ኢሳይያስ 49:1-26
49 እናንተ ደሴቶች ስሙኝ፤እናንተም በሩቅ ያላችሁ ብሔራት+ በጥሞና አዳምጡ።
ይሖዋ ከመወለዴ በፊት* ጠርቶኛል።+
በእናቴ ማህፀን ከነበርኩበት ጊዜ አንስቶ ስሜን ጠርቷል።
2 አፌን እንደተሳለ ሰይፍ አደረገው፤በእጁ ጥላ ሥር ሰወረኝ።+
የሾለ ፍላጻ አደረገኝ፤በኮሮጆው ውስጥ ሸሸገኝ።
3 እሱም “እስራኤል ሆይ፣ አንተ ግርማዬን የምገልጥብህ+አገልጋዬ ነህ”+ አለኝ።
4 እኔ ግን “የደከምኩት በከንቱ ነው።
ጉልበቴንም ያፈሰስኩት ከንቱ ለሆነና ምንም ፋይዳ ለሌለው ነገር ነው።
ሆኖም የሚዳኘኝ ይሖዋ ነው፤*ደሞዜንም* የሚከፍለኝ አምላኬ ነው”+ አልኩ።
5 የእሱ አገልጋይ እንድሆን ከማህፀን ጀምሮ የሠራኝ ይሖዋ፣እስራኤል ወደ እሱ ይሰበሰብ ዘንድያዕቆብን ወደ እሱ እንድመልስ አዞኛል።+
በይሖዋ ፊት እከብራለሁ፤አምላኬም ብርታቴ ይሆናል።
6 እንዲህም አለ፦ “የያዕቆብን ነገዶች ዳግመኛ ለማቋቋምናጥበቃ ያገኙትን እስራኤላውያን መልሰህ ለማምጣትአገልጋዬ መሆንህ በቂ አይደለም።
የማዳን ሥራዬ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ+ለብሔራት ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ።”+
7 እስራኤልን የሚቤዠው፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆነው ይሖዋ፣+ እጅግ ለተናቀውና*+ በሕዝብ ለተጠላው የገዢዎች አገልጋይ እንዲህ ይላል፦
“ታማኝ በሆነው በይሖዋ፣+አንተንም በመረጠህ+ በእስራኤል ቅዱስ የተነሳነገሥታት አይተው ይነሳሉ፤መኳንንትም ይሰግዳሉ።”
8 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ሞገስ* በማሳይበት ዘመን መልስ ሰጥቼሃለሁ፤+በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤+ለሰዎች ቃል ኪዳን አድርጌ እሰጥህ ዘንድ ጠብቄሃለሁ፤+ይህም ምድሪቱን ዳግመኛ እንድታቋቁም፣የወደመውን ርስታቸውን መልሰህ እንድታወርሳቸው፣+
9 እስረኞቹን ‘ኑ ውጡ!’+
በጨለማ ያሉትንም+ ‘ራሳችሁን ግለጡ!’ እንድትል ነው።
በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤በተበላሹ መንገዶችም* ሁሉ አጠገብ መሰማሪያ ያገኛሉ።
10 አይራቡም፤ አይጠሙም፤+ሐሩርም ሆነ ፀሐይ አያቃጥላቸውም።+
ምሕረት የሚያደርግላቸው ይመራቸዋልና፤+የውኃ ምንጮች ወዳሉበትም ይወስዳቸዋል።+
11 ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤አውራ ጎዳናዎቼም ከፍ ያሉ ይሆናሉ።+
12 እነሆ፣ እነዚህ ከሩቅ ይመጣሉ፤+እነሆም፣ እነዚህ ከሰሜንና ከምዕራብ፣እነዚህ ደግሞ ከሲኒም ምድር ይመጣሉ።”+
13 እናንተ ሰማያት፣ እልል በሉ፤ አንቺም ምድር፣ ሐሴት አድርጊ።+
ተራሮች በደስታ እልል ይበሉ።+
ይሖዋ ሕዝቡን አጽናንቷልና፤+ለተጎሳቆሉት ሕዝቦቹም ምሕረት ያሳያል።+
14 ጽዮን ግን “ይሖዋ ትቶኛል፤+
ይሖዋም ረስቶኛል”+ ትላለች።
15 እናት የምታጠባውን ልጇን ልትረሳ ትችላለች?ከማህፀኗ ለወጣውስ ልጅ አትራራም?
