ገንዘብ
ገንዘብን መውደድ አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው?
“ፍቅረ ንዋይ” የሚለውን ተመልከት
ቤተሰብን ለማስተዳደር የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት መሥራት ምንም ስህተት እንደሌለው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያሳየው እንዴት ነው?
መክ 7:12፤ 10:19፤ ኤፌ 4:28፤ 2ተሰ 3:10፤ 1ጢሞ 5:8, 18
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፍ 31:38-42—ያዕቆብ ቤተሰቡን ለማስተዳደር ሲል ለአማቱ ለላባ በሐቀኝነት ሠርቷል፤ ላባ አግባብ ያልሆነ ነገር ቢያደርግበትም ይሖዋ ድካሙን አይቶ ያዕቆብን ባርኮታል
-
ሉቃስ 19:12, 13, 15-23—ኢየሱስ ከተናገረው ምሳሌ እንደምንረዳው ትርፍ ለማግኘት ገንዘብን ሥራ ላይ ማዋል በዘመኑ የተለመደ ነገር ነበር
-
ገንዘብ ከመበደርና ከማበደር ጋር በተያያዘ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች መመሪያ ይሆኑናል?
አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ አለመግባት የተሻለ የሆነው ለምንድን ነው?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ነህ 5:2-8—በአገረ ገዢው ነህምያ ዘመን የነበሩ አበዳሪዎች በተበዳሪዎቻቸው ላይ ግፍ ይፈጽሙ ነበር
-
ማቴ 18:23-25—ከኢየሱስ ምሳሌ እንደምንረዳው ብድር መመለስ ያልቻለ ተበዳሪ ቅጣት ሊደርስበት ይችላል
-
አንድ ክርስቲያን፣ ከማያምን ሰውም ሆነ ከእምነት ባልንጀራው ሌላው ቀርቶ ከቤተሰቡ አባል ጋር የንግድ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ምን ጥንቃቄዎች መውሰድ አለበት?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፍ 23:14-20—አብርሃም ለሣራ መቃብር እንዲሆን ዋሻ ያለው እርሻ በገዛ ጊዜ ግዢውን በምሥክሮች ፊት ፈጽሟል፤ ይህን ያደረገው ወደፊት ሊከሰት የሚችል አለመግባባትን ወይም ግጭትን ለማስቀረት ብሎ ሳይሆን አይቀርም
-
ኤር 32:9-12—ነቢዩ ኤርምያስ ከአጎቱ ልጅ መሬት ሲገዛ ውልና ግልባጭ አዘጋጀ፤ ከዚያም ግዢውን በምሥክሮች ፊት ፈጸመ
-
በጀት ማውጣት ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?
ክርስቲያኖች ከገንዘብ ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች በጉባኤው ውስጥ ክፍፍል እንዲፈጥሩ መፍቀድ የሌለባቸው ለምንድን ነው?
እውነተኛ ደስታ የምናገኘው ገንዘባችንን እንዴት ብንጠቀምበት ነው?