ምሳሌ 19:1-29
19 ሞኝ ከመሆንና ውሸት ከመናገርድሃ ሆኖ ንጹሕ አቋምን* ጠብቆ መመላለስ ይሻላል።+
2 እውቀት የሌለው ሰው* ጥሩ አይደለም፤+ችኩል* ሰውም ኃጢአት ይሠራል።
3 የሰውን መንገድ የሚያጣምምበት የገዛ ሞኝነቱ ነው፤ልቡም በይሖዋ ላይ ይቆጣል።
4 ሀብት ብዙ ወዳጆችን ይስባል፤ድሃን ግን ጓደኛው እንኳ ይተወዋል።+
5 ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤+ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ከቅጣት አያመልጥም።+
6 ብዙዎች በተከበረ ሰው* ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ይጥራሉ፤ስጦታ ከሚሰጥ ሰው ጋር ደግሞ ሁሉም ይወዳጃል።
7 ድሃን ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤+ጓደኞቹማ ምን ያህል ይርቁት!+
እየተከታተለ ሊለማመጣቸው ይሞክራል፤ ምላሽ የሚሰጠው ግን የለም።
8 ማስተዋል* የሚያገኝ ሰው ሁሉ ራሱን* ይወዳል።+
ጥልቅ ግንዛቤን እንደ ውድ ሀብት አድርጎ የሚመለከት ሁሉ ይሳካለታል።*+
9 ሐሰተኛ ምሥክር መቀጣቱ አይቀርም፤ባወራ ቁጥር የሚዋሽም ይጠፋል።+
10 ሞኝ ሰው ተንደላቆ መኖር አይገባውም፤አገልጋይ መኳንንትን ቢገዛማ ምንኛ የከፋ ነው!+
11 ጥልቅ ማስተዋል ሰውን ቶሎ እንዳይቆጣ ያደርገዋል፤+በደልንም መተዉ* ውበት ያጎናጽፈዋል።+
12 የንጉሥ ቁጣ እንደ አንበሳ* ግሳት ነው፤+ሞገሱ ግን በሣር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው።
13 ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ መከራ ያመጣል፤+ጨቅጫቃ ሚስትም * ያለማቋረጥ እንደሚያንጠባጥብ ጣሪያ ናት።+
14 ቤትና ሀብት ከአባቶች ይወረሳል፤ልባም ሚስት ግን የምትገኘው ከይሖዋ ነው።+
15 ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ታካች ሰውም ይራባል።*+
16 ትእዛዝን የሚጠብቅ ሕይወቱን* ይጠብቃል፤+መንገዱን ቸል የሚል ይሞታል።+
17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+
18 ገና ተስፋ ሳለ ልጅህን ገሥጽ፤+ለእሱም ሞት ተጠያቂ አትሁን።*+
19 ግልፍተኛ ሰው ይቀጣል፤ልታድነው ብትሞክር እንኳ በተደጋጋሚ እንዲህ ለማድረግ ትገደዳለህ።+
20 የኋላ ኋላ ጥበበኛ እንድትሆንምክርን ስማ፤ ተግሣጽንም ተቀበል።+
21 ሰው በልቡ ብዙ ነገር ያቅዳል፤የሚፈጸመው ግን የይሖዋ ፈቃድ* ነው።+
22 የሰው ተወዳጅ ባሕርይ ታማኝ ፍቅሩ ነው፤+ውሸታም ከመሆን ድሃ መሆን ይሻላል።
23 ይሖዋን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤+እንዲህ የሚያደርግ ሰው ጥሩ እረፍት ያገኛል፤ ጉዳትም አይደርስበትም።+
24 ሰነፍ እጁን ወደ ሳህን ያጠልቃል፤ሆኖም ወደ አፉ እንኳ መመለስ ይሳነዋል።+
25 ተሞክሮ የሌለው ብልህ+ እንዲሆን ፌዘኛን ምታው፤+ተጨማሪ እውቀት እንዲያገኝም አስተዋይ የሆነን ሰው ውቀሰው።+
26 አባቱን የሚበድልና እናቱን የሚያባርር ልጅኀፍረትና ውርደት ያመጣል።+
27 ልጄ ሆይ፣ ተግሣጽን መስማት ከተውክእውቀት ከሚገኝበት ቃል ትርቃለህ።
28 የማይረባ ምሥክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤+የክፉዎችም አፍ ክፋትን ይሰለቅጣል።+
29 ፌዘኞች ፍርድ ይጠብቃቸዋል፤+ለሞኞች ጀርባ ደግሞ ዱላ ተዘጋጅቷል።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “ነፍስ።”
^ ቃል በቃል “በእግሩ የሚጣደፍ።”
^ ወይም “ለጋስ በሆነ ሰው።”
^ ወይም “ነፍሱን።”
^ ቃል በቃል “መልካም ነገር ያገኛል።”
^ ቃል በቃል “ልብ።”
^ ቃል በቃል “በደልንም ማለፉ።”
^ ወይም “ደቦል አንበሳ።”
^ ወይም “ነዝናዛ ሚስትም።”
^ ወይም “ታካች ነፍስም ትራባለች።”
^ ወይም “ነፍሱን።”
^ ወይም “ወሮታ።”
^ ወይም “የእሱንም ሞት አትመኝ።” ቃል በቃል “ለእሱ ሞት ነፍስህን አታንሳ።”
^ ወይም “ዓላማ።”