መዝሙር 25:1-22
የዳዊት መዝሙር።
א [አሌፍ]
25 ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እማጸናለሁ።*
ב [ቤት]
2 አምላኬ ሆይ፣ በአንተ እታመናለሁ፤+ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።+
ጠላቶቼ በደረሰብኝ መከራ አይፈንድቁ።+
ג [ጊሜል]
3 አንተን ተስፋ የሚያደርግ ሁሉ በፍጹም አያፍርም፤+ያላንዳች ምክንያት ክህደት የሚፈጽሙ ግን ለኀፍረት ይዳረጋሉ።+
ד [ዳሌት]
4 ይሖዋ ሆይ፣ መንገድህን አሳውቀኝ፤+ጎዳናህንም አስተምረኝ።+
ה [ሄ]
5 አንተ አዳኝ አምላኬ ስለሆንክበእውነትህ እንድመላለስ አድርገኝ፤ አስተምረኝም።+
ז [ዋው]
ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አደርጋለሁ።
ז [ዛየን]
6 ይሖዋ ሆይ፣ ምንጊዜም ታሳያቸው የነበሩትን*+ምሕረትህንና ታማኝ ፍቅርህን አስታውስ።+
ח [ኼት]
7 በወጣትነቴ የሠራኋቸውን ኃጢአቶችና በደሎች አታስብብኝ።
ይሖዋ ሆይ፣ ለጥሩነትህ ስትል+እንደ ታማኝ ፍቅርህ መጠን አስበኝ።+
ט [ቴት]
8 ይሖዋ ጥሩና ቀና ነው።+
ኃጢአተኞችን ሊኖሩበት የሚገባውን መንገድ የሚያስተምራቸው ለዚህ ነው።+
י [ዮድ]
9 የዋሆችን በትክክለኛ መንገድ* ይመራቸዋል፤+እንዲሁም ለየዋሆች መንገዱን ያስተምራል።+
כ [ካፍ]
10 የይሖዋ መንገዶች ሁሉ፣ ቃል ኪዳኑንና+ ማሳሰቢያዎቹን+ ለሚጠብቁ፣ታማኝ ፍቅር የሚንጸባረቅባቸውና እምነት የሚጣልባቸው ናቸው።
ל [ላሜድ]
11 ይሖዋ ሆይ፣ ኃጢአቴ ታላቅ ቢሆንም እንኳለስምህ ስትል ይቅር በለኝ።+
מ [ሜም]
12 ይሖዋን የሚፈራ ሰው ማን ነው?+
መምረጥ ስላለበት መንገድ ያስተምረዋል።+
נ [ኑን]
13 እሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ያገኛል፤*+ዘሮቹም ምድርን ይወርሳሉ።+
ס [ሳሜኽ]
14 ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት የሚኖራቸው እሱን የሚፈሩ ሰዎች ናቸው፤+ቃል ኪዳኑንም ያሳውቃቸዋል።+
ע [አይን]
15 ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ይሖዋ ያያሉ፤+እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና።+
פ [ፔ]
16 ብቸኛና ምስኪን ስለሆንኩፊትህን ወደ እኔ መልስ፤ ቸርነትም አሳየኝ።
צ [ጻዴ]
17 የልቤ ጭንቀት በዝቷል፤+ከሥቃዬ ገላግለኝ።
ר [ረሽ]
18 ጉስቁልናዬንና መከራዬን ተመልከት፤+ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በል።+
19 ጠላቶቼ ምን ያህል ብዙ እንደሆኑ ተመልከት፤ምን ያህል አምርረው እንደሚጠሉኝም እይ።
ש [ሺን]
20 ሕይወቴን* ጠብቅ፤ አድነኝም።+
አንተን መጠጊያ ስላደረግኩ ለኀፍረት እንድዳረግ አትፍቀድ።
ת [ታው]
21 ንጹሕ አቋሜና* ቅንነቴ ይጠብቁኝ፤+አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና።+
22 አምላክ ሆይ፣ እስራኤልን ከጭንቀቱ ሁሉ ታደገው።*
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ነፍሴን ወደ አንተ አነሳለሁ።”
^ ወይም “ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበሩትን።”
^ ቃል በቃል “በፍርድ።”
^ ወይም “ነፍሱ ጥሩ የሆነውን ነገር ታገኛለች።”
^ ወይም “ነፍሴን።”
^ ቃል በቃል “ዋጀው።”