ሕዝቅኤል 15:1-8

  • ኢየሩሳሌም፣ የማትጠቅም የወይን ተክል (1-8)

15  የይሖዋ ቃል ዳግመኛ እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦  “የሰው ልጅ ሆይ፣ የወይን ተክል እንጨት በጫካ ዛፎች መካከል ካለ ከየትኛውም ዛፍ ወይም ቅርንጫፍ ከተወሰደ እንጨት ጋር እንዴት ሊወዳደር ይችላል?  ከወይን ተክል የሚገኝ ግንድ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል? ወይስ ሰዎች ግንዱን ተጠቅመው ዕቃ ለማንጠልጠል የሚያገለግል ኩላብ ይሠራሉ?  እነሆ፣ ማገዶ እንዲሆን እሳት ውስጥ ይጣላል፤ እሳቱ ጫፍና ጫፉን ይበላዋል፤ መሃሉንም ይለበልበዋል። ከዚህ በኋላ ሥራ ላይ ሊውል ይችላል?  ምንም ነገር ሳይነካውም እንኳ ለምንም ነገር ሊያገለግል አይችልም። እሳት ሲበላውና ሲለበልበውማ ጨርሶ ከጥቅም ውጭ ይሆናል!”  “ስለዚህ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ማገዶ እንዲሆን ለእሳት አሳልፌ እንደሰጠሁት በጫካ ዛፎች መካከል እንዳለ የወይን ተክል እንጨት ሁሉ፣ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።+  ፊቴን በእነሱ ላይ አድርጌአለሁ። ከእሳቱ ቢያመልጡም እሳት ይበላቸዋል። ፊቴንም በእነሱ ላይ በማደርግበት ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።’”+  “‘ታማኝ ሳይሆኑ በመቅረታቸውም+ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች