ሆሴዕ 9:1-17

  • የኤፍሬም ኃጢአት በአምላክ ፊት ተቀባይነት አሳጣው (1-17)

    • ለአሳፋሪው አምላክ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ (10)

9  “እስራኤል ሆይ፣ ሐሴት አታድርግ፤+እንደ ሌሎቹ ሕዝቦች ደስ አይበልህ። ምንዝር በመፈጸም* ከአምላክህ ርቀሃልና።+ በየእህል አውድማ ላይ ለዝሙት አዳሪ የሚከፈለውን ደሞዝ ወደኸዋል።+   ሆኖም የእህል አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፤አዲሱም የወይን ጠጅ ይቋረጥባቸዋል።+   በይሖዋ ምድር ላይ አይኖሩም፤+ይልቁንም ኤፍሬም ወደ ግብፅ ይመለሳል፤በአሦርም የረከሰ ነገር ይበላሉ።+   ከእንግዲህ ለይሖዋ የወይን ጠጅ መባ አያፈሱም፤+መሥዋዕታቸውም አያስደስተውም።+ እንደ እዝን እንጀራ ናቸው፤የሚበሉትም ሁሉ ራሳቸውን ያረክሳሉ። ምግባቸው ለራሳቸው ብቻ* ነውና፤ወደ ይሖዋ ቤት አይገባም።   የምትሰበሰቡበትና* ለይሖዋ በዓል የምታከብሩበት ቀን ሲደርስምን ታደርጉ ይሆን?   እነሆ፣ ምድሪቱ በመውደሟ ለመሸሽ ይገደዳሉ።+ ግብፅ ትሰበስባቸዋለች፤+ ሜምፊስ ደግሞ ትቀብራቸዋለች።+ ከብር የተሠሩ ውድ ንብረቶቻቸውን ሳማ ይወርሰዋል፤በድንኳኖቻቸውም ውስጥ እሾሃማ ቁጥቋጦ ይበቅላል።   ምርመራ የሚካሄድበት ጊዜ ይመጣል፤+የበቀል ቀን ይመጣል፤እስራኤልም ይህን ይወቅ! የእነሱ ነቢይ ሞኝ፣ በመንፈስ የሚናገረውም ሰው እንደ እብድ ይሆናል፤ምክንያቱም በደልህ ብዙ ነው፤ በአንተም ላይ የሚደርሰው ጥላቻ በዝቷል።”   የኤፍሬም ጠባቂ+ ከአምላኬ ጋር ነበር።+ አሁን ግን የነቢያቱ+ መንገዶች ሁሉ እንደ ወፍ አዳኝ ወጥመዶች ናቸው፤በአምላኩ ቤት ጠላትነት አለ።   በጊብዓ ዘመን እንደነበረው፣ ጥፋት በሚያስከትሉ ነገሮች ተዘፍቀዋል።+ እሱ በደላቸውን ያስባል፤ በሠሩትም ኃጢአት የተነሳ ይቀጣቸዋል።+ 10  “እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ ወይን ሆኖ አገኘሁት።+ አባቶቻችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ባፈራ የበለስ ዛፍ ላይ እንደ ጎመራ የበለስ ፍሬ ሆነው አየኋቸው። ሆኖም ወደ ፌጎር ባአል ሄዱ፤+ለአሳፋሪውም ነገር* ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤+እንደወደዱትም ነገር አስጸያፊዎች ሆኑ። 11  የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይጠፋል፤መውለድ፣ ማርገዝም ሆነ መፀነስ የለም።+ 12  ልጆች ቢያሳድጉም እንኳአንድም ሰው እስከማይቀር ድረስ የወላድ መሃን አደርጋቸዋለሁ፤+አዎ፣ ከእነሱ በራቅኩ ጊዜ ወዮላቸው!+ 13  በግጦሽ ስፍራ የተተከለው ኤፍሬም ለእኔ እንደ ጢሮስ ነበር፤+አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለእርድ አሳልፎ ይሰጣል።” 14  ይሖዋ ሆይ፣ ልትሰጣቸው የሚገባውን ስጣቸው፤የሚጨነግፍ ማህፀንና የደረቁ* ጡቶች ስጣቸው። 15  “ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ በጊልጋል ፈጸሙ፤+ እኔም በዚያ ጠላኋቸው። በሠሩት ክፉ ድርጊት የተነሳ ከቤቴ አባርራቸዋለሁ።+ ከእንግዲህ ወዲያ ፍቅሬን እነፍጋቸዋለሁ፤+አለቆቻቸው ሁሉ እልኸኞች ናቸው። 16  ኤፍሬም ጉዳት ይደርስበታል።+ ሥራቸው ይደርቃል፤ አንዳችም ፍሬ አያፈሩም። ቢወልዱ እንኳ የሚወዷቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።” 17  እሱን ስላልሰሙት+አምላኬ ይተዋቸዋል፤በብሔራትም መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነውር በመፈጸም፤ ሴሰኛ በመሆን።”
ወይም “ለገዛ ነፍሳቸው።”
ወይም “የተወሰነው ክብረ በዓላችሁና።”
ወይም “ለአሳፋሪውም አምላክ።”
ወይም “የሟሸሹ።”