በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጽናት

ጽናት

የይሖዋ አገልጋዮች ጽናት ያስፈልጋቸዋል?

አንዳንዶች ለምንሰብከው መልእክት ግድየለሽ እንደሚሆኑ ይባስ ብሎም እንደሚቃወሙን መጠበቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 10:22፤ ዮሐ 15:18, 19፤ 2ቆሮ 6:4, 5

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ጴጥ 2:5፤ ዘፍ 7:23፤ ማቴ 24:37-39 —ኖኅ “የጽድቅ ሰባኪ” ሰባኪ ቢሆንም አብዛኞቹ ሰዎች አልሰሙትም፤ ከጥፋት ውኃው የተረፉት እሱና ቤተሰቡ ብቻ ናቸው

    • 2ጢሞ 3:10-14—ሐዋርያው ጳውሎስ የራሱን ምሳሌ በመጥቀስ ጢሞቴዎስን እንዲጸና አበረታቶታል

የቤተሰባችን አባላት እንኳ ሊቃወሙን እንደሚችሉ መጠበቅ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 10:22, 36-38፤ ሉቃስ 21:16-19

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 4:3-11፤ 1ዮሐ 3:11, 12—ቃየን የእሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ የአቤል ሥራ ግን ጽድቅ ስለነበረ ወንድሙን ገድሎታል

    • ዘፍ 37:5-8, 18-28—ዮሴፍ በወንድሞቹ ጥቃት ደርሶበታል፤ እንዲሁም ለባርነት ሸጠውታል፤ ለዚህ አንዱ ምክንያት ከይሖዋ የተገለጠለትን ሕልም መናገሩ ነው

ስደት ሲደርስብን ሞትን መፍራት የሌለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 10:28፤ 2ጢሞ 4:6, 7

በተጨማሪም ራእይ 2:10⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 3:1-6, 13-18—ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ አቋማቸውን አላልተው ጣዖት ከማምለክ ይልቅ ሞትን መርጠዋል

    • ሥራ 5:27-29, 33, 40-42—ሐዋርያቱ የግድያ ዛቻ ቢሰነዘርባቸውም በስብከቱ ሥራ ጸንተዋል

ተግሣጽ በሚሰጠን ጊዜም እንኳ ለይሖዋ ታማኝ ሆነን ለመጽናት ምን ሊረዳን ይችላል?

ምሳሌ 3:11, 12፤ ዕብ 12:5-7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘኁ 20:9-12፤ ዘዳ 3:23-28፤ 31:7, 8—የይሖዋ ተግሣጽ ነቢዩ ሙሴን አሳዝኖታል፤ ሆኖም እስከ ሕይወቱ መጨረሻ ጸንቷል

    • 2ነገ 20:12-18፤ 2ዜና 32:24-26—ንጉሥ ሕዝቅያስ ኃጢአት በመሥራቱ እርማት ተሰጠው፤ ሆኖም ራሱን ዝቅ ያደረገ ከመሆኑም ሌላ በቀረው ሕይወቱ በታማኝነት ጸንቷል

የሌሎች ታማኝ አለመሆን መጽናት ከባድ እንዲሆንብን ሊያደርግ የሚችለው እንዴት ነው?

ኤር 1:16-19፤ ዕን 1:2-4

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • መዝ 73:2-24—መዝሙራዊው፣ ክፉዎች በሰላምና በብልጽግና እንደሚኖሩ ሲያይ ይሖዋን በጽናት ማገልገሉ ያለውን ጥቅም እስከመጠራጠር ደርሷል

    • ዮሐ 6:60-62, 66-68—ሐዋርያው ጴጥሮስ ብዙዎች ኢየሱስን መከተላቸውን ቢያቆሙም እንኳ በእምነቱ ለመጽናት ቆርጧል

ለመጽናት ምን ይረዳናል?

ከይሖዋ ጋር መጣበቅ

የአምላክን ቃል በማጥናትና በማሰላሰል እውቀት ማግኘት

ለይሖዋ አዘውትሮ ከልብ የመነጨ ጸሎት ማቅረብ

ሮም 12:12፤ ቆላ 4:2፤ 1ጴጥ 4:7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 6:4-11—ነቢዩ ዳንኤል ሕይወቱን ለማጥፋት ሴራ እንደተጠነሰሰበት ቢያውቅም በይፋ አዘውትሮ መጸለዩን ቀጥሏል

    • ማቴ 26:36-46፤ ዕብ 5:7—ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው የመጨረሻ ምሽት አጥብቆ ጸልዮአል፤ ሌሎችም እንዲህ እንዲያደርጉ አሳስቧል

ከእምነት ባልንጀሮቻችን ጋር ይሖዋን ለማምለክ አዘውትረን መሰብሰብ

አእምሯችን ይሖዋ ቃል በገባልን ሽልማት ላይ እንዲያተኩር ማድረግ

ለይሖዋ፣ ለክርስቲያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንዲሁም ለጽድቅ ያለንን ፍቅር ማጠናከር

እምነታችንን ማጠናከር

ለችግሮቻችን ትክክለኛውን አመለካከት ማዳበር

በታማኝነት መጽናት ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች አንዳንዶቹ ምንድን ናቸው?

ይሖዋ አምላክን እናስከብራለን

ምሳሌ 27:11፤ ዮሐ 15:7, 8፤ 1ጴጥ 1:6, 7

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 1:6-12፤ 2:3-5—ሰይጣን በኢዮብ ንጹሕ አቋም ጠባቂነት ላይ በይሖዋ ፊት ጥያቄ አነሳ፤ ጥያቄው መልስ ማግኘት የሚችለው ኢዮብ በታማኝነት ከጸና ብቻ ነው

    • ሮም 5:19፤ 1ጴጥ 1:20, 21—ከአዳም በተቃራኒ ኢየሱስ በታማኝነት ጸንቷል፤ ይህም ‘አንድ ፍጹም ሰው እስከ መጨረሻው ቢፈተን ንጹሕ አቋሙን መጠበቅ ይችላል?’ ለሚለው ወሳኝ ጥያቄ መልስ አስገኝቷል

ሌሎችም እንዲጸኑ እናበረታታለን

ጽናት አገልግሎታችን ፍሬያማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ያደርጋል

በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንዲሁም ቃል የተገቡልንን ሽልማቶች እናገኛለን