ናሆም 2:1-13
2 የሚበትን መጥቶብሻል።*+
ምሽጎቹን ጠብቂ።
መንገዱን በትኩረት ተመልከቺ።
ወገብሽን ታጠቂ፤* ኃይልሽንም ሁሉ አሰባስቢ።
2 ይሖዋ የያዕቆብን ክብርከእስራኤል ክብር ጋር ይመልሳልና፤አጥፊዎች አጥፍተዋቸዋልና፤+ቀንበጦቻቸውንም ከጥቅም ውጭ አድርገዋል።
3 የኃያላኑ ጋሻዎች ቀይ ቀለም የተነከሩ ናቸው፤ተዋጊዎቹ ደማቅ ቀይ ልብስ ለብሰዋል።
ለጦርነት ዝግጁ በሚሆንበት ቀን፣የጦር ሠረገላው ብረቶች እንደ እሳት ያብረቀርቃሉ፤ከጥድ የተሠሩት ረጃጅም ጦሮች ይወዛወዛሉ።
4 የጦር ሠረገሎቹ በጎዳናዎቹ ላይ ይከንፋሉ።
በአደባባዮቹም ላይ ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ።
እንደሚነድ ችቦ ያበራሉ፤ እንደ መብረቅም ያንጸባርቃሉ።
5 እሱ አለቆቹን ይጠራል።
እነሱ ወደ ፊት ሲገሰግሱ ይሰናከላሉ።
ወደ ቅጥሯ እየተጣደፉ ይሄዳሉ፤መከላከያም ያቆማሉ።
6 የወንዞቹ በሮች ይከፈታሉ፤ቤተ መንግሥቱም ይቀልጣል።*
7 ጉዳዩ ታውጇል፦* እሷ ተጋልጣለች፤ተማርካ ተወስዳለች፤ ሴቶች ባሪያዎቿም ያቃስታሉ፤ደረታቸውን* እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ።
8 ነነዌ ከተቆረቆረችበት+ ጊዜ አንስቶ እንደ ውኃ ኩሬ ነበረች፤አሁን ግን እነሱ ይሸሻሉ።
አንዳንዶች “ቁሙ! ቁሙ!” ብለው ይጮኻሉ።
ሆኖም ወደ ኋላ የሚዞር የለም።+
9 ብሩን ዝረፉ፤ ወርቁን ዝረፉ!
የተከማቸው ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም።
በብዙ ዓይነት የከበሩ ዕቃዎች ተሞልቷል።
10 ከተማዋ ባዶና ወና እንዲሁም ባድማ ሆናለች!+
ልባቸው በፍርሃት ቀልጧል፤ ጉልበታቸው ተብረክርኳል፤ ወገባቸውም ተንቀጥቅጧል፤የሁሉም ፊት ቀልቷል።
11 ደቦል አንበሶቹ የሚመገቡበት፣ማንም ሳያስፈራቸው አንበሳው ግልገሎቹን እየመራ የሚወጣበትየአንበሶቹ ዋሻ የት አለ?+
12 አንበሳው ለግልገሎቹ የሚበቃቸውን ያህል አደነ፤ለእንስቶቹም አንቆ ገደለላቸው።
ጎሬውን በታደኑ እንስሶች፣ዋሻውንም በተቦጫጨቁ እንስሶች ሞላ።
13 “እነሆ፣ በአንቺ ላይ ተነስቻለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፤+“የጦር ሠረገላዋን በጭስ መካከል አቃጥላለሁ፤+ደቦል አንበሶችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል።
አደንሽን ከምድር ገጽ አስወግዳለሁ፤የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ነነዌን ያመለክታል።
^ ቃል በቃል “ዳሌዎችሽን አጠንክሪ።”
^ ወይም “ይፈርሳል።”
^ ወይም “ተቆርጧል።”
^ ቃል በቃል “ልባቸውን።”