ሆሴዕ 8:1-14
8 “ቀንደ መለከት ንፋ!+
ቃል ኪዳኔን ስላፈረሱና+ ሕጌን ስለጣሱ+በይሖዋ ቤት ላይ ጠላት እንደ ንስር ይመጣል።+
2 ‘አምላካችን ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች እናውቅሃለን!’ እያሉ ወደ እኔ ይጮኻሉ።+
3 እስራኤል መልካም የሆነውን ነገር ገሸሽ አድርጓል።+
ጠላት ያሳደው።
4 እኔ ሳልላቸው ነገሥታትን አነገሡ።
መኳንንትን ሾሙ፤ እኔ ግን እውቅና አልሰጠኋቸውም።
በገዛ ራሳቸው ላይ ጥፋት ለማምጣት+በብራቸውና በወርቃቸው ጣዖቶች ሠሩ።+
5 ሰማርያ ሆይ፣ የጥጃ ጣዖትሽ ተጥሏል።+
ቁጣዬ በእነሱ ላይ ይነዳል።+
ንጹሕ መሆን* የሚሳናቸው እስከ መቼ ነው?
6 ይህ ከእስራኤል ነውና።
የእጅ ጥበብ ባለሙያ የሠራው ይህ ጥጃ አምላክ አይደለም፤የሰማርያ ጥጃ ተሰባብሮ እንዳልነበረ ይሆናል።
7 ነፋስን ይዘራሉ፤አውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ።+
አገዳው፣ የደረሰ ፍሬ* የለውም፤+እህሉ፣ ዱቄት አላስገኘም።
ፍሬ ቢያፈራ እንኳ ባዕዳን* ይበሉታል።+
8 የእስራኤል ሰዎች ይዋጣሉ።+
በብሔራት መካከልማንም እንደማይፈልገው ዕቃ ይሆናሉ።+
9 ተገልሎ እንደሚኖር የዱር አህያ ወደ አሦር ሄደዋልና።+
ኤፍሬም በገንዘብ ፍቅረኞች አፍርቷል።+
10 ፍቅረኞቻቸውን ያፈሩት ከብሔራት ቢሆንም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤ንጉሥና መኳንንት በጫኑባቸው ሸክም የተነሳ ሥቃይ ይደርስባቸዋል።+
11 ኤፍሬም ኃጢአት ለመሥራት መሠዊያዎችን አብዝቷል።+
ኃጢአት የሚፈጽምባቸው መሠዊያዎች ሆነውለታል።+
12 በሕጌ* ውስጥ ያለውን አብዛኛውን ነገር ጽፌለታለሁ፤እነሱ ግን እንግዳ ነገር አድርገው ቆጠሩት።+
13 መሥዋዕቶችን ስጦታ አድርገው ለእኔ ያቀርባሉ፤ ሥጋውንም ይበላሉ፤ይሖዋ ግን በእነሱ አልተደሰተም።+
በደላቸውን ያስታውሳል፤ ለሠሯቸውም ኃጢአቶች ይቀጣቸዋል።+
እነሱ ወደ ግብፅ ተመልሰዋል።*+
14 እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል፤+ ቤተ መቅደሶችንም ገንብቷል፤+ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አብዝቷል።+
እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ራሳቸውን ማንጻት።”
^ ወይም “ዛላ።”
^ ወይም “እንግዶች።”
^ ወይም “በመመሪያዬ፤ በትምህርቴ።”
^ “ይመለሳሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።