ሶፎንያስ 3:1-20

  • ዓመፀኛና ብልሹ የሆነችው ኢየሩሳሌም (1-7)

  • ፍርድና ተመልሶ መቋቋም (8-20)

    • “ንጹሕ ቋንቋ እሰጣቸዋለሁ” (9)

    • ትሑት የሆነና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብ ይድናል (12)

    • ይሖዋ በጽዮን ሐሴት ያደርጋል (17)

3  ዓመፀኛ ለሆነችው፣ ለረከሰችውና ለጨቋኟ ከተማ ወዮላት!+   ማንንም ለመታዘዝ ፈቃደኛ አልሆነችም፤+ ምንም ዓይነት ተግሣጽ አልተቀበለችም።+ በይሖዋ አልታመነችም፤+ ወደ አምላኳም አልቀረበችም።+   በውስጧ ያሉት መኳንንቷ የሚያገሱ አንበሶች ናቸው።+ ፈራጆቿ የሌሊት ተኩላዎች ናቸው፤ለጠዋት ምንም ሳያስቀሩ አጥንቱን ሁሉ ይግጣሉ።   ነቢያቷ እብሪተኞችና አታላዮች ናቸው።+ ካህናቷ ቅዱስ የሆነውን ነገር ያረክሳሉ፤+በሕጉ ላይ ያምፃሉ።+   በመካከሏ ያለው ይሖዋ ጻድቅ ነው፤+ እሱ ምንም ዓይነት ስህተት አይፈጽምም። ፍርዱን እንደማይነጥፍ የንጋት ብርሃን፣በየማለዳው ያሳውቃል።+ ክፉ ሰው ግን ኀፍረት የሚባል ነገር አያውቅም።+   “ብሔራትን አጥፍቻለሁ፤ በቅጥር ማዕዘኖች ላይ ያሉ ማማዎቻቸው ወድመዋል። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፍርሻለሁ። ከተሞቻቸው ፈራርሰዋል፤ በዚያ አንድም ሰው የለም፤ ነዋሪም አይገኝባቸውም።+   እኔም ‘በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ተግሣጽም* ትቀበያለሽ’ አልኩ፤+ ይህም መኖሪያዋ እንዳይጠፋ ነው፤+ለሠራችው ኃጢአት ሁሉ ተጠያቂ አደርጋታለሁ።* እነሱ ግን ብልሹ ነገር ለመፈጸም ይበልጥ ጓጉ።+   ‘ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሳበት ቀን* ድረስእኔን በተስፋ ተጠባበቁ’*+ ይላል ይሖዋ፤‘ብሔራትን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፣በእነሱም ላይ መዓቴንና የሚነደውን ቁጣዬን ሁሉ ለማውረድ የፍርድ ውሳኔ አስተላልፌአለሁና፤+መላዋ ምድር በቅንዓቴ እሳት ትበላለች።+   በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የይሖዋን ስም እንዲጠሩናእጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲያገለግሉት*ቋንቋቸውን ለውጬ ንጹሕ ቋንቋ እሰጣቸዋለሁ።’+ 10  የሚለምኑኝ ሰዎች ይኸውም የተበተኑት ሕዝቦቼየኢትዮጵያ ወንዞች ከሚገኙበት ስፍራ ስጦታ ያመጡልኛል።+ 11  በዚያን ቀን በእኔ ላይ በማመፅ በፈጸምሻቸው ሥራዎች ሁሉለኀፍረት አትዳረጊም፤+በዚያን ጊዜ በትዕቢት ጉራ የሚነዙትን ከመካከልሽ አስወግዳለሁና፤አንቺም ከእንግዲህ በተቀደሰው ተራራዬ ላይ ፈጽሞ አትታበዪም።+ 12  እኔም ትሑት የሆነና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብ በመካከላችሁ እንዲቀር አደርጋለሁ፤+እነሱም የይሖዋን ስም መጠጊያቸው ያደርጉታል። 13  የእስራኤል ቀሪዎች+ ምንም ዓይነት ክፋት አይሠሩም፤+ውሸት አይናገሩም፤ በአፋቸውም ውስጥ አታላይ ምላስ አይገኝም፤ይልቁንም ይመገባሉ፤* ይተኛሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም።”+ 14  የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ! እስራኤል ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ!+ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በሙሉ ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሴትም አድርጊ!+ 15  ይሖዋ በአንቺ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ሽሯል።+ ጠላትሽን ከአንቺ መልሷል።+ የእስራኤል ንጉሥ ይሖዋ በመካከልሽ ነው።+ ከእንግዲህ ወዲህ ጥፋት አያስፈራሽም።+ 16  በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም እንዲህ ይባላል፦ “ጽዮን ሆይ፣ አትፍሪ።+ እጆችሽ አይዛሉ። 17  አምላክሽ ይሖዋ በመካከልሽ ነው።+ እንደ ኃያል ተዋጊ ያድናል። በታላቅ ደስታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል።+ ለአንቺ ፍቅር በማሳየቱ ረክቶ ዝም ይላል።* በእልልታ በአንቺ ሐሴት ያደርጋል። 18  በበዓላትሽ ላይ ባለመገኘታቸው ያዘኑትን ሰዎች እሰበስባለሁ፤+ለእሷ ሲሉ በደረሰባቸው ነቀፋ የተነሳ ወደ አንቺ አልመጡም።+ 19  እነሆ፣ በዚያን ጊዜ በሚጨቁኑሽ ሁሉ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ፤+የምታነክሰውንም አድናታለሁ፤+የተበተነችውንም እሰበስባለሁ።+ ኀፍረት በተከናነቡበት ምድር ሁሉእንዲወደሱና ዝና* እንዲያተርፉ አደርጋቸዋለሁ። 20  በዚያን ጊዜ መልሼ አመጣችኋለሁ፤አዎ፣ በዚያን ጊዜ እሰበስባችኋለሁ። ተማርከው የተወሰዱባችሁን ሰዎች በፊታችሁ መልሼ በምሰበስብበት ጊዜ+በምድር ሕዝቦች ሁሉ መካከል ዝና* እንድታተርፉና እንድትወደሱ አደርጋለሁና”+ ይላል ይሖዋ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እቀጣታለሁ።”
ወይም “እርማትም።”
“ምሥክር ሆኜ እስከምነሳበት ቀን” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “እኔን በትዕግሥት ጠብቁ።”
ወይም “በአንድነት እንዲያመ​ልኩት።”
ወይም “ይግጣሉ።”
ወይም “ጸጥ ይላል፤ ያርፋል፤ ስሜቱ ይረ​ጋጋል።”
ቃል በቃል “ስም።”
ቃል በቃል “ስም።”