በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ይሖዋ

ይሖዋ

ስሙ

ይሖዋ የሚለው ስም “እንዲሆን ያደርጋል” የሚል ትርጉም እንዳለው ይታመናል

ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ሲል የትኞቹን ነገሮች ይሆናል?

የአምላክ ስም መቀደስ ከሁሉ የላቀ ቦታ የሚሰጠው ለምንድን ነው?

የአጽናፈ ዓለም ሉዓላዊ ገዢ የሆነው ይሖዋ ታዛዥነታችን የሚገባው ለምንድን ነው?

ከይሖዋ የማዕረግ ስሞች አንዳንዶቹ

ሁሉን ቻይ— ዘፍ 17:1፤ ራእይ 19:6

ሉዓላዊው ጌታ—ኢሳ 25:8፤ አሞጽ 3:7

ልዑል አምላክ—ዘፍ 14:18-22፤ መዝ 7:17

ታላቅ አስተማሪ—ኢሳ 30:20

አባት—ማቴ 6:9፤ ዮሐ 5:21

ዓለት—ዘዳ 32:4፤ ኢሳ 26:4

የሠራዊት ጌታ ይሖዋ—1ሳሙ 1:11

የዘላለም ንጉሥ—1ጢሞ 1:17፤ ራእይ 15:3

ግርማዊ—ዕብ 1:3፤ 8:1

ከይሖዋ አስደናቂ ባሕርያት አንዳንዶቹ

ይሖዋ ቅድስናውን አጉልቶ የገለጸው እንዴት ነው? አገልጋዮቹስ ይህን ማወቃቸው ምን እንዲያደርጉ ሊያነሳሳቸው ይገባል?

ዘፀ 28:36፤ ዘሌ 19:2፤ 2ቆሮ 7:1 1ጴጥ 1:13-16

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢሳ 6:1-8—ነቢዩ ኢሳይያስ የይሖዋን ቅድስና በራእይ ሲመለከት ይሖዋን ለማገልገል ብቁ እንዳልሆነ ተሰምቶት ነበር፤ ሆኖም ከሱራፌል አንዱ መጥቶ ኃጢአተኛ የሰው ልጆችም እንኳ በአምላክ ዓይን ንጹሕ ተደርገው ሊቆጠሩ እንደሚችሉ አረጋገጠለት

    • ሮም 6:12-23፤ 12:1, 2—ሐዋርያው ጳውሎስ የኃጢአት ዝንባሌዎችን መዋጋትና “በቅድስና ጎዳና” ላይ መሄድ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ገልጿል

ይሖዋ ምን ያህል ኃያል ነው? ኃይሉን የሚጠቀምባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ዘፀ 15:3-6፤ 2ዜና 16:9፤ ኢሳ 40:22, 25, 26, 28-31

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 8:12-18—ነቢዩ ሙሴ፣ ሕዝቡ ያሏቸውን መልካም ነገሮች ሁሉ ያገኙት ይሖዋ ኃይሉን ተጠቅሞ ስለባረካቸው እንደሆነ ነግሯቸዋል

    • 1ነገ 19:9-14—ይሖዋ፣ ተስፋ የቆረጠውን ነቢዩን ኤልያስን ለማበረታታት ኃይሉ የተገለጠባቸውን አስደናቂ ነገሮች አሳይቶታል

ይሖዋ በፍትሑ ተወዳዳሪ የለውም የምንለው ለምንድን ነው?

ዘዳ 32:4፤ ኢዮብ 34:10፤ 37:23 መዝ 37:28፤ ኢሳ 33:22

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 24:16-22—የሙሴ ሕግ እንደሚያሳየው የይሖዋ ፍትሕ ከምሕረቱና ከፍቅሩ ጋር ሙሉ በሙሉ ይጣጣማል

    • 2ዜና 19:4-7—ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ለሾማቸው ፈራጆች ማሳሰቢያ ሲሰጥ እንደ ሰው ሳይሆን እንደ ይሖዋ እንዲፈርዱ ነግሯቸዋል

ይሖዋ በጥበቡ ተወዳዳሪ እንደሌለው የሚያሳየው ምንድን ነው?

መዝ 104:24፤ ምሳሌ 2:1-8፤ ኤር 10:12፤ ሮም 11:33፤ 16:27

በተጨማሪም መዝ 139:14፤ ኤር 17:10⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 4:29-34—ይሖዋ፣ ንጉሥ ሰለሞንን በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይበልጥ ጥበበኛ በማድረግ ባርኮታል

    • ሉቃስ 11:31፤ ዮሐ 7:14-18—ኢየሱስ በጥበቡ ከሰለሞን ይበልጣል፤ ሆኖም ኢየሱስ ጥበቡን ያገኘው ከይሖዋ እንደሆነ በትሕትና ተናግሯል

