ለዮሐንስ የተገለጠለት ራእይ 15:1-8
15 እኔም ሌላ ታላቅና አስደናቂ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ ሰባት መቅሰፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት+ ነበሩ። የአምላክ ቁጣ የሚደመደመው በእነዚህ ስለሆነ እነዚህ መቅሰፍቶች የመጨረሻዎቹ ናቸው።+
2 እኔም ከእሳት ጋር የተቀላቀለ የብርጭቆ ባሕር+ የሚመስል ነገር አየሁ፤ እንዲሁም አውሬውን፣ ምስሉንና+ የስሙን ቁጥር+ ድል የነሱት+ የአምላክን በገናዎች ይዘው በብርጭቆው ባሕር አጠገብ ቆመው ነበር።
3 የአምላክን ባሪያ የሙሴን መዝሙርና+ የበጉን+ መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፦
“ሁሉን ቻይ የሆንከው ይሖዋ* አምላክ ሆይ፣+ ሥራዎችህ ታላቅና አስደናቂ ናቸው።+ የዘላለም ንጉሥ ሆይ፣+ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።+
4 ይሖዋ* ሆይ፣ ለመሆኑ አንተን የማይፈራና ስምህን ከፍ ከፍ የማያደርግ ማን ነው? አንተ ብቻ ታማኝ ነህና!+ የጽድቅ ድንጋጌዎችህ ስለተገለጡ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”+
5 ከዚህ በኋላ አየሁ፤ የምሥክሩ ድንኳን+ ቅዱስ ስፍራ* በሰማይ ተከፍቶ ነበር፤+
6 ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባቱ መላእክትም+ ንጹሕና የሚያንጸባርቅ በፍታ ለብሰው እንዲሁም ደረታቸውን በወርቅ መታጠቂያ ታጥቀው ከቅዱሱ ስፍራ ወጡ።
7 ከአራቱ ሕያዋን ፍጥረታት አንዱ ለዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ+ የተሞሉ ሰባት የወርቅ ሳህኖችን ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።
8 ቅዱሱ ስፍራም ከአምላክ ክብርና+ ከኃይሉ የተነሳ በጭስ ተሞላ፤ የሰባቱ መላእክት ሰባት መቅሰፍቶች+ እስኪፈጸሙ ድረስም ወደ ቅዱሱ ስፍራ ማንም መግባት አልቻለም።