ሆሴዕ 14:1-9

  • ወደ ይሖዋ ለመመለስ የቀረበ ልመና (1-3)

    • የከንፈር ውዳሴ ማቅረብ (2)

  • “ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ” (4-9)

14   “እስራኤል ሆይ፣ በበደልህ ስለተሰናከልክወደ አምላክህ ወደ ይሖዋ ተመለስ።+  2  ይህን ቃል ይዛችሁ ወደ ይሖዋ ተመለሱ፤እንዲህ በሉት፦ ‘በደላችንን ይቅር በለን፤+ መልካም የሆነውንም ነገር ተቀበለን፤እኛም ወይፈኖች እንደምናቀርብ፣ የከንፈራችንን ውዳሴ እናቀርብልሃለን።*+  3  አሦር አያድነንም።+ ፈረሶችን አንጋልብም፤+ከእንግዲህም ወዲህ የገዛ እጆቻችን የሠሩትን “አምላካችን ሆይ!” አንልም፤አባት የሌለው ልጅ ምሕረት ያገኘው በአንተ ነውና።’+  4  እኔም ከዳተኛነታቸውን እፈውሳለሁ።+ በገዛ ፈቃዴ እወዳቸዋለሁ፤+ምክንያቱም ቁጣዬ ከእሱ ተመልሷል።+  5  እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤እሱም እንደ አበባ ያብባል፤እንደ ሊባኖስ ዛፎችም ሥሮቹን ይሰዳል።  6  ቀንበጦቹ ይንሰራፋሉ፤ውበቱ እንደ ወይራ ዛፍ፣መዓዛውም እንደ ሊባኖስ ዛፍ ይሆናል።  7  እነሱም ዳግመኛ በጥላው ሥር ይኖራሉ። እህል ያበቅላሉ፤ እንደ ወይን ተክልም ያብባሉ።+ ዝናው* እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይሆናል።  8  ኤፍሬም ‘ከእንግዲህ ከጣዖቶች ጋር ምን ጉዳይ አለኝ?’ ይላል።+ መልስ እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም እጠብቀዋለሁ።+ እኔ እንደለመለመ የጥድ ዛፍ እሆናለሁ። ከእኔም ፍሬ ታገኛላችሁ።”  9  ጥበበኛ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ያስተውል። ልባም የሆነ ማን ነው? እነዚህን ነገሮች ይወቅ። የይሖዋ መንገዶች ቀና ናቸውና፤+ጻድቃንም በመንገዶቹ ላይ ይሄዳሉ፤በደለኞች ግን በእነሱ ይሰናከላሉ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “እኛም በምላሹ የከንፈሮቻችንን ወይፈኖች እናቀርባለን።”
ቃል በቃል “መታሰቢያው።”