ኢሳይያስ 55:1-13
55 እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ+ ኑ፤ ወደ ውኃው ኑ!+
እናንተ ገንዘብ የሌላችሁ ኑና ገዝታችሁ ብሉ!
አዎ፣ ኑና ያለገንዘብ፣ ያለዋጋም የወይን ጠጅና ወተት+ ግዙ።+
2 ምግብ ላልሆነ ነገር ለምን ገንዘባችሁን ታወጣላችሁ?እርካታ ለማያስገኝ ነገርስ ለምን ገቢያችሁን* ታባክናላችሁ?
እኔን በጥሞና አዳምጡ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤+ምርጥ ምግብ በመብላትም* ሐሴት ታደርጋላችሁ።*+
3 ጆሯችሁን አዘንብሉ፤ ወደ እኔም ኑ።+
አዳምጡ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤*ለዳዊት ካሳየሁት የማይከስም * ታማኝ ፍቅር+ ጋር በሚስማማ ሁኔታከእናንተ ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።+
4 እነሆ፣ ለብሔራት ምሥክር፣+መሪና+ አዛዥ+ አድርጌዋለሁ።
5 እነሆ፣ የማታውቀውን ብሔር ትጠራለህ፤የማያውቅህ ብሔርም ለአምላክህ ለይሖዋና ለእስራኤል ቅዱስ ሲልወደ አንተ ሮጦ ይመጣል፤+ምክንያቱም እሱ ክብር ያጎናጽፍሃል።+
6 ይሖዋን በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት።+
በቅርብም ሳለ ጥሩት።+
7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+
8 “ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ፣መንገዳችሁም እንደ መንገዴ አይደለምና”+ ይላል ይሖዋ።
9 “ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉመንገዴ ከመንገዳችሁ፣ሐሳቤም ከሐሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።+
10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣ምድርን በማራስ እንድታበቅልና እንድታፈራ፣ለዘሪው ዘርን፣ ለበላተኛውም ምግብን እንድትሰጥ ሳያደርግ ወደመጣበት እንደማይመለስ ሁሉ፣
11 ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ እንዲሁ ይሆናል።+
ደስ የሚያሰኘኝን ነገር* ያደርጋል፣+የተላከበትንም ዓላማ በእርግጥ ይፈጽማል እንጂያላንዳች ውጤት ወደ እኔ አይመለስም።+
12 በታላቅ ደስታ ትወጣላችሁና፤+በሰላምም ትመለሳላችሁ።+
ተራሮቹና ኮረብቶቹ በደስታ በፊታችሁ እልል ይላሉ፤+የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።+
13 በቁጥቋጦ ፋንታ የጥድ ዛፍ ይበቅላል፤+በሳማም ፋንታ የአደስ ዛፍ ይበቅላል።
የይሖዋ ስም እንዲገን ያደርጋል፤*+እንዲሁም ፈጽሞ የማይጠፋ የዘላለም ምልክት ይሆናል።”
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “በብዙ ድካም ያገኛችሁትን ገንዘብ።”
^ ቃል በቃል “በስብ።”
^ ወይም “ነፍሳችሁም ምርጥ ምግብ በመብላት ሐሴት ታደርጋለች።”
^ ወይም “ነፍሳችሁም በሕይወት ትኖራለች።”
^ ወይም “እምነት የሚጣልበት፤ አስተማማኝ የሆነ።”
^ ወይም “በነፃ ይቅር ይላልና።”
^ ወይም “ፈቃዴን።”
^ ወይም “የይሖዋን ስም ያስጠራል።”