ሆሴዕ 5:1-15
-
በኤፍሬምና በይሁዳ ላይ የተላለፈ ፍርድ (1-15)
5 “እናንተ ካህናት፣ ይህን ስሙ፤+እናንተ የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ በትኩረት አዳምጡ፤እናንተም የንጉሡ ቤት ሰዎች፣ አዳምጡ፤ፍርዱ እናንተንም ይጨምራልና፤ምክንያቱም ለምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም+ ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
2 ከትክክለኛው መንገድ የራቁት ሰዎች* ደም በማፍሰስ ወንጀል ተዘፍቀዋል፤*እኔም ለሁሉም ማስጠንቀቂያ እሰጣለሁ።*
3 ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረ አይደለም።
ኤፍሬም ሆይ፣ አሁን አንተ ሴሰኛ ሆነሃል፤*እስራኤል ራሱን አርክሷል።+
4 የሠሩት ሥራ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፤ምክንያቱም በመካከላቸው የአመንዝራነት* መንፈስ አለ፤+ለይሖዋም እውቅና አይሰጡም።
5 የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ* መሥክሮበታል፤+እስራኤልና ኤፍሬም የሠሩት በደል አሰናክሏቸዋል፤ይሁዳም ከእነሱ ጋር ተሰናክሏል።+
6 መንጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን ይዘው ይሖዋን ፍለጋ ሄዱ፤ሆኖም ሊያገኙት አልቻሉም።
እሱ ከእነሱ ርቋል።+
7 እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤+ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና።
አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን* ይውጣል።*
8 በጊብዓ ቀንደ መለከት፣ በራማም+ መለከት ንፉ!+
‘ቢንያም ሆይ፣ ከኋላህ ነን!’ ብላችሁ በቤትአዌን+ ቀረርቶ አሰሙ።
9 ኤፍሬም ሆይ፣ በምትቀጣበት ቀን መቀጣጫ ትሆናለህ።+
በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ምን እንደሚከሰት አሳውቄአለሁ።
10 የይሁዳ መኳንንት ወሰን እንደሚገፉ ሰዎች ናቸው።+
በእነሱ ላይ ቁጣዬን እንደ ውኃ አፈሳለሁ።
11 ኤፍሬም ተጨቁኗል፤ በፍርድ ተረግጧል፤ባላጋራውን ለመከተል ቆርጧልና።+
12 በመሆኑም እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳ ቤት ደግሞ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ።
13 ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቁስሉን ሲመለከትኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤+ ወደ ታላቅ ንጉሥም መልእክተኞች ላከ።
ይሁንና ንጉሡ እናንተን ሊፈውሳችሁ አልቻለም፤ቁስላችሁንም ሊያድን አልቻለም።
14 እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም ቤት እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና።
እኔ ራሴ ቦጫጭቄአቸው እሄዳለሁ፤+ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ የሚታደጋቸውም አይኖርም።+
15 እሄዳለሁ፤ በደላቸው የሚያስከትልባቸውን መዘዝ እስኪሸከሙም ድረስ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤በዚህ ጊዜም ሞገሴን* ይሻሉ።+
በጭንቀት በሚዋጡበት ጊዜ እኔን ይሻሉ።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ዓመፀኞቹ።”
^ ወይም “እጅግ ተጠላልፈዋል።”
^ ወይም “ሁሉንም እገሥጻለሁ።”
^ ወይም “እጅግ ነውረኛ ሆነሃል፤ አመንዝረሃል።”
^ ወይም “የነውረኝነት፤ የሴሰኝነት።”
^ ቃል በቃል “በፊቱ።”
^ “በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እነሱም ሆኑ ድርሻቸው ይዋጣሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “መሬታቸውን።”
^ ቃል በቃል “ፊቴን።”