ሕዝቅኤል 45:1-25

  • መዋጮ ሆኖ የተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከተማዋ (1-6)

  • የአለቃው ድርሻ (7, 8)

  • አለቆቹ በሐቀኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል (9-12)

  • የሕዝቡ መዋጮና አለቃው (13-25)

45  “‘ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ በምትከፋፈሉበት ጊዜ+ ከምድሪቱ ላይ ቅዱስ የሆነ ድርሻ ለይሖዋ መዋጮ አድርጋችሁ ስጡ።+ ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣* ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ ይሁን።+ ስፍራው በሙሉ* ቅዱስ ድርሻ ይሆናል።  በዚህ ቦታ ውስጥ ለቅዱሱ ስፍራ የሚያገለግል 500 ክንድ በ500 ክንድ*+ የሆነ አራት ማዕዘን ቦታ ይኖራል፤ በሁሉም በኩል 50 ክንድ የሆነ የግጦሽ መሬት ይኖረዋል።+  ከተለካው መሬት ላይ ርዝመቱ 25,000፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 የሆነ ስፍራ ለካ፤ እጅግ ቅዱስ የሆነውም መቅደስ በዚያ ውስጥ ይሆናል።  ይሖዋን ለማገልገል ለሚቀርቡትና በመቅደሱ ለሚያገለግሉት ካህናት ቅዱስ ድርሻ ይሆናል።+ ለቤቶቻቸው እንዲሁም ለመቅደሱ የሚሆን ቅዱስ ስፍራ ይሆናል።  “‘በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉት ሌዋውያን ርዝመቱ 25,000 ክንድ፣ ወርዱ ደግሞ 10,000 ክንድ የሆነ ድርሻ ይኖራቸዋል፤+ እነሱም 20 የመመገቢያ ክፍሎችን*+ ርስት አድርገው ይወስዳሉ።  “‘እናንተም ለከተማዋ እንደ ርስት እንዲሆን ርዝመቱ 25,000 ክንድ (መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራ ትይዩ የሆነ) ወርዱ ደግሞ 5,000 ክንድ የሆነ ቦታ ትሰጣላችሁ።+ ይህም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል።  “‘አለቃው መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ለከተማዋ ከተሰጠው ቦታ ግራና ቀኝ መሬት ይኖረዋል። መሬቱ መዋጮ ሆኖ ከተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከከተማዋ ይዞታ አጠገብ ይሆናል። ደግሞም በስተ ምዕራብና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ይሆናል። ከምዕራቡ ወሰን እስከ ምሥራቁ ወሰን ድረስ ያለው ርዝመት ለአንዱ ነገድ ከተሰጠው ድርሻ ጋር ተመሳሳይ ነው።+  ይህ መሬት በእስራኤል ምድር የእሱ ርስት ይሆናል። ከእንግዲህ አለቆቼ በሕዝቤ ላይ ግፍ አይፈጽሙም፤+ ምድሪቱንም ለእስራኤል ቤት ሰዎች በየነገዳቸው ይሰጧቸዋል።’+  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ የእስራኤል አለቆች፣ በጣም አብዝታችሁታል!’ “‘ግፍና ጭቆና መፈጸማችሁን አቁሙ፤ ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ።+ የሕዝቤን ንብረት መቀማታችሁን ተዉ’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 10  ‘ትክክለኛ ሚዛን፣ ትክክለኛ የኢፍ መስፈሪያና* ትክክለኛ የባዶስ መስፈሪያ* ተጠቀሙ።+ 11  ለኢፍ መስፈሪያና ለባዶስ መስፈሪያ ቋሚ የሆነ መመዘኛ መኖር አለበት። የባዶስ መስፈሪያው አንድ አሥረኛ ሆሜር* የሚይዝ ይሁን፤ የኢፍ መስፈሪያውም አንድ አሥረኛ ሆሜር የሚይዝ ይሁን። ሆሜር መደበኛ መመዘኛ ይሆናል። 12  አንድ ሰቅል*+ 20 ጌራ* ይሁን። ደግሞም 20 ሰቅል፣ 25 ሰቅልና 15 ሰቅል አንድ ላይ ሲደመር አንድ ማኔህ* ይሁንላችሁ።’ 13  “‘የምትሰጡት መዋጮ ይህ ነው፦ ከእያንዳንዱ ሆሜር ስንዴ የኢፍ አንድ ስድስተኛ፣ ከእያንዳንዱ ሆሜር ገብስ ደግሞ የኢፍ አንድ ስድስተኛ መዋጮ ታደርጋላችሁ። 14  የሚሰጠው ዘይት የሚለካው በባዶስ መስፈሪያ ይሆናል። አንድ ባዶስ፣ የቆሮስ* አንድ አሥረኛ ነው፤ አሥር ባዶስ ደግሞ አንድ ሆሜር ነው፤ አሥር ባዶስ ከአንድ ሆሜር ጋር እኩል ነውና። 15  ደግሞም ከእስራኤል መንጎች መካከል ከየሁለት መቶው አንድ በግ ስጡ። እነዚህ ስጦታዎች ለሕዝቡ ማስተሰረያ እንዲሆኑ+ ለእህል መባ፣+ ሙሉ በሙሉ ለሚቃጠል መባና+ ለኅብረት መሥዋዕት+ ይውላሉ’ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ። 16  “‘የምድሪቱ ነዋሪ ሁሉ ይህን መዋጮ ለእስራኤል አለቃ ይሰጣል።+ 17  አለቃውም በበዓላት፣ አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ወቅት፣ በየሰንበቱና+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች በተወሰኑት በዓላት ወቅት ሁሉ+ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባ፣+ የእህሉን መባና+ የመጠጡን መባ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት።+ ለእስራኤል ቤት ሰዎች ማስተሰረያ እንዲሆን የኃጢአት መባ፣ የእህል መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት የሚያቀርበው እሱ ነው።’ 18  “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ከከብቶቹ መካከል ምንም እንከን የሌለበት አንድ ወይፈን ወስደህ መቅደሱን ከኃጢአት አንጻው።+ 19  ካህኑ የኃጢአት መባ ሆኖ ከቀረበው ደም የተወሰነውን ወስዶ በቤተ መቅደሱ መቃን፣+ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን አራት ማዕዘኖችና በውስጠኛው ግቢ በር መቃን ላይ ያድርግ። 20  አንድ ሰው በስህተትና ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ+ ከወሩ በሰባተኛው ቀን እንዲሁ አድርግ፤ እናንተም ለቤተ መቅደሱ ማስተሰረያ ታቀርባላችሁ።+ 21  “‘በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በ14ኛው ቀን የፋሲካን በዓል ታከብራላችሁ።+ ለሰባት ቀን ቂጣ* ትበላላችሁ።+ 22  በዚያም ቀን አለቃው ለራሱና ለምድሩ ነዋሪ ሁሉ የኃጢአት መባ እንዲሆን አንድ ወይፈን ያቀርባል።+ 23  በዓሉ በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀናት፣ በእያንዳንዱ ቀን፣ እንከን የሌለባቸውን ሰባት ወይፈኖችና እንከን የሌለባቸውን ሰባት አውራ በጎች ለይሖዋ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ አድርጎ ያቀርባል፤+ ደግሞም ለኃጢአት መባ በየዕለቱ አንድ አውራ ፍየል ያቀርባል። 24  በተጨማሪም ለእያንዳንዱ ወይፈን አንድ ኢፍ፣ ለእያንዳንዱም አውራ በግ አንድ ኢፍ የእህል መባ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ኢፍ አንድ ሂን* ዘይት ያቅርብ። 25  “‘በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በ15ኛው ቀን፣ በበዓሉ ወቅት ለሰባት ቀናት+ ይህንኑ የኃጢአት መባ፣ ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባ፣ የእህል መባና ዘይት ያቅርብ።’”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በወሰኑ ውስጥ ያለው በሙሉ።”
ይህ ረጅም ክንድ የሚባለውን መለኪያ ያመለክታል። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ቃል በቃል “500 በ500።”
ወይም “20 ክፍሎችን።”
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ምናን።” ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።
ለ14ን ተመልከት።