መዝሙር 24:1-10
-
ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ
-
‘ምድር የይሖዋ ናት’ (1)
-
የዳዊት መዝሙር። ማህሌት።
24 ምድርና በውስጧ ያለው ነገር ሁሉ፣ፍሬያማ የሆነችው ምድርና በእሷ ላይ የሚኖር ሁሉ የይሖዋ ነው።+
2 እሱ በባሕሮች ላይ መሥርቷታልና፤+በወንዞችም ላይ አጽንቶ አስቀምጧታል።
3 ወደ ይሖዋ ተራራ መውጣት የሚችል ማን ነው?+በቅዱስ ስፍራውስ ሊቆም የሚችል ማን ነው?
4 ከክፋት የጸዱ እጆችና ንጹሕ ልብ ያለው፣+በእኔ ሕይወት* በሐሰት ያልማለ፣በማታለልም መሐላ ያልፈጸመ።+
5 እሱ በረከትን ከይሖዋ ያገኛል፤+ጽድቅንም* አዳኝ ከሆነው አምላኩ ይቀበላል።+
6 እሱን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ ይህ ነው፤የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ፊትህን የሚፈልጉ ሰዎች ትውልድ እንዲህ ያለ ነው። (ሴላ)
7 እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ!*+
8 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው?
ብርቱና ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው፤+በውጊያ ኃያል የሆነው ይሖዋ ነው።+
9 እናንተ ደጆች፣ ራሳችሁን ቀና አድርጉ፤+እናንተ ጥንታዊ በሮች፣ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ ይገባ ዘንድ ተከፈቱ!
10 ይህ ክብር የተጎናጸፈ ንጉሥ ማን ነው?
የሠራዊት አምላክ ይሖዋ ነው፤ ክብር የተጎናጸፈው ንጉሥ እሱ ነው።+ (ሴላ)