2017 አጠቃላይ ድምር
የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ 90
ሪፖርቱ ውስጥ የተካተቱ አገሮች ብዛት፦ 240
አጠቃላይ ጉባኤዎች፦ 120,053
በዓለም ዙሪያ በመታሰቢያው በዓል ላይ የተገኙ፦ 20,175,477
በዓለም ዙሪያ በመታሰቢያው በዓል ላይ ከቂጣውና ከወይን ጠጁ የወሰዱ፦ 18,564
ከፍተኛ የአስፋፊዎች * ቁጥር፦ 8,457,107
የአስፋፊዎች አማካይ ቁጥር (በየወሩ)፦ 8,248,982
በ2016 ላይ ጭማሪ በመቶኛ፦ 1.4
አጠቃላይ ተጠማቂዎች *፦ 284,212
የዘወትር አቅኚዎች * አማካይ ቁጥር (በየወሩ)፦ 1,249,946
የረዳት አቅኚዎች አማካይ ቁጥር (በየወሩ)፦ 439,571
በአገልግሎት ያሳለፉት ጠቅላላ ሰዓት፦ 2,046,000,202
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች * አማካይ ቁጥር (በየወሩ)፦ 10,071,524
በ2017 የአገልግሎት ዓመት * ልዩ አቅኚዎች፣ ሚስዮናውያን እንዲሁም የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በተመደቡበት የአገልግሎት ክልል ሲያገለግሉ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ለመሸፈን የይሖዋ ምሥክሮች ከ202 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ አውጥተዋል። በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ የሚያገለግሉ 19,730 የተሾሙ የአምላክ አገልጋዮች አሉ። ሁሉም፣ የዓለም አቀፉ የይሖዋ ምሥክሮች የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሥርዓተ ማኅበር አባላት ናቸው።
^ አን.7 አስፋፊ የሚባለው የአምላክን መንግሥት ምሥራች በትጋት የሚያስፋፋ ወይም የሚሰብክ ክርስቲያን ነው። (ማቴዎስ 24:14) የአስፋፊዎች ቁጥር እንዴት እንደሚሰላ የተሟላ ማብራሪያ ለማግኘት jw.org/am ላይ የወጣውን “በዓለም ዙሪያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች አሉ?” የሚል ርዕስ ተመልከት።
^ አን.10 አንድ ሰው የይሖዋ ምሥክር ለመሆን ሊወስዳቸው ስለሚገቡት እርምጃዎች ተጨማሪ መረጃ ማብራሪያ ለማግኘት jw.org/am ላይ የወጣውን “የይሖዋ ምሥክር መሆን የምችለው እንዴት ነው?” የሚል ርዕስ ተመልከት።
^ አን.11 አቅኚ የሚባለው ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ በየወሩ የተወሰነ ሰዓት ለማሳለፍ ፈቃደኛ የሆነና ጥሩ አርዓያ ተደርጎ የሚታይ የተጠመቀ የይሖዋ ምሥክር ነው።
^ አን.14 ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት jw.org/am ላይ የወጣውን “መጽሐፍ ቅዱስን መማር ሲባል ምን ማለት ነው?” የሚል ርዕስ ተመልከት።
^ አን.15 የ2017 የአገልግሎት ዓመት ከመስከረም 1, 2016 እስከ ነሐሴ 31, 2017 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል።