መዝሙር 103:1-22

  • “ይሖዋን ላወድስ”

    • አምላክ በደላችንን ከእኛ አራቀ (12)

    • የአምላክ አባታዊ ምሕረት (13)

    • አምላክ አፈር መሆናችንን ያስታውሳል (14)

    • የይሖዋ ዙፋንና ንግሥና (19)

    • መላእክት የአምላክን ቃል ይፈጽማሉ (20)

የዳዊት መዝሙር። 103  ይሖዋን ላወድስ፤*ሁለንተናዬ ቅዱስ ስሙን ያወድስ።  2  ይሖዋን ላወድስ፤*ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ፈጽሞ አልርሳ።+  3  እሱ በደልሽን ሁሉ ይቅር ይላል፤+ሕመምሽንም ሁሉ ይፈውሳል፤+  4  ሕይወትሽን ከጉድጓድ* ያወጣል፤+ታማኝ ፍቅሩንና ምሕረቱን ያጎናጽፍሻል፤+  5  የወጣትነት ዕድሜሽ እንደ ንስር እንዲታደስ፣+በሕይወት ዘመንሽ ሁሉ መልካም ነገሮች ያጠግብሻል።+  6  ይሖዋ ለተጨቆኑ ሁሉበጽድቅና በፍትሕ እርምጃ ይወስዳል።+  7  መንገዶቹን ለሙሴ፣ያከናወናቸውንም ነገሮች ለእስራኤል ልጆች አሳወቀ።+  8  ይሖዋ መሐሪና ሩኅሩኅ፣*+ለቁጣ የዘገየ እንዲሁም ታማኝ ፍቅሩ* የበዛ ነው።+  9  እሱ ሁልጊዜ ስህተት አይፈላልግም፤+ለዘላለምም ቂም አይዝም።+ 10  እንደ ኃጢአታችን አላደረገብንም፤+ለበደላችን የሚገባውንም ብድራት አልከፈለንም።+ 11  ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣እሱ ለሚፈሩት የሚያሳየው ታማኝ ፍቅር ታላቅ ነውና።+ 12  ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፣በደላችንን ከእኛ አራቀ።+ 13  አባት ለልጆቹ ምሕረት እንደሚያሳይ፣ይሖዋም ለሚፈሩት ምሕረት አሳይቷል።+ 14  እሱ እንዴት እንደተሠራን በሚገባ ያውቃልና፤+አፈር መሆናችንን ያስታውሳል።+ 15  ሟች የሆነ የሰው ልጅ የሕይወት ዘመኑ እንደ ሣር ነው፤+እንደ ሜዳ አበባ ያብባል።+ 16  ይሁንና ነፋስ ሲነፍስበት ደብዛው ይጠፋል፤በዚያ ስፍራ ያልነበረ ያህል ይሆናል።* 17  ይሖዋ ግን እሱን ለሚፈሩትታማኝ ፍቅሩን ከዘላለም እስከ ዘላለም ያሳያል፤+ጽድቁንም ለልጅ ልጆቻቸው ይገልጣል፤+ 18  ይህን የሚያደርገው ቃል ኪዳኑን ለሚጠብቁ፣+መመሪያዎቹን ለመፈጸም ለሚተጉ ነው። 19  ይሖዋ ዙፋኑን በሰማያት አጽንቶ መሥርቷል፤+በሁሉም ላይ ንጉሥ ሆኖ ይገዛል።+ 20  ትእዛዛቱን በማክበር ቃሉን የምትፈጽሙ፣*+እናንተ ብርቱዎችና ኃያላን መላእክቱ ሁሉ፣+ ይሖዋን አወድሱ። 21  ፈቃዱን የምታደርጉ አገልጋዮቹ፣+ሠራዊቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ።+ 22  በግዛቱ* ሁሉ ያላችሁ፣ፍጥረታቱ ሁሉ፣ ይሖዋን አወድሱ። ሁለንተናዬ ይሖዋን ያወድስ።*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”
ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”
ወይም “ከመቃብር።”
ወይም “ቸር።”
ወይም “ፍቅራዊ ደግነቱ።”
ቃል በቃል “ቦታውም ከዚያ በኋላ አያውቀውም።”
ቃል በቃል “የቃሉን ድምፅ የምትሰሙ።”
ወይም “ሉዓላዊነቱ በሰፈነበት ቦታ።”
ወይም “ነፍሴ ይሖዋን ታወድስ።”