ኢሳይያስ 41:1-29
41 “እናንተ ደሴቶች፣ ዝም ብላችሁ አዳምጡኝ፤*ብሔራትም ኃይላቸውን ያድሱ።
በመጀመሪያ ይቅረቡ፤ ከዚያም ይናገሩ።+
ለፍርድ አንድ ላይ እንሰብሰብ።
2 ብሔራትን አሳልፎ ይሰጠውናነገሥታትን ድል ይነሳ ዘንድ+ከፀሐይ መውጫ* አንዱን ያስነሳው፣+በጽድቅ ወደ እግሩ የጠራው* ማን ነው?
በሰይፉ ፊት አቧራ የሚያደርጋቸው፣በቀስቱ ፊት በነፋስ እንደተወሰደ ገለባ የሚያደርጋቸው ማን ነው?
3 እግሩ ባልረገጠው መንገድ በመጓዝምንም ነገር ሳያግደው እነሱን ያሳድዳል።
4 ይህን የሠራና ያደረገ፣ትውልዶቹንም ከመጀመሪያ አንስቶ የጠራ ማን ነው?
እኔ ይሖዋ የመጀመሪያው ነኝ፤+ከመጨረሻዎቹም ጋር እኔ ያው ነኝ።”+
5 ደሴቶች አይተው ፈሩ።
የምድር ዳርቻዎች ተንቀጠቀጡ።
ቀረቡ፤ ወደ ፊትም መጡ።
6 እያንዳንዱም ባልንጀራውን ይረዳል፤ወንድሙንም “አይዞህ፣ በርታ” ይለዋል።
7 የእጅ ጥበብ ባለሙያውም አንጥረኛውን ያበረታታል፤+በመዶሻ ብረቱን የሚያሳሳውበመስፍ ላይ የሚቀጠቅጠውን ያበረታታዋል።
ብየዳውን በተመለከተ “ጥሩ ነው” ይላል።
ከዚያም ጣዖቱ እንዳይወድቅ አንድ ሰው በምስማር ይቸነክረዋል።
8 “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግን አገልጋዬ ነህ፤+ያዕቆብ ሆይ፣ አንተን መርጬሃለሁ፤+የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፤+
9 አንተን ከምድር ዳርቻዎች ወሰድኩህ፤+እጅግ ርቀው ከሚገኙ ቦታዎችም ጠራሁህ።
እንዲህ ብዬሃለሁ፦ ‘አንተ አገልጋዬ ነህ፤+እኔ መርጬሃለሁ፤ ገሸሽ አላደረግኩህም።+
10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ።+
እኔ አምላክህ ነኝና አትጨነቅ።+
አበረታሃለሁ፤ አዎ እረዳሃለሁ፤+በጽድቅ ቀኝ እጄ አጥብቄ እይዝሃለሁ።’
11 እነሆ፣ በአንተ ላይ የተቆጡ ሁሉ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም።+
ከአንተ ጋር የሚጣሉ ሁሉ እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።+
12 ከአንተ ጋር የሚፋለሙትን ሰዎች ትፈልጋቸዋለህ፤ ሆኖም አታገኛቸውም፤ከአንተ ጋር የሚዋጉ ሰዎች እንደሌሉና ፈጽሞ እንዳልነበሩ ያህል ይሆናሉ።+
13 ‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህእኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁና።+
14 ትል* የሆንከው አንተ ያዕቆብ አትፍራ፤+እናንተ የእስራኤል ሰዎች፣ እረዳችኋለሁ” ይላል የሚቤዥህ+ የእስራኤል ቅዱስ ይሖዋ።
15 “እነሆ፣ ማሄጃ፣ በሁለቱም በኩል የተሳሉ ጥርሶች ያሉትአዲስ የመውቂያ መሣሪያ አድርጌሃለሁ።+
አንተም ተራሮቹን ረግጠህ ታደቃቸዋለህ፤ኮረብቶቹንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
16 ወደ ላይ ትበትናቸዋለህ፤ነፋስም ይወስዳቸዋል፤አውሎ ነፋስ ይበትናቸዋል።
በይሖዋ ደስ ይልሃል፤+በእስራኤልም ቅዱስ ትኮራለህ።”+
17 “ችግረኞችና ድሆች ውኃ ይፈልጋሉ፤ ሆኖም አያገኙም።
