በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ፍቅረ ንዋይ

ፍቅረ ንዋይ

መጽሐፍ ቅዱስ የገንዘብ ወይም የንብረት ባለቤት መሆንን ያወግዛል?

መክ 7:12

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ነገ 3:11-14—ንጉሥ ሰለሞን ትሑት በመሆኑ ይሖዋ ብዙ ሀብት በመስጠት ባርኮታል

    • ኢዮብ 1:1-3, 8-10—ኢዮብ የናጠጠ ሀብታም ነበር፤ በዋነኝነት የሚታወቀው ግን በንጹሕ አቋም ጠባቂነቱ ነው

ሀብትና ንብረት ማካበት እርካታና የአእምሮ ሰላም የማያስገኘው ለምንድን ነው?

ሀብት ምንም እርባና የማይኖረው መቼ ነው?

ከገንዘብና ከንብረት ጋር በተያያዘ ትልቁ አደጋ ምንድን ነው?

ሀብት የማታለል ኃይል ያለው እንዴት ነው?

ምሳሌ 11:4, 18, 28፤ 18:11፤ ማቴ 13:22

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 8:18-24—ስምዖን በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ መብቶችን በገንዘብ መግዛት እንደሚችል በሞኝነት አስቦ ነበር

የገንዘብ ፍቅር ምን ኪሳራ ሊያደርስብን ይችላል?

ማቴ 6:19-21፤ ሉቃስ 17:31, 32

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማር 10:17-23—አንድ ወጣት ባለጸጋ ለንብረቱ ያለው ፍቅር፣ ኢየሱስን መከተል የሚያስገኛቸውን መብቶች አሳጥቶታል

    • 1ጢሞ 6:17-19—ሐዋርያው ጳውሎስ ባለጸጋ ክርስቲያኖችን እንዳይታበዩ አስጠንቅቋል፤ ይህ ዓይነቱ ዝንባሌ የአምላክን ሞገስ ያሳጣቸዋል

ፍቅረ ንዋይ እምነት የሚያዳክመውና የአምላክን ሞገስ የሚያሳጣው እንዴት ነው?

ዘዳ 8:10-14፤ ምሳሌ 28:20፤ 1ዮሐ 2:15-17

በተጨማሪም መዝ 52:6, 7፤ አሞጽ 3:12, 15፤ 6:4-8⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኢዮብ 31:24, 25, 28—ኢዮብ በሀብት መታመን ያለውን አደጋ ተገንዝቧል፤ ይህን ማድረግ አምላክን ከመካድ እንደማይተናነስ ተናግሯል

    • ሉቃስ 12:15-21—ኢየሱስ፣ ሀብታም ሆኖም በአምላክ ዘንድ ባለጸጋ ስላልሆነ ሰው ምሳሌ በመናገር ፍቅረ ንዋይ ያለውን አደጋ አስጠንቅቋል

ከቁሳዊ ነገሮች ጋር በተያያዘ ባለን ረክተን መኖር የምንችለው እንዴት ነው?

ከቁሳዊ ንብረት የሚበልጡ ምን ውድ ነገሮች አሉ? የሚበልጡትስ ለምንድን ነው?

ምሳሌ 3:11, 13-18፤ 10:22፤ ማቴ 6:19-21

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሐጌ 1:3-11—ሕዝቡ የቤተ መቅደሱን ግንባታ ከማስቀደም ይልቅ የራሳቸውን ቤት በመገንባትና ኑሯቸውን በማደላደል በመጠመዳቸው ይሖዋ በቁሳዊ ነገሮችም ጭምር በረከቱን እንደሚነሳቸው በነቢዩ ሐጌ አማካኝነት ነግሯቸዋል

    • ራእይ 3:14-19—የሎዶቅያ ጉባኤ ክርስቲያኖች ለአምላክ ከሚያቀርቡት አገልግሎት ይልቅ ለሀብት ትልቅ ቦታ በመስጠታቸው ኢየሱስ ወቅሷቸዋል

ይሖዋ የሚያስፈልጉንን ቁሳዊ ነገሮች እንደሚያሟላልን መተማመን የምንችለው ለምንድን ነው?