ኢሳይያስ 54:1-17

  • መሃን የሆነችው ጽዮን ብዙ ልጆች ትወልዳለች (1-17)

    • የጽዮን ባል የሆነው ይሖዋ (5)

    • የጽዮን ልጆች ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ (13)

    • ጽዮንን ለማጥቃት የተሠራ መሣሪያ ይከሽፋል (17)

54  “አንቺ ያልወለድሽ መሃን ሴት፣ እልል በይ!+ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ ሴት፣+ ደስ ይበልሽ፤ በደስታም ጩኺ፤+የተተወችው ሴት ወንዶች ልጆች፣*ባል ካላት ሴት* ወንዶች ልጆች ይልቅ በዝተዋልና”+ ይላል ይሖዋ።  2  “የድንኳንሽን ቦታ አስፊ።+ ታላቅ የሆነውን የማደሪያ ድንኳንሽን ሸራዎች ዘርጊ። ፈጽሞ አትቆጥቢ፤ የድንኳንሽን ገመዶች አስረዝሚ፤ካስማዎችሽንም አጠንክሪ።+  3  በቀኝም ሆነ በግራ ትስፋፊያለሽና። ዘሮችሽ ብሔራትን ይወርሳሉ፤ባድማ በሆኑትም ከተሞች ውስጥ ይኖራሉ።+  4  ኀፍረት ስለማይደርስብሽ+ አትፍሪ፤+ለሐዘን ስለማትዳረጊም አትሸማቀቂ። በልጅነትሽ ዘመን የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺዋለሽና፤መበለትነትሽ ያስከተለብሽን ውርደትም ከእንግዲህ አታስታውሽም።”  5  “ታላቁ ሠሪሽ+ ባልሽ* ነውና፤+ስሙም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው፤የሚቤዥሽም+ የእስራኤል ቅዱስ ነው። እሱም የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል።+  6  ይሖዋ የተተወችና በሐዘን የተደቆሰች* ሚስት፣+ደግሞም በልጅነቷ አግብታ፣ ከጊዜ በኋላ የተጠላች ሚስት እንደሆንሽ ቆጥሮ ጠርቶሻልና” ይላል አምላክሽ።  7  “ለአጭር ጊዜ ተውኩሽ፤ሆኖም በታላቅ ምሕረት መልሼ እሰበስብሻለሁ።+  8  በቁጣ ጎርፍ ለጥቂት ጊዜ ፊቴን ከአንቺ ሰውሬ ነበር፤+ሆኖም በዘላለማዊ ታማኝ ፍቅር ምሕረት አሳይሻለሁ”+ ይላል የሚቤዥሽ+ ይሖዋ።  9  “ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ዘመን ነው።+ የኖኅ ውኃ ምድርን ዳግመኛ አያጥለቀልቅም ብዬ እንደማልኩ ሁሉ+አንቺንም ከእንግዲህ ላለመቆጣትም ሆነ ላለመገሠጽ እምላለሁ።+ 10  ተራሮች ከቦታቸው ሊወገዱ፣ኮረብቶችም ሊናወጡ ይችላሉ፤ይሁንና ታማኝ ፍቅሬ ከአንቺ አይለይም፤+የሰላም ቃል ኪዳኔም አይናጋም”+ ይላል ምሕረት የሚያሳይሽ ይሖዋ።+ 11  “አንቺ የተጎሳቆልሽ፣+ በአውሎ ነፋስ የተናወጥሽና ማጽናኛ ያላገኘሽ ሴት ሆይ፣+እነሆ ድንጋዮችሽን በኃይለኛ ማጣበቂያ እገነባለሁ፤መሠረትሽንም በሰንፔር እሠራለሁ።+ 12  መጠበቂያ ማማዎችሽን በሩቢ ድንጋዮች፣የከተማሽንም በሮች በሚያብረቀርቁ ድንጋዮች፣*ወሰኖችሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። 13  ልጆችሽም* ሁሉ ከይሖዋ የተማሩ ይሆናሉ፤+የልጆችሽም* ሰላም ብዙ ይሆናል።+ 14  በጽድቅ ጽኑ ሆነሽ ትመሠረቺያለሽ።+ ጭቆና ከአንቺ ይርቃል፤+ምንም ነገር አትፈሪም፤ የሚያሸብርሽም ነገር አይኖርም፤ወደ አንቺ አይቀርብምና።+ 15  ማንም ጥቃት ቢሰነዝርብሽእኔ አዝዤው አይደለም። ጥቃት የሚሰነዝርብሽ ሁሉ ከአንቺ የተነሳ ይወድቃል።”+ 16  “እነሆ፣ የከሰል እሳቱን በወናፍ የሚያናፋውንየእጅ ጥበብ ባለሙያ የፈጠርኩት እኔ ነኝ፤የሚያከናውነውም ሥራ የጦር መሣሪያ ያስገኛል። ደግሞም ጥፋት እንዲያደርስ አጥፊውን ሰው የፈጠርኩት እኔ ራሴ ነኝ።+ 17  አንቺን ለማጥቃት የተሠራ ማንኛውም መሣሪያ ይከሽፋል፤+አንቺን ለመክሰስ የሚነሳን ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የይሖዋ አገልጋዮች ውርሻ* ይህ ነው፤ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው” ይላል ይሖዋ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጌታ ካላት ሴት።”
ወይም “የተተወችው ሴት ልጆች።”
ወይም “ጌታሽ።”
ቃል በቃል “መንፈሷ የተጎዳ።”
ወይም “በእሳት ድንጋዮች።”
ቃል በቃል “የወንዶች ልጆችሽም።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆችሽም።”
ወይም “ርስት።”