መዝሙር 111:1-10
111 ያህን አወድሱ!*+
א [አሌፍ]
ቅኖች በተሰበሰቡበት ማኅበርና በጉባኤב [ቤት]
ይሖዋን በሙሉ ልቤ አወድሰዋለሁ።+
ג [ጊሜል]
2 የይሖዋ ሥራ ታላቅ ነው፤+ד [ዳሌት]
በሥራው የሚደሰቱ ሰዎች ሁሉ ያጠኑታል።+
ה [ሄ]
3 ሥራው ግርማና ውበት የተላበሰ ነው፤ו [ዋው]
ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+
ז [ዛየን]
4 አስደናቂ ሥራዎቹ እንዲታወሱ ያደርጋል።+
ח [ኼት]
ይሖዋ ሩኅሩኅና* መሐሪ ነው።+
ט [ቴት]
5 ለሚፈሩት ምግብ ይሰጣል።+
י [ዮድ]
ቃል ኪዳኑን ለዘላለም ያስታውሳል።+
כ [ካፍ]
6 የብሔራትን ርስት በመስጠት፣+ל [ላሜድ]
ኃያል ሥራዎቹን ለሕዝቡ ገልጧል።
ס [ሜም]
7 የእጆቹ ሥራዎች እውነትና ፍትሕ ናቸው፤+נ [ኑን]
መመሪያዎቹ ሁሉ እምነት የሚጣልባቸው ናቸው።+
ס [ሳሜኽ]
8 አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ* ናቸው፤ע [አይን]
በእውነትና በጽድቅ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።+
פ [ፔ]
9 ሕዝቡን ዋጀ።+
צ [ጻዴ]
ቃል ኪዳኑ ለዘላለም እንዲጸና አዘዘ።
ק [ኮፍ]
ስሙ ቅዱስና እጅግ የሚፈራ ነው።+
ר [ረሽ]
10 ይሖዋን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው።+
ש [ሺን]
መመሪያዎቹን የሚጠብቁ* ሁሉ ጥሩ ማስተዋል አላቸው።+
ת [ታው]
ውዳሴው ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
^ ወይም “ቸርና።”
^ ወይም “ጽኑ መሠረት ያላቸው።”
^ ቃል በቃል “እነሱን የሚጠብቁ።”