ይሖዋ ዋነኛ ባሕርይው ፍቅር መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

ዮሐ 3:16፤ ሮም 8:32፤ 1ዮሐ 4:8-10, 19

በተጨማሪም ሶፎ 3:17፤ ዮሐ 3:35⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 10:29-31—ኢየሱስ የድንቢጥን ምሳሌ በመጠቀም ይሖዋ አገልጋዮቹን በግለሰብ ደረጃ ምን ያህል እንደሚወዳቸውና ከፍ አድርጎ እንደሚመለከታቸው አሳይቷል

    • ማር 1:9-11—ይሖዋ ከሰማይ ልጁን አነጋግሮታል፤ አፍቃሪ የሆነ ወላጅ እንደሚያደርገው ሁሉ እንደሚወደውና እንደሚደሰትበት በይፋ ነግሮታል

ወደ ይሖዋ ለመቅረብ የሚያነሳሱን ሌሎች ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው? መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተጠቀሱት የይሖዋ ማራኪ ባሕርያት መካከል ከታች የተዘረዘሩት ይገኙበታል፦

ሁሉን የሚያይ— 2ዜና 16:9፤ ምሳሌ 15:3

ለጋስ—መዝ 104:13-15፤ 145:16

መሐሪ—ዘፀ 34:6

ሩኅሩኅ—ኢሳ 49:15፤ 63:9፤ ዘካ 2:8

ሰላማዊ—ፊልጵ 4:9

ታማኝ—ራእይ 15:4

ታጋሽ—ኢሳ 30:18፤ 2ጴጥ 3:9

ትሑት—መዝ 18:35

ክብራማ—ራእይ 4:1-6

ዘላለማዊ፤ መጀመሪያም ሆነ መጨረሻ የሌለው—መዝ 90:2፤ 93:2

የማይለዋወጥ፤ እምነት የሚጣልበት—ሚል 3:6ያዕ 1:17

ደስተኛ—1ጢሞ 1:11

ደግ—ሉቃስ 6:35፤ ሮም 2:4

ግርማዊ—መዝ 8:1፤ 148:13

ጻድቅ—መዝ 7:9

ይሖዋን ይበልጥ እያወቅነው ስንሄድ ምን እናደርጋለን?

ይሖዋን ማገልገል ያለብን እንዴት ነው?

ይሖዋ ከአገልጋዮቹ በሚጠብቀው ነገር ምክንያታዊ እንደሆነ የሚያሳየው ምንድን ነው?

ዘዳ 10:12፤ ሚክ 6:8፤ 1ዮሐ 5:3

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 30:11-14—በነቢዩ ሙሴ በኩል የተሰጠው ሕግ ለእስራኤላውያን ያን ያህል ከባድ አልነበረም

    • ማቴ 11:28-30—አባቱን ፍጹም በሆነ መንገድ የመሰለው ኢየሱስ፣ ደግና እረፍት የሚሰጥ ጌታ መሆኑን ለተከታዮቹ አረጋግጦላቸዋል

ይሖዋን ማወደሳችን ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?

መዝ 105:1, 2፤ ኢሳ 43:10-12, 21

በተጨማሪም ኤር 20:9፤ ሉቃስ 6:45ሥራ 4:19, 20⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 104:1, 2, 10-20, 33, 34—መዝሙራዊው ፍጥረትን ሲመለከት ይሖዋን በመዝሙር ለማወደስ የሚያነሳሳ ብዙ ምክንያት እንዳለው ተሰምቶታል

    • መዝ 148:1-14—የይሖዋ የፍጥረት ሥራዎችና መላእክቱ በሙሉ ይሖዋን ያወድሱታል፤ እኛም ልናወድሰው ይገባል

ምግባራችን ስለ ይሖዋ ምሥክርነት የሚሰጠው እንዴት ነው?

ማቴ 5:16፤ ዮሐ 15:8፤ 1ጴጥ 2:12

በተጨማሪም ያዕ 3:13⁠ን ተመልከት

ወደ ይሖዋ ይበልጥ ለመቅረብ ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

ትሕትና ወደ ይሖዋ ለመቅረብ የሚረዳን እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማሰላሰል ወደ ይሖዋ ለመቅረብ የሚረዳን እንዴት ነው?

ስለ ይሖዋ የተማርነውን ነገር በተግባር ማዋላችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ከይሖዋ ምንም ነገር ለመደበቅ ፈጽሞ መሞከር የሌለብን ለምንድን ነው?

ኢዮብ 34:22፤ ምሳሌ 28:13፤ ኤር 23:24፤ 1ጢሞ 5:24, 25

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ነገ 5:20-27—ግያዝ ኃጢአቱን ለመደበቅ ሞከረ፤ ይሖዋ ግን ነቢዩ ኤልሳዕ እውነቱን እንዲያውቅ አደረገ

    • ሥራ 5:1-11—ሐናንያና ሰጲራ ለመደበቅ የሞከሩት ነገር ተጋልጧል፤ መንፈስ ቅዱስን በመዋሸታቸውም ተቀጥተዋል