መዝሙር 92:1-15
በሰንበት ቀን የሚዘመር መዝሙር። ማህሌት።
92 ለይሖዋ ምስጋና ማቅረብ ጥሩ ነው፤+ልዑሉ አምላክ ሆይ፣ ለስምህም የውዳሴ መዝሙር መዘመር መልካም ነው፤
2 ታማኝ ፍቅርህን በማለዳ፣ታማኝነትህንም በሌሊት ማሳወቅ+ መልካም ነው፤
3 አሥር አውታር ባለው መሣሪያና በክራር፣ደስ በሚል የበገና ድምፅ+ ታጅቦ ማሳወቅ ጥሩ ነው።
4 ይሖዋ ሆይ፣ ባከናወንካቸው ነገሮች እንድደሰት አድርገኸኛልና፤ከእጅህ ሥራዎች የተነሳ እልል እላለሁ።
5 ይሖዋ ሆይ፣ ሥራህ ምንኛ ታላቅ ነው!+
ሐሳብህም እንዴት ጥልቅ ነው!+
6 ማመዛዘን የጎደለው ሰው ይህን ሊያውቅ አይችልም፤ሞኝ የሆነም ሰው ይህን ሊረዳ አይችልም፦+
7 ክፉዎች እንደ አረም* ቢበቅሉ፣ክፉ አድራጊዎች ሁሉ ቢያብቡ እንኳ፣ለዘላለም መጥፋታቸው የማይቀር ነው።+
8 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም ከሁሉ በላይ ነህ።
9 ይሖዋ ሆይ፣ ጠላቶችህን በድል አድራጊነት ስሜት ተመልከት፤ጠላቶችህ እንዴት እንደሚጠፉ እይ፤ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ይበተናሉ።+
10 አንተ ግን ኃይሌን* እንደ ዱር በሬ ኃይል ታደርጋለህ፤እኔም ገላዬን ጥሩ ዘይት እቀባለሁ።+
11 ዓይኔ ጠላቶቼን በድል አድራጊነት ስሜት ያያል፤+ጆሮዬም የሚያጠቁኝን ክፉ ሰዎች ውድቀት ይሰማል።
12 ጻድቅ ግን እንደ ዘንባባ ዛፍ ይለመልማል፤እንደ አርዘ ሊባኖስም ትልቅ ይሆናል።+
13 በይሖዋ ቤት ተተክለዋል፤በአምላካችን ቅጥር ግቢዎች ያብባሉ።+
14 ባረጁ* ጊዜም እንኳ ማበባቸውን ይቀጥላሉ፤+እንደበረቱና* እንደጠነከሩ ይኖራሉ፤+
15 ይሖዋ ትክክለኛ እንደሆነ እያወጁ ይኖራሉ።
እሱ ዓለቴ ነው፤+ በእሱም ዘንድ ክፋት የለም።