በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥናት

ጥናት

አንድ ክርስቲያን የአምላክን ቃል አዘውትሮ ማጥናት ያለበት ለምንድን ነው?

መዝ 1:1-3፤ ምሳሌ 18:15፤ 1ጢሞ 4:6፤ 2ጢሞ 2:15

በተጨማሪም ሥራ 17:11⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 119:97-101—መዝሙራዊው ለአምላክ ሕግ ስላለው ፍቅር እንዲሁም ሕጉን በሕይወቱ ውስጥ ተግባራዊ ማድረጉ ስላስገኘለት ጥቅሞች በመንፈስ መሪነት ጽፏል

    • ዳን 9:1-3 ግርጌ—ዳንኤል ቅዱሳን መጻሕፍትን በማጥናት፣ እስራኤላውያን በግዞት የሚቆዩባቸው 70 ዓመታት ማብቂያ እንደተቃረበ ተረዳ

እውቀት መቅሰማችንን መቀጠል ያለብን ለምንድን ነው?

ዕብ 6:1-3፤ 2ጴጥ 3:18

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ምሳሌ 4:18—የማለዳ ብርሃን እየደመቀ እንደሚሄድ ሁሉ መንፈሳዊ ሰው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ያለው ግንዛቤም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠራ ይሄዳል፤ ምክንያቱም ይሖዋ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን የሚገልጠው ደረጃ በደረጃ ነው

    • ማቴ 24:45-47—ኢየሱስ በመጨረሻዎቹ ቀናት መንፈሳዊ ምግብ በወቅቱ የሚያቀርብ “ታማኝና ልባም ባሪያ” እንደሚሾም አስቀድሞ ተናግሯል

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥበብ ሰብዓዊ ፍልስፍናን በያዙ መጻሕፍት ላይ ካለው ከማንኛውም ጥበብ የላቀው ለምንድን ነው?

ይሖዋ መጽሐፍ ቅዱስን በቅንነት ለሚያጠኑ ሰዎች ምን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቷል?

ከግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ጥቅም ለማግኘት ይሖዋ ምን እንዲሰጠን መጸለይ ያስፈልገናል?

ሉቃስ 11:13፤ 1ቆሮ 2:10፤ ያዕ 1:5

በተጨማሪም መዝ 119:66⁠ን ተመልከት

“ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚያቀርብልንን መንፈሳዊ ምግብ በሙሉ ጥሩ አድርገን ልንጠቀምበት የሚገባው ለምንድን ነው?

ማቴ 24:45-47

በተጨማሪም ማቴ 4:4፤ 1ጢሞ 4:15⁠ን ተመልከት

ለዝርዝር ጉዳዮች ሳይቀር ትኩረት በመስጠት ትክክለኛ እውቀት ለማግኘት ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

ጥበብና ማስተዋል ማግኘታችን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

ረጋ ብለን እንዲሁም ቃላቱን በደንብ እያሰብን ማንበብ ያለብን ለምንድን ነው?

የአምላክን ቃል በሕይወታችን ውስጥ እንዴት ተግባራዊ እንደምናደርገው ማሰብ ያለብን ለምንድን ነው?

የተማርነውን ነገር ለሌሎች እንዴት እንደምናካፍል ማሰላሰል ያለብን ለምንድን ነው?

አስፈላጊ እውነቶችን ደጋግመን ማጥናታችን ምን ጥቅም አለው?

2ጴጥ 1:13፤ 3:1, 2

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘዳ 6:6, 7፤ 11:18-20—ይሖዋ፣ ሕዝቡ የእሱን ቃል በልጆቻቸው ልብ ውስጥ እንዲቀርጹና ደጋግመው እንዲያስተምሯቸው አዟቸዋል

የአምላክን ቃል በቤተሰብ መወያየት ምን ጥቅም አለው?

ኤፌ 6:4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 18:17-19—አብርሃም ጽድቅ ስለሆነው የሕይወት መንገድ ቤተሰቡን እንዲያስተምር ይሖዋ ነግሮታል

    • መዝ 78:5-7—በእስራኤል ብሔር ውስጥ እያንዳንዱ ትውልድ ቀጣዩን ትውልድ እንዲያስተምር ይጠበቅበት ነበር፤ የዚህም ዓላማ ሕዝቡ በትውልዶቹ ሁሉ በይሖዋ ታምኖ እንዲኖር ነው

ከጉባኤው ጋር አብረን ማጥናት የሚጠቅመን እንዴት ነው?

ዕብ 10:25

በተጨማሪም ምሳሌ 18:1⁠ን ተመልከት