ይቅር ባይነት
ይሖዋ ይቅር ለማለት ምን ያህል ፍላጎት አለው?
በተጨማሪም 2ጴጥ 3:9ን ተመልከት
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
መዝ 78:40, 41፤ 106:36-46—ዓመፀኛ የሆኑት እስራኤላውያን ብዙ ጊዜ ቢያሳዝኑትም ይሖዋ በተደጋጋሚ ይቅር ብሏቸዋል
-
ሉቃስ 15:11-32—ኢየሱስ የይሖዋን ይቅርታ የሚያጎላ አንድ ምሳሌ ተናግሯል፤ ምሳሌው አንድ መሐሪ አባት፣ ከመጥፎ አካሄዱ የተመለሰውን ልጁን እንዴት እንደያዘው ይተርካል
-
ይሖዋ ኃጢአታችንን ይቅር የሚለው ምንን መሠረት በማድረግ ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዕብ 9:22-28—ሐዋርያው ጳውሎስ፣ የክርስቶስ ደም የኃጢአት ይቅርታ የሚገኝበት ብቸኛው መንገድ እንደሆነ አስረድቷል
-
ራእይ 7:9, 10, 14, 15—ሐዋርያው ዮሐንስ፣ በፈሰሰው የክርስቶስ ደም አማካኝነት በአምላክ ዘንድ ንጹሕ ተደርገው የተቆጠሩ “እጅግ ብዙ ሕዝብ” በራእይ ተመልክቷል
-
ይሖዋ ይቅር እንዲለን ከፈለግን ሌሎች ሲበድሉን ምን ማድረግ አለብን?
ማቴ 6:14, 15፤ ማር 11:25፤ ሉቃስ 17:3, 4፤ ያዕ 2:13
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ኢዮብ 42:7-10—ይሖዋ የኢዮብ መከራ እንዲያበቃ እንዲሁም ጤንነቱና ብልጽግናው እንዲመለስለት ከማድረጉ በፊት፣ ስህተት ለሠሩት ወዳጆቹ እንዲጸልይ ነግሮታል
-
ማቴ 18:21-35—ኢየሱስ፣ ይቅር መባል ከፈለግን ሌሎችን ይቅር ማለት ያለውን አስፈላጊነት ሕያው በሆነ ምሳሌ አስረድቷል
-
ኃጢአትን መናዘዝና ከልብ ንስሐ መግባት ምን ያህል አስፈላጊ ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
መዝ 32:1-5፤ 51:1, 2, 16, 17—ንጉሥ ዳዊት በሠራቸው ከባድ ኃጢአቶች የተነሳ ተደቁሷል እንዲሁም ልቡ ተሰብሯል፤ ደግሞም ለኃጢአቱ ከልቡ ንስሐ ገብቷል
-
ያዕ 5:14-16—ያዕቆብ ከባድ ኃጢአት ከሠራን ለሽማግሌዎች መንገር እንዳለብን ተናግሯል
-
ይሖዋ ይቅር እንዲለን ከፈለግን ምን ለውጥ ማድረግ አለብን?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ነገ 21:27-29፤ 2ዜና 18:18-22, 33, 34፤ 19:1, 2—ንጉሥ አክዓብ የተላለፈበትን ፍርድ ሲሰማ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ ይሖዋም በተወሰነ መጠን ምሕረት አደረገለት፤ ሆኖም እውነተኛ የንስሐ ፍሬ ስላላሳየ ይሖዋ እሱን ክፉ አድርጎ መመልከቱን አልተወም፤ እንዲሞትም አድርጓል
-
2ዜና 33:1-16—ምናሴ በጣም ክፉ ንጉሥ ነበር፤ ንስሐ ሲገባ ግን ይሖዋ ይቅር አለው። ምናሴ ጣዖት አምልኮን በማስወገድና እውነተኛውን አምልኮ በማስፋፋት ከልቡ እንደተለወጠ አሳይቷል
-
ይሖዋ ንስሐ የገቡ ኃጢአተኞችን ይቅር የሚለው እስከ ምን ድረስ ነው?
መዝ 103:10-14፤ ኢሳ 1:18፤ 38:17፤ ኤር 31:34፤ ሚክ 7:19
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
2ሳሙ 12:13፤ 24:1፤ 1ነገ 9:4, 5—ንጉሥ ዳዊት በጣም ከባድ ኃጢአቶች ቢፈጽምም ንስሐ በመግባቱ ይሖዋ ይቅር ብሎታል፤ ከጊዜ በኋላ ስለ እሱ ሲናገር ንጹሕ አቋሙን እንደጠበቀ መሥክሮለታል
-
ኢየሱስ ይቅር ለማለት ፈቃደኛ በመሆን ረገድ ይሖዋን ፍጹም በሆነ መንገድ የመሰለው እንዴት ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 26:36, 40, 41—ኢየሱስ የቅርብ ተከታዮቹን እርዳታ በጣም በሚፈልግበት ወቅት እነሱ እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር፤ ሆኖም ኢየሱስ ድካማቸውን ተረድቶላቸዋል
-
ማቴ 26:69-75፤ ሉቃስ 24:33, 34፤ ሥራ 2:37-41—ጴጥሮስ፣ ኢየሱስን አላውቀውም ብሎ ሦስት ጊዜ ክዶታል፤ ንስሐ በመግባቱ ግን ክርስቶስ ይቅር ብሎታል፤ ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለጴጥሮስ በግል ተገልጦለታል፤ በኋላ ላይ ደግሞ በጉባኤው ውስጥ ለየት ያሉ ኃላፊነቶች ሰጥቶታል
-
የይሖዋ ይቅርታ ገደብ እንዳለው እንዴት እናውቃለን?
ማቴ 12:31፤ ዕብ 10:26, 27፤ 1ዮሐ 5:16, 17
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 23:29-33—ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በቡድን ደረጃ የገሃነም ፍርድ ማለትም ዘላለማዊ ጥፋት እንደሚጠብቃቸው ኢየሱስ አስጠንቅቋል
-
ዮሐ 17:12፤ ማር 14:21—ኢየሱስ የአስቆሮቱ ይሁዳን ‘የጥፋት ልጅ’ ሲል ጠርቶታል፤ ይህ ከሃዲ ባይወለድ ይሻለው እንደነበረም ተናግሯል
-
ክርስቲያኖች ይቅር ለማለት እንዲነሳሱ ምን ሊረዳቸው ይችላል?