መዝሙር 147:1-20

  • አምላክን ድንቅ ለሆኑት ሥራዎቹ ማወደስ

    • የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይፈውሳል (3)

    • ከዋክብትን ሁሉ በስማቸው ይጠራቸዋል (4)

    • በረዶን እንደ ሱፍ ይልካል (16)

147  ያህን አወድሱ!* ለአምላካችን የውዳሴ መዝሙር መዘመር ጥሩ ነው፤እሱን ማወደስ ደስ ያሰኛል፤ ደግሞም ተገቢ ነው።+  2  ይሖዋ ኢየሩሳሌምን ይገነባል፤+የተበተኑትን የእስራኤል ነዋሪዎች ይሰበስባል።+  3  የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል፤ቁስላቸውን ይፈውሳል።  4  የከዋክብትን ብዛት ይቆጥራል፤ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።+  5  ጌታችን ታላቅ ነው፤ ደግሞም እጅግ ኃያል ነው፤+ማስተዋሉም ወሰን የለውም።+  6  ይሖዋ የዋሆችን ያነሳል፤+ክፉዎችን ግን መሬት ላይ ይጥላል።  7  ለይሖዋ በምስጋና ዘምሩ፤ለአምላካችን በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤  8  እሱ ሰማያትን በደመናት ይሸፍናል፤ለምድር ዝናብ ይሰጣል፤+በተራሮች ላይ ሣር እንዲበቅል ያደርጋል።+  9  ለእንስሳት እንዲሁም የሚበሉትን ለማግኘት ለሚጮኹ የቁራ ጫጩቶችምግብ ይሰጣል።+ 10  በፈረስ ጉልበት አይደሰትም፤+የሰው እግር ጥንካሬም አያስደንቀውም።+ 11  ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እሱን በሚፈሩ፣ታማኝ ፍቅሩን በሚጠባበቁ ሰዎች ይደሰታል።+ 12  ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ይሖዋን ከፍ ከፍ አድርጊ። ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽን አወድሺ። 13  እሱ የከተማሽን በሮች መወርወሪያዎች ያጠናክራል፤በውስጥሽ ያሉትን ወንዶች ልጆች ይባርካል። 14  በክልልሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤+ምርጥ በሆነ ስንዴ* ያጠግብሻል።+ 15  ትእዛዙን ወደ ምድር ይልካል፤ቃሉም በፍጥነት ይሮጣል። 16  በረዶን እንደ ሱፍ ይልካል፤+አመዳዩን እንደ አመድ ይበትናል።+ 17  የበረዶውን ድንጋይ እንደ ዳቦ ፍርፋሪ ይወረውራል።+ እሱ የሚልከውን ቅዝቃዜ ማን ሊቋቋም ይችላል?+ 18  ቃሉን ይልካል፤ እነሱም ይቀልጣሉ። ነፋሱ እንዲነፍስ ያደርጋል፤+ ውኃውም ይፈስሳል። 19  ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዓቱንና ፍርዶቹን ለእስራኤል ያስታውቃል።+ 20  ይህን ለሌላ ለማንም ብሔር አላደረገም፤+እነሱ ስለ ፍርዶቹ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። ያህን አወድሱ!*+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ቃል በቃል “በስንዴ ስብ።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።