ምሳሌ 9:1-18
9 እውነተኛ ጥበብ ቤቷን ሠራች፤ሰባቱን ምሰሶዎቿንም ጠርባ አዘጋጀች።
2 ሥጋዋን በሚገባ አዘጋጀች፤*የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ደግሞም ገበታዋን አሰናዳች።
3 ከከተማዋ በላይ ባሉ ከፍታ ቦታዎች ላይ ሆነውእንዲህ ብለው እንዲጣሩ ሴት አገልጋዮቿን ላከች፦+
4 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
ማስተዋል* ለጎደለው እንዲህ ትላለች፦
5 “ኑ፣ ያዘጋጀሁትን ምግብ ብሉ፤የደባለቅኩትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።
6 አላዋቂነታችሁን ተዉ፤* በሕይወትም ኑሩ፤+በማስተዋል መንገድ ወደ ፊት ሂዱ።”+
7 ፌዘኛን የሚያርም በራሱ ላይ ውርደት ያመጣል፤+ክፉን ሰው የሚወቅስም ሁሉ ጉዳት ይደርስበታል።
8 ፌዘኛን አትውቀስ፤ አለዚያ ይጠላሃል።+
ጥበበኛን ሰው ውቀሰው፤ እሱም ይወድሃል።+
9 ጥበበኛን ሰው አስተምረው፤ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል።+
ጻድቅን ሰው አስተምረው፤ ተጨማሪ እውቀት ያገኛል።
10 የጥበብ መጀመሪያ ይሖዋን መፍራት ነው፤+እጅግ ቅዱስ ስለሆነው አምላክ ማወቅም+ ማስተዋል ነው።
11 በእኔ ምክንያት ዘመንህ ይረዝማል፤+በሕይወትህም ላይ ዕድሜ ይጨመርልሃል።
12 ጥበበኛ ብትሆን፣ ጥበበኛነትህ የሚጠቅመው ራስህን ነው፤ፌዘኛ ብትሆን ግን መዘዙን የምትቀበለው አንተው ነህ።
13 ማስተዋል የጎደላት ሴት ጯኺ ናት።+
እሷ ጨርሶ ማመዛዘን አትችልም፤ ደግሞም አንዳች ነገር አታውቅም።
14 በከተማዋ ከፍ ያሉ ቦታዎች ላይ፣በቤቷ ደጃፍ ወንበር ላይ ትቀመጣለች፤+
15 በጎዳናው የሚያልፉትን፣ቀጥ ብለው በመንገዳቸው የሚሄዱትን ትጣራለች፦
16 “ተሞክሮ የሌለው ሁሉ ወደዚህ ይምጣ።”
ማስተዋል* ለጎደላቸው ሁሉ እንዲህ ትላለች፦+
17 “የተሰረቀ ውኃ ይጣፍጣል፤ተደብቀው የበሉት ምግብም ይጥማል።”+
18 እሱ ግን በሞት የተረቱት በዚያ እንዳሉ፣እንግዶቿም በመቃብር* ጥልቅ ውስጥ እንደሚገኙ አያውቅም።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “እርዷን አረደች።”
^ ቃል በቃል “ልብ።”
^ ወይም “ተሞክሮ ከሌላቸው ሰዎች ራቁ።”
^ ቃል በቃል “ልብ።”
^ ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።