እነዚህ ሴቶች ቢረሱ እንኳ እኔ ፈጽሞ አልረሳሽም።+
16 እነሆ፣ በእጄ መዳፍ ላይ ቀርጬሻለሁ።
ግንቦችሽ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።
17 ወንዶች ልጆችሽ ፈጥነው ይመለሳሉ።
ያፈራረሱሽና ያወደሙሽ አንቺን ለቀው ይሄዳሉ።
18 ዓይንሽን አንስተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ።
ሁሉም በአንድነት እየተሰበሰቡ ነው።+
ወደ አንቺም እየመጡ ነው።
“በሕያውነቴ እምላለሁ” ይላል ይሖዋ፣“አንቺም ሁሉንም እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤እንደ ሙሽራም ትጎናጸፊያቸዋለሽ።
19 ስፍራዎችሽ ባድማና ወና፣ ምድርሽም የወደመ ቢሆንም+አሁን በዚያ የሚኖሩ ሰዎች ቦታው በጣም ይጠባቸዋል፤+የዋጡሽም+ ከአንቺ ይርቃሉ።+
20 የወላድ መሃን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱት ወንዶች ልጆች፣ጆሮሽ እየሰማ ‘ይህ ቦታ በጣም ጠቦናል።
የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይላሉ።+
21 አንቺም በልብሽ እንዲህ ትያለሽ፦‘እኔ ልጆቼን በሞት ያጣሁና መሃንእንዲሁም በምርኮ የተወሰድኩና እስረኛ የሆንኩ ሴት ሆኜ ሳለእነዚህን ልጆች የወለደልኝ ማን ነው?
ያሳደጋቸውስ ማን ነው?+
እነሆ፣ እኔ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤+ታዲያ እነዚህ ከየት መጡ?’”+
22 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ እጄን ለብሔራት አነሳለሁ፤ምልክቴንም * ለሕዝቦች ከፍ አደርጋለሁ።+
ወንዶች ልጆችሽን በክንዳቸው* ይዘው ያመጧቸዋል፤ሴቶች ልጆችሽንም በትከሻቸው ይሸከሟቸዋል።+
23 ነገሥታት ይንከባከቡሻል፤+ልዕልቶቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ።
በግንባራቸው ተደፍተው ይሰግዱልሻል፤+የእግርሽንም አቧራ ይልሳሉ፤+አንቺም እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቂያለሽ፤እኔን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም።”+
24 በምርኮ የተያዙ ሰዎች ከኃያል ሰው እጅ ሊወሰዱ ይችላሉ?ወይስ በጨቋኝ እጅ የወደቁ ምርኮኞችን የሚታደጋቸው ይኖራል?
25 ይሖዋ ግን እንዲህ ይላል፦
“በኃያል ሰው የተማረኩ ሰዎችም እንኳ ከእጁ ላይ ይወሰዳሉ፤+በጨቋኝ እጅ የወደቁ ሰዎችንም የሚታደጋቸው ይኖራል።+
አንቺን የሚቃወሙትን እቃወማለሁ፤+ወንዶች ልጆችሽንም አድናቸዋለሁ።
26 በደል የሚፈጽሙብሽን የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋቸዋለሁ፤ልክ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ።
ሰውም* ሁሉ እኔ ይሖዋአዳኝሽና+ የምቤዥሽ፣+የያዕቆብም ኃያል አምላክ እንደሆንኩ ያውቃል።”+
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ቃል በቃል “ከማህፀን ጀምሮ።”
^ ወይም “ሆኖም ይሖዋ ፍትሕ ያሰፍንልኛል።”
^ ወይም “ወሮታዬንም።”
^ ወይም “በነፍስ ለተናቀውና።”
^ ወይም “በጎ ፈቃድ።”
^ “በተራቆቱ ኮረብቶችም” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶዬንም።”
^ ቃል በቃል “በእቅፋቸው።”
^ ቃል በቃል “ሥጋም።”