ሆሴዕ 3:1-5
3 ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ሕዝብ ሌሎች አማልክትን የሚከተሉና+ የዘቢብ ቂጣ* የሚወዱ ሆነው ሳለ ይሖዋ እንደወደዳቸው ሁሉ፣+ አንተም ሄደህ በሌላ ሰው የተወደደችውንና ምንዝር የምትፈጽመውን ሴት ዳግመኛ ውደዳት።”+
2 በመሆኑም በ15 የብር ሰቅልና በአንድ ተኩል የሆሜር* መስፈሪያ ገብስ ለራሴ ገዛኋት።
3 ከዚያም እንዲህ አልኳት፦ “ለብዙ ቀናት የእኔ ሆነሽ ትቀመጫለሽ። አታመንዝሪ፤* ከሌላ ሰውም ጋር ግንኙነት አታድርጊ፤ እኔም ከአንቺ ጋር ግንኙነት አልፈጽምም።”
4 ምክንያቱም የእስራኤል ሕዝብ ለረጅም ጊዜ ያለንጉሥ፣+ ያለገዢ፣ ያለመሥዋዕት፣ ያለዓምድ፣ ያለኤፉድና+ ያለተራፊም ምስል*+ ይኖራሉ።
5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ተመልሰው አምላካቸውን ይሖዋንና ንጉሣቸውን ዳዊትን ይፈልጋሉ፤+ በዘመኑም መጨረሻ ወደ ይሖዋና ወደ ጥሩነቱ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ለሐሰት አምልኮ የሚጠቀሙበትን ቂጣ ያመለክታል።
^ ወይም “ነውር አትፈጽሚ (አትሴስኚ)።”
^ ወይም “የቤት ውስጥ አማልክት፤ ጣዖታት።”