ከመጠማታቸው የተነሳ ምላሳቸው ደርቋል።+
እኔ ይሖዋ እመልስላቸዋለሁ።+
እኔ የእስራኤል አምላክ አልተዋቸውም።+
18 በተራቆቱ ኮረብቶች ላይ ወንዞች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ፤+በሸለቋማ ሜዳዎች መካከል ምንጮችን አፈልቃለሁ።+
ምድረ በዳውን ቄጠማ የሞላበት ኩሬ፣ውኃ የሌለበትንም ምድር የውኃ ምንጭ አደርጋለሁ።+
19 በበረሃ አርዘ ሊባኖስ፣ግራር፣ አደስና ዘይት የሚሰጥ ዛፍ እተክላለሁ።+
በበረሃማ ሜዳ የጥድ ዛፍ፣የአሽ ዛፍና* የፈረንጅ ጥድ በአንድነት እተክላለሁ፤+
20 ይህም የሚሆነው የይሖዋ እጅ ይህን እንዳደረገናየእስራኤል ቅዱስ ይህን እንደፈጠረሰዎች ሁሉ እንዲያዩና እንዲያውቁ፣ልብ እንዲሉና በጥልቅ እንዲያስተውሉ ነው።”+
21 “ሙግታችሁን አቅርቡ” ይላል ይሖዋ።
“የመከራከሪያ ሐሳባችሁን አሰሙ” ይላል የያዕቆብ ንጉሥ።
22 “ማስረጃ አቅርቡ፤ እንዲሁም ወደፊት የሚሆኑትን ነገሮች ንገሩን።
በጥሞና እንድናስብባቸውና* ፍጻሜያቸውን እንድናውቅስለቀድሞዎቹ* ነገሮች ንገሩን።
ወይም የሚመጡትን ነገሮች አሳውቁን።+
23 አማልክት መሆናችሁን እንድናውቅወደፊት የሚሆነውን ነገር ንገሩን።+
አዎ፣ አይተን በአድናቆት እንድንዋጥመልካምም ሆነ ክፉ፣ የሆነ ነገር አድርጉ።+
24 እነሆ፣ እናንተ ጨርሶ ሕልውና የሌላችሁ ናችሁ፤ምንም የምታከናውኑት ነገር የለም።+
እናንተን የሚመርጥ ሁሉ አስጸያፊ ነው።+
25 አንዱን ከሰሜን አስነስቻለሁ፤ እሱም ይመጣል፤+የሚመጣው ከፀሐይ መውጫ*+ ሲሆን ስሜንም ይጠራል።
ጭቃውን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪገዢዎችን* እንደ ሸክላ አፈር ይረግጣቸዋል።+
26 እኛ እናውቅ ዘንድ ስለዚህ ነገር ከመጀመሪያው የተናገረወይም ‘እሱ ትክክል ነው’ እንድንል ከጥንት ጀምሮ የተናገረ ማን ነው?+
በእርግጥ የተናገረ የለም!
ያሳወቀም የለም!
ከእናንተ አንዳች ነገር የሰማ የለም!”+
27 ከማንም በፊት ጽዮንን “ወደፊት የሚሆነውን ነገር ተመልከቺ!” ያልኩት እኔ ነኝ፤+
ለኢየሩሳሌምም ምሥራች ነጋሪ እልካለሁ።+
28 ሆኖም እኔ መመልከቴን ቀጠልኩ፤ አንድም ሰው አልነበረም፤ከእነሱ መካከል ምክር የሚሰጥ አልነበረም።
እኔም መልስ እንዲሰጡ መጠየቄን ቀጠልኩ።
29 እነሆ፣ ሁሉም ቅዠት* ናቸው።
ሥራቸው ከንቱ ነው።
ከብረት የተሠሩት ምስሎቻቸው* ነፋስና መና ናቸው።+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “እናንተ ደሴቶች፣ በፊቴ ዝም በሉ።”
^ ወይም “ከምሥራቅ።”
^ እሱን እንዲያገለግል የጠራው ማለት ነው።
^ አቅመ ቢስና ትንሽ መሆኑን ያመለክታል።
^ እስከ 15 ሜትር የሚደርስ ርዝመት ያለው ትልቅ ዛፍ ነው። ቅጠሎቹ ፈዘዝ ያለ አረንጓዴ ቀለም ያላቸው ሲሆን ቅርንጫፎቹ ደግሞ አመድማ መልክ አላቸው።
^ ወይም “ልብ እንድናደርግና።”
^ ቃል በቃል “ስለ መጀመሪያዎቹ።”
^ ወይም “ከምሥራቅ።”
^ ወይም “የበታች ገዢዎችን።”
^ ወይም “ሁሉም ሕልውና የሌላቸው ነገሮች።”
^ ወይም “ቀልጠው የተሠሩት ሐውልቶቻቸው።”