መዝሙር 13:1-6
ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የዳዊት ማህሌት።
13 ይሖዋ ሆይ፣ የምትረሳኝ እስከ መቼ ነው? ለዘላለም?
ፊትህን ከእኔ የምትሰውረው እስከ መቼ ነው?+
2 ልቤ በየዕለቱ በሐዘን እየተደቆሰ፣በጭንቀት ተውጬ የምኖረው* እስከ መቼ ነው?
ጠላቴ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ነው?+
3 ይሖዋ አምላኬ ሆይ፣ ወደ እኔ ተመልከት፤ መልስም ስጠኝ።
በሞት እንዳላንቀላፋ ዓይኖቼን አብራልኝ፤
4 እንዲህ ከሆነ ጠላቴ “አሸነፍኩት!” አይልም፤
ባላጋራዎቼ በእኔ ውድቀት ሐሴት እንዲያደርጉ አትፍቀድ።+
5 እኔ በበኩሌ በታማኝ ፍቅርህ እታመናለሁ፤+ልቤ በማዳን ሥራህ ሐሴት ያደርጋል።+
6 በእጅጉ ስለካሰኝ+ ለይሖዋ እዘምራለሁ።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ነፍሴ በጭንቀት ተውጣ የምትኖረው።”