው ሳይሆኑ ሲቀሩ፣ ሲጎዱን ይባስ ብሎም ሲከዱን
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
1ሳሙ 8:1-6—ነቢዩ ሳሙኤል፣ እስራኤላውያን መጥተው ንጉሥ ካላነገሥክልን ሲሉት ቅር ተሰኝቷል
1ሳሙ 20:30-34—ዮናታን፣ አባቱ ንጉሥ ሳኦል በቁጣ በመናገር ስላዋረደው ስሜቱ ተጎድቷል
የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦
በተጨማሪም ምሳሌ 19:11፤ ፊልጵ 4:8ን ተመልከት
የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
መዝ 55:12-14, 16-18, 22—ንጉሥ ዳዊት የቅርብ ወዳጁ የሆነው አኪጦፌል ቢከዳውም ሸክሙን በይሖዋ ላይ ጥሏል፤ ይህም አጽናንቶታል
2ጢሞ 4:16-18—ሐዋርያው ጳውሎስ ፈተና ውስጥ ሳለ አንዳንዶች ትተውት ሄደዋል፤ ሆኖም ይሖዋ ኃይል ሰጥቶታል፤ ተስፋውም አበርትቶታል
በራሳችን ድክመት ወይም ኃጢአት የተነሳ፣ የጠበቅነው ሳይሆን ሲቀር
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
መዝ 51:1-5—ንጉሥ ዳዊት በይሖዋ ላይ በፈጸመው ኃጢአት የተነሳ፣ በበደለኝነት ስሜት ተደቁሷል
ሮም 7:19-24—ሐዋርያው ጳውሎስ ከኃጢአት ዝንባሌ ጋር በሚያደርገው የማያባራ ትግል የተነሳ ከንቱነት ተሰምቶታል
የሚያጽናኑ ጥቅሶች፦
የሚያጽናኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
1ነገ 9:2-5—ንጉሥ ዳዊት ከባድ ኃጢአቶች ቢሠራም ይሖዋ የሚያስታውሰው በንጹሕ አቋም ጠባቂነቱ ነው
1ጢሞ 1:12-16—ሐዋርያው ጳውሎስ በቀድሞ ሕይወቱ አስከፊ ነገሮች ቢያደርግም ምሕረት እንደሚያገኝ ተማምኗል