ሕዝቅኤል 2:1-10

  • ሕዝቅኤል የነቢይነት ተልእኮ ተሰጠው (1-10)

    • “ቢሰሙም ባይሰሙም” (5)

    • ሙሾ የተጻፈበት ጥቅልል አየ (9, 10)

2  ከዚያም “የሰው ልጅ* ሆይ፣ ተነስተህ በእግርህ ቁም፤ እኔም አናግርሃለሁ” አለኝ።+  እሱም ባናገረኝ ጊዜ መንፈስ ወደ ውስጤ ገባ፤ የሚያነጋግረኝንም እሰማ ዘንድ በእግሬ አቆመኝ።+  ከዚያም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ፣ በእኔ ላይ ወዳመፁት ወደ ዓመፀኞቹ ብሔራት+ እልክሃለሁ።+ እነሱም ሆኑ አባቶቻቸው እስከዚህች ቀን ድረስ ሕጌን ተላልፈዋል።+  ግትርና* ልበ ደንዳና+ ወደሆኑ ልጆች እልክሃለሁ፤ አንተም ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል’ በላቸው።  እነሱ ዓመፀኛ+ ቤት ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ በእርግጥ ያውቃሉ።+  “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ በአሜኬላና በእሾህ+ የተከበብክ* እንዲሁም በጊንጦች መካከል የምትኖር ቢሆንም እነሱንም ሆነ የሚናገሩትን ቃል አትፍራ።+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ስለሆኑ የሚናገሩትን አትፍራ፤+ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር።+  እነሱ ዓመፀኛ ስለሆኑ ቢሰሙም ባይሰሙም ቃሌን ንገራቸው።+  “አንተ ግን የሰው ልጅ ሆይ፣ የምነግርህን ስማ። እንደዚህ ዓመፀኛ ቤት፣ ዓመፀኛ አትሁን። አፍህን ክፈት፤ የምሰጥህንም ብላ።”+  እኔም ባየሁ ጊዜ ወደ እኔ የተዘረጋ እጅ+ ተመለከትኩ፤ ደግሞም የተጻፈበት ጥቅልል*+ አየሁ። 10  እሱም በፊቴ ጥቅልሉን ሲተረትረው፣ ከፊትና ከኋላ ተጽፎበት ነበር።+ በላዩ ላይ የሙሾ፣* የሐዘንና የዋይታ ቃላት ተጽፈውበት ነበር።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“የሰው ልጅ” የሚለው አገላለጽ በሕዝቅኤል መጽሐፍ ውስጥ 93 ጊዜ የሚገኝ ሲሆን ይህ የመጀመሪያው ነው።
ወይም “ፊታቸውን ወደማይመልሱና።”
“ሕዝቡ ልበ ደንዳኖችና እንደሚዋጉ ነገሮች ቢሆኑም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “የመጽሐፍ ጥቅልል።”
ወይም “የሐዘን እንጉርጉሮ።”