ሆሴዕ 7:1-16

  • የኤፍሬም ክፋት ተገለጸ (1-16)

    • ከአምላክ መረብ ማምለጥ አይቻልም (12)

7  “እስራኤልን ለመፈወስ በሞከርኩ ቁጥርየኤፍሬም በደል፣+የሰማርያም ክፋት ይገለጣል።+ እነሱ ያታልላሉና፤+ሌቦች ሰብረው ይገባሉ፤ የወራሪዎች ቡድን በውጭ ጥቃት ይሰነዝራል።+   እነሱ ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ ልብ አይሉም።+ የገዛ ድርጊታቸው ከቧቸዋል፤የሠሩት ሥራ ሁሉ በፊቴ ነው።   ንጉሡን በክፋታቸው፣መኳንንቱንም አታላይ በሆነ ድርጊታቸው ያስደስታሉ።   ሁሉም አመንዝሮች ናቸው፤አንድ ዳቦ ጋጋሪ እሳቱን አንዴ ካቀጣጠለው በኋላ፣ያቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንደማያስፈልገው የጋለ ምድጃ ናቸው።   በንጉሣችን ክብረ በዓል ቀን፣ መኳንንቱ ታመሙ፤በወይን ጠጅ የተነሳ በቁጣ ተሞሉ።+ ንጉሡ ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።   እንደ ምድጃ የሚነድ ልብ ይዘው ይቀርባሉና።* ዳቦ ጋጋሪው ሌሊቱን ሙሉ ይተኛል፤በማለዳ ምድጃው እንደሚንበለበል እሳት ይንቀለቀላል።   ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዢዎቻቸውንም* ይውጣሉ። ነገሥታታቸው ሁሉ ወድቀዋል፤+ከእነሱ መካከል ወደ እኔ የሚጮኽ ማንም የለም።+   ኤፍሬም ከብሔራት ጋር ይቀላቀላል።+ እሱ እንዳልተገላበጠ ቂጣ ነው።   እንግዶች ጉልበቱን በዘበዙ፤+ እሱ ግን ይህን አላወቀም። ራሱንም ሽበት ወረሰው፤ እሱ ግን ይህን ልብ አላለም። 10  የእስራኤል ኩራት በራሱ ላይ መሥክሮበታል፤+ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ አምላካቸው ወደ ይሖዋ አልተመለሱም፤+እሱንም አልፈለጉትም። 11  ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላት* ሞኝ ርግብ ነው።+ ግብፅን ተጣሩ፤+ ወደ አሦርም ሄዱ።+ 12  የትም ቢሄዱ መረቤን በላያቸው እዘረጋለሁ። እንደ ሰማይ ወፎች ወደ ታች አወርዳቸዋለሁ። ለጉባኤያቸው በሰጠሁት ማስጠንቀቂያ መሠረት እገሥጻቸዋለሁ።+ 13  ከእኔ ስለሸሹ ወዮላቸው! በእኔ ላይ በደል ስለፈጸሙ ጥፋት ይምጣባቸው! እነሱን ለመዋጀት ዝግጁ ነበርኩ፤ እነሱ ግን በእኔ ላይ ውሸት ተናገሩ።+ 14  በአልጋቸው ላይ ሆነው ዋይ ዋይ ቢሉምእርዳታ ለማግኘት ከልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም።+ ለእህላቸውና ለአዲስ የወይን ጠጃቸው ሲሉ ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤በእኔም ላይ ዓመፁ። 15  ያሠለጠንኳቸውና ክንዳቸውን ያበረታሁ ቢሆንምክፉ ነገር በማሴር በእኔ ላይ ተነስተዋል። 16  አካሄዳቸውን ለወጡ፤ ከፍ ወዳለ ነገር ግን አይደለም፤*ጅማቱ እንደረገበ ደጋን እምነት የማይጣልባቸው ሆነዋል።+ አለቆቻቸው እብሪተኛ ከሆነው አንደበታቸው የተነሳ በሰይፍ ይወድቃሉ። በዚህም ምክንያት በግብፅ ምድር መሳለቂያ ይሆናሉ።”+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“ሴራ ጠንስሰው ሲቀርቡ ልባቸው እንደ ምድጃ ነውና” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ቃል በቃል “ፈራጆቻቸውንም።”
ቃል በቃል “ልብ እንደሌላት።”
ላቅ ያለ አምልኮ መከተል አለመጀመራቸውን ያሳያል።