ኢሳይያስ 45:1-25

  • ቂሮስ ባቢሎንን ድል እንዲያደርግ ተቀብቷል (1-8)

  • ሸክላ ከሠሪው ጋር ሙግት አይገጥምም (9-13)

  • ሌሎች ብሔራት ለእስራኤል እውቅና ይሰጣሉ (14-17)

  • የአምላክ የፍጥረት ሥራም ሆነ የሚናገረው ትንቢት አስተማማኝ ነው (18-25)

    • ምድር የተፈጠረችው መኖሪያ እንድትሆን ነው (18)

45  ይሖዋ ለቀባው ለቂሮስ+ እንዲህ ይላል፦ብሔራትን በፊቱ ለማስገዛት፣+ነገሥታትን ትጥቅ ለማስፈታት*እንዲሁም የከተማው በሮች እንዳይዘጉመዝጊያዎቹን በፊቱ ለመክፈት ስልቀኝ እጁን ለያዝኩት+ ለቂሮስ፦  2  “እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤+ኮረብቶቹንም ደልዳላ አደርጋለሁ። የመዳብ በሮቹን እሰባብራለሁ፤የብረት መቀርቀሪያዎቹንም እቆርጣለሁ።+  3  በስምህ የምጠራህ+እኔ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ መሆኔን እንድታውቅ፣በጨለማ ያለውን ውድ ሀብትናስውር በሆኑ ቦታዎች የተደበቀውን ውድ ሀብት እሰጥሃለሁ።+  4  ለአገልጋዬ ለያዕቆብ፣ ለመረጥኩትም ለእስራኤል ስልበስምህ እጠራሃለሁ። አንተ ባታውቀኝም እንኳ የክብር ስም እሰጥሃለሁ።  5  እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።+ አንተ ባታውቀኝም እንኳ አበረታሃለሁ፤*  6  ይኸውም ከፀሐይ መውጫ እስከ ፀሐይ መግቢያ* ያሉ ሕዝቦችከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው።+እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።+  7  ብርሃንን እሠራለሁ፤+ ጨለማንም እፈጥራለሁ፤+ሰላምን አሰፍናለሁ፤+ ጥፋትንም እፈጥራለሁ፤+እኔ ይሖዋ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አደርጋለሁ።  8  እናንተ ሰማያት፣ ከላይ አዝንቡ፤+ደመናት ጽድቅን እንደ ዶፍ ያውርዱ። ምድር ትከፈት፤ መዳንንም ታፍራ፤ጽድቅንም በአንድነት ታብቅል።+ እኔ ይሖዋ ፈጥሬዋለሁ።”  9  ከሠሪው ጋር ሙግት ለሚገጥም* ወዮለት!እሱ መሬት ላይ በተጣሉሌሎች ገሎች መካከል ያለ ተራ ገል ነውና። ሸክላ፣ ሠሪውን* “የምትሠራው ምንድን ነው?” ይለዋል?+ የሠራኸውስ ነገር “እሱ እጅ የለውም” ይላል?* 10  አንድን አባት “ምን ልትወልድ ነው?” ብሎ ለሚጠይቅ፣ ሴትንም “ምን ልትወልጂ ነው?”* ለሚል ወዮለት! 11  የእስራኤል ቅዱስ፣+ ሠሪው የሆነው ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ወደፊት ስለሚሆኑት ነገሮች ልትጠይቁኝ፣ደግሞስ ልጆቼንና+ የእጆቼን ሥራ በተመለከተ ልታዙኝ ትፈልጋላችሁ? 12  እኔ ምድርን ሠርቻለሁ፤+ በላይዋም ላይ ሰውን ፈጥሬአለሁ።+ በገዛ እጆቼ ሰማያትን ዘርግቻለሁ፤+ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዛለሁ።”+ 13  “እኔ አንድን ሰው በጽድቅ አስነስቻለሁ፤+መንገዱንም ሁሉ ቀና አደርጋለሁ። እሱ ከተማዬን ይገነባል፤+በግዞት ያለውንም ሕዝቤን ያለዋጋ ወይም ያለጉቦ ነፃ ያወጣል”+ ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ። 