ምሳሌ 1:1-33
1 የእስራኤል ንጉሥ፣+ የዳዊት ልጅ+ የሰለሞን ምሳሌዎች፦+
2 ጥበብንና+ ተግሣጽን ለመማር፣*ጥበብ ያዘሉ አባባሎችን ለመረዳት፣
3 ጥልቅ ማስተዋል፣ ጽድቅ፣+ ጥሩ ፍርድና*+ቅንነት* የሚያስገኝ ተግሣጽ ለመቀበል፣+
4 ተሞክሮ ለሌላቸው ብልሃትን፣+ለወጣቶች እውቀትንና የማመዛዘን ችሎታን ለመስጠት።+
5 ጥበበኛ ሰው ያዳምጣል፤ ደግሞም ተጨማሪ ትምህርት ይቀስማል፤+ማስተዋል ያለው ሰውም ጥበብ ያለበትን መመሪያ ይቀበላል፤+
6 ይህም ምሳሌንና ስውር የሆነ አባባልንእንዲሁም የጥበበኞችን ቃላትና የሚናገሩትን እንቆቅልሽ ይረዳ ዘንድ ነው።+
7 ይሖዋን መፍራት* የእውቀት መጀመሪያ ነው።+
ጥበብንና ተግሣጽን የሚንቁት ሞኞች ብቻ ናቸው።+
8 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ተግሣጽ አዳምጥ፤+የእናትህንም መመሪያ* አትተው።+
9 ለራስህ የሚያምር የአበባ ጉንጉን፣+ለአንገትህም ውብ ጌጥ ይሆንልሃል።+
10 ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች ሊያግባቡህ ቢሞክሩ እሺ አትበላቸው።+
11 እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ና አብረን እንሂድ።
ደም ለማፍሰስ እናድባ።
ንጹሐን ሰዎችን ያለምክንያት ለማጥቃት እናደፍጣለን።
12 እንደ መቃብር፣* በሕይወት እንዳሉ እንውጣቸዋለን፤ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንሰለቅጣቸዋለን።
13 ውድ ሀብታቸውን ሁሉ እንውሰድባቸው፤ቤቶቻችንን በዘረፍናቸው ነገሮች እንሞላለን።
14 ከእኛ ጋር ልትተባበር ይገባል፤*ሁላችንም የሰረቅነውን እኩል እንካፈላለን።”*
15 ልጄ ሆይ፣ አትከተላቸው።
እግርህን ከመንገዳቸው አርቅ፤+
16 እግሮቻቸው ክፉ ነገር ለመሥራት ይሮጣሉና፤ደም ለማፍሰስ ይጣደፋሉ።+
17 ወፎች ዓይናቸው እያየ እነሱን ለማጥመድ መረብ መዘርጋት ከንቱ ነው።
18 እነዚህ ሰዎች ደም ለማፍሰስ የሚያደቡት ለዚህ ነው፤የሰዎችን ሕይወት* ለማጥፋት ያደፍጣሉ።
19 በማጭበርበር ትርፍ ለማግኘት የሚሹ መንገዳቸው ይህ ነው፤እንዲህ ያለው ትርፍ የተጠቃሚዎቹን ሕይወት* ያጠፋል።+
20 እውነተኛ ጥበብ+ በጎዳና ላይ ትጮኻለች።+
በአደባባይ ላይ ያለማቋረጥ ድምፅዋን ታሰማለች።+
21 ሰው በሚበዛባቸው ጎዳናዎች ማዕዘን* ላይ ሆና ትጣራለች።
በከተማው መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ ትላለች፦+
22 “እናንተ አላዋቂዎች እስከ መቼ አላዋቂነትን ትወዳላችሁ?
እናንተ ፌዘኞች እስከ መቼ በሌሎች ላይ በማፌዝ ትደሰታላችሁ?
እናንተ ሞኞች እስከ መቼ እውቀትን ትጠላላችሁ?+
23 ለወቀሳዬ ምላሽ ስጡ።*+
እንዲህ ብታደርጉ መንፈሴን አፈስላችኋለሁ፤ቃሌን አሳውቃችኋለሁ።+
24 በተጣራሁ ጊዜ በእንቢተኝነታችሁ ጸንታችኋል፤እጄን በዘረጋሁ ጊዜ ማንም ትኩረት አልሰጠም፤+
25 ምክሬን ሁሉ ችላ ብላችኋል፤ወቀሳዬንም አልተቀበላችሁም፤
26 እኔም ጥፋት ሲደርስባችሁ እስቃለሁ፤የፈራችሁት ነገር ሲደርስ አላግጥባችኋለሁ፤+
27 የፈራችሁት ነገር እንደ ማዕበል ሲደርስባችሁ፣ጥፋታችሁም እንደ አውሎ ነፋስ ከተፍ ሲልባችሁ፣ጭንቀትና መከራ ሲመጣባችሁ አፌዝባችኋለሁ።
28 በዚያን ጊዜ ደጋግመው ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ሆኖም አያገኙኝም፤+
29 ምክንያቱም እውቀትን ጠልተዋል፤+ይሖዋን መፍራትንም አልወደዱም።+
30 ምክሬን አልተቀበሉም፤ወቀሳዬን ሁሉ አቃለዋል።
31 ስለዚህ መንገዳቸው የሚያስከትለውን መዘዝ ይቀበላሉ፤*+በገዛ ራሳቸውም ምክር* ከልክ በላይ ይጠግባሉ።
32 ተሞክሮ የሌላቸውን ሰዎች ጋጠወጥነታቸው ይገድላቸዋልና፤ሞኞችን ደግሞ ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል።
33 እኔን የሚሰማ ሰው ግን ተረጋግቶ ይኖራል፤+መከራ ይደርስብኛል የሚል ስጋትም አያድርበትም።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “ለማወቅ።”
^ ወይም “ፍትሕና።”
^ ወይም “ሚዛናዊነት።”
^ ወይም “በጥልቅ ማክበር።”
^ ወይም “ሕግ፤ ትምህርት።”
^ ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል።”
^ ወይም “አንድ የጋራ ከረጢት (ቦርሳ) ይኖረናል።”
^ ወይም “ነፍስ።”
^ ወይም “ነፍስ።”
^ ቃል በቃል “ራስ።”
^ ወይም “ስወቅሳችሁ ተመለሱ።”
^ ቃል በቃል “የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ።”
^ ወይም “ውጥን፤ ዕቅድ።”