በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጽድቅ

ጽድቅ

ትክክል ወይም ፍትሐዊ የሆነውን ነገር የመወሰን ሥልጣን ያለው ማን ብቻ ነው?

ዘዳ 32:4፤ ሕዝ 33:17-20

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 18:23-33—ይሖዋ፣ ጻድቅ ዳኛ መሆኑን ለአብርሃም አሳይቶታል

    • መዝ 72:1-4, 12-14—በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ይህ መዝሙር፣ የይሖዋን ጽድቅ ፍጹም በሆነ መንገድ የሚያንጸባርቀውን መሲሐዊውን ንጉሥ ያወድሳል

የይሖዋን የጽድቅ መሥፈርቶች አክብረን መኖራችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?

መዝ 37:25, 29፤ ያዕ 5:16፤ 1ጴጥ 3:12

በተጨማሪም መዝ 35:24፤ ኢሳ 26:9ሮም 1:17⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 37:22-24—ኤሊሁ፣ ይሖዋን በጽድቁ አወድሶታል፤ የይሖዋ ጽድቅ አገልጋዮቹ ለእሱ ጥልቅ አክብሮት እንዲያድርባቸው ያደርጋል

    • መዝ 89:13-17—መዝሙራዊው፣ አገዛዙ በጽድቅ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ይሖዋን አወድሶታል

የአምላክን ጽድቅ መፈለግ ሲባል ምን ማለት ነው?

ሕዝ 18:25-31፤ ማቴ 6:33፤ ሮም 12:1, 2፤ ኤፌ 4:23, 24

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 6:9, 22፤ 7:1—ኖኅ ይሖዋ ያዘዘውን ነገር ሁሉ ልክ እሱ በነገረው መሠረት በማድረግ ጻድቅ መሆኑን አሳይቷል

    • ሮም 4:1-3, 9—አብርሃም በይሖዋ ላይ አስደናቂ እምነት እንዳለው በማሳየቱ ይሖዋ ጻድቅ አድርጎ ቆጥሮታል

ሌሎችን ለማስደመም ብለን ሳይሆን ለይሖዋ ባለን ፍቅር ተነሳስተን ጻድቅ ለመሆን ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

ማቴ 6:1፤ 23:27, 28፤ ሉቃስ 16:14, 15፤ ሮም 10:10

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማቴ 5:20፤ 15:7-9—ኢየሱስ፣ ሕዝቡ ጻድቅ እንዲሆኑ ሆኖም ጽድቃቸው ግብዝ የሆኑት ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ባወጡት መሥፈርት መሠረት እንዳይሆን አስተምሯል

    • ሉቃስ 18:9-14—ኢየሱስ፣ ራሳቸውን በማመጻደቅ ጻድቅ መስለው ለመታየት የሚሞክሩ ሰዎችን ለማረም አንድ ምሳሌ ተናግሯል

ጥሩነት ከጽድቅም እንኳ የሚበልጠው ለምንድን ነው?

ራሳችንን እንዳናመጻድቅ ወይም ከሌሎች በላይ ጻድቅ መስለን ለመታየት እንዳንሞክር መጠንቀቅ ያለብን ለምንድን ነው?