ኢሳይያስ 35:1-10
35 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ሐሴት ያደርጋል፤+በረሃማው ቦታም ደስ ይለዋል፤ እንደ ሳሮን አበባም * ያብባል።+
2 በእርግጥ ያብባል፤+ሐሴት ያደርጋል፤ በደስታም እልል ይላል።
የሊባኖስ ክብር ይሰጠዋል፤+የቀርሜሎስንና+ የሳሮንን+ ግርማ ይለብሳል።
የይሖዋን ክብር፣ የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፤የሚብረከረኩትንም ጉልበቶች አጽኑ።+
4 በጭንቀት የተዋጠ ልብ ላላቸው እንዲህ በሏቸው፦
“በርቱ፤ አትፍሩ።
እነሆ፣ አምላካችሁ ሊበቀል ይመጣል፤አምላክ ብድራት ሊከፍል ይመጣል።+
እሱ መጥቶ ያድናችኋል።”+
5 በዚያን ጊዜ የዓይነ ስውራን ዓይን ይገለጣል፤+መስማት የተሳናቸው ሰዎች ጆሮም ይከፈታል።+
6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤+የዱዳም ምላስ በደስታ እልል ይላል።+
በምድረ በዳ ውኃ ይፈልቃልና፤በበረሃማ ሜዳም ጅረት ይፈስሳል።
7 በሐሩር የተቃጠለው ምድር ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣የተጠማውም ምድር የውኃ ምንጭ ይሆናል።+
ቀበሮዎች ይኖሩበት የነበረው ጎሬ+ለምለም ሣር፣ ሸምበቆና ደንገል ይበቅልበታል።
8 በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፤+ደግሞም “የቅድስና ጎዳና” ተብሎ ይጠራል።
ንጹሕ ያልሆነ ሰው አይጓዝበትም።+
ጎዳናው፣ በመንገዱ ላይ ለሚሄዱት ብቻ ይሆናል፤ሞኞችም አይሄዱበትም።
9 በዚያ አንበሳ አይኖርም፤አዳኝ አራዊትም ወደዚያ አይወጡም።
አንዳቸውም በዚያ አይገኙም፤+የተቤዡት ብቻ በዚያ ይሄዳሉ።+
10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+
ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+
ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “ሳፍሮንም።”