14  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የግብፅ ትርፍ፣* የኢትዮጵያ ሸቀጦችና* ቁመተ ረጃጅሞቹ የሳባ ሰዎችወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የአንቺም ይሆናሉ። በሰንሰለት ታስረው ከኋላሽ ይሄዳሉ። መጥተው ይሰግዱልሻል።+ ደግሞም በጸሎት ‘አምላክ በእርግጥ ከአንቺ ጋር ነው፤+ከእሱም በቀር ሌላ የለም፤ ሌላም አምላክ የለም’ ይሉሻል።” 15  አዳኝ የሆንከው የእስራኤል አምላክ ሆይ፣+በእርግጥ አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ። 16  ሁሉም ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ውርደት ተከናንበው ይሄዳሉ።+ 17  እስራኤል ግን በይሖዋ ዘላለማዊ መዳን ያገኛል።+ እናንተም ለዘላለም አታፍሩም ወይም አትዋረዱም።+ 18  ሰማያትን የፈጠረው፣+ እውነተኛው አምላክ፣ምድርን የሠራትና ያበጃት፣ አጽንቶም የመሠረታት፣+መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ* ያልፈጠራት+ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም። 19  ስውር በሆነ ቦታ፣ ጨለማ በዋጠው ምድር አልተናገርኩም፤+ለያዕቆብ ዘር‘በከንቱ ፈልጉኝ’ አላልኩም። እኔ ይሖዋ ጽድቅ የሆነውን እናገራለሁ፤ ቅን የሆነውንም አወራለሁ።+ 20  ተሰብስባችሁ ኑ። እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ።+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ+ ምንም እውቀት የላቸውም። 21  ጉዳያችሁን ተናገሩ፤ እንዲሁም ሙግታችሁን አቅርቡ። ተሰብስበው በአንድነት ይማከሩ። ከረጅም ጊዜ በፊት ይህን አስቀድሞ የተናገረ ማን ነው?ከጥንትስ ጀምሮ ይህን ያወጀ ማን ነው? ይህን ያደረግኩት እኔ ይሖዋ አይደለሁም? ከእኔ ሌላ አምላክ የለም፤ከእኔ በቀር ጻድቅ አምላክና አዳኝ+ የሆነ ማንም የለም።+ 22  የምድር ዳርቻዎች ሁሉ፣ ወደ እኔ ተመለሱ፤ ትድናላችሁ፤+እኔ አምላክ ነኝና፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።+ 23  በራሴ ምያለሁ፤ቃል ከአፌ በጽድቅ ወጥቷል፤ደግሞም አይመለስም፦+ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ምላስም ሁሉ ታማኝ ለመሆን ይምላል፤+ 24  እንዲህም ይላል፦ ‘በእርግጥም በይሖዋ ዘንድ እውነተኛ ጽድቅና ብርታት አለ። በእሱ ላይ የተቆጡ ሁሉ ኀፍረት ተከናንበው ወደ እሱ ይመጣሉ። 25  የእስራኤል ዘር ሁሉ በይሖዋ ትክክለኛ ሆኖ ይገኛል፤+በእሱም ይኮራል።’”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ቃል በቃል “የነገሥታትን ዳሌዎች ለመፍታት።”
ቃል በቃል “በሚገባ አስታጥቅሃለሁ።”
ወይም “ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ።”
ወይም “ለሚከራከር።”
ወይም “ያበጀውን።”
“ወይስ ሸክላው ‘ሥራህ እጀታ የለውም’ ይላል?” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “ምን እያማጥሽ ነው?”
“የጉልበት ሠራተኞች” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“ነጋዴዎችና” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“ባዶ እንድትሆን” ማለትም ሊሆን ይችላል።