ኢሳይያስ 64:1-12

  • የንስሐ ጸሎት ቀጣይ ክፍል (1-12)

    • ይሖዋ ሠሪያችን ነው (8)

64  በአንተ የተነሳ ተራሮች ይናወጡ ዘንድምነው ሰማያትን ቀደህ በወረድክ!  2  እሳት ጭራሮን አቀጣጥሎውኃን እንደሚያፈላ ሁሉ፣ያን ጊዜ ጠላቶችህ ስምህን ያውቃሉ፤ብሔራትም በፊትህ ይሸበራሉ!  3  እኛ ፈጽሞ ያልጠበቅናቸውን እጅግ አስደናቂ ነገሮች ባደረግክ ጊዜ፣+አንተ ወረድክ፤ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።+  4  ከጥንት ዘመን ጀምሮ፣ እሱን በተስፋ ለሚጠባበቁት* ሲል እርምጃ የወሰደከአንተ በቀር ሌላ አምላክ እንዳለ የሰማም ሆነ በጆሮው ያዳመጠወይም በዓይኑ ያየ ማንም የለም።+  5  ትክክል የሆነውን ነገር በደስታ ከሚያደርጉ፣+አንተን ከሚያስቡና መንገዶችህን ከሚከተሉ ሰዎች ጋር ተገናኝተሃል። እነሆ፣ ኃጢአት መሥራታችንን በቀጠልን ጊዜ ተቆጣህ፤+ይህን ያደረግነውም ለረጅም ጊዜ ነው። ታዲያ አሁን መዳን ይገባናል?  6  ሁላችንም እንደረከሰ ሰው ሆነናል፤የጽድቅ ሥራችንም ሁሉ እንደ ወር አበባ ጨርቅ ነው።+ ሁላችንም እንደ ቅጠል እንጠወልጋለን፤በደላችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎ ይወስደናል።  7  ስምህን የሚጠራ የለም፤አንተን የሙጥኝ ብሎ ለመያዝ የሚነሳሳ የለም፤ፊትህን ከእኛ ሰውረሃልና፤+በበደላችን የተነሳ እንድንመነምን* አድርገኸናል።  8  አሁን ግን ይሖዋ ሆይ፣ አንተ አባታችን ነህ።+ እኛ ሸክላ ነን፤ አንተም ሠሪያችን ነህ፤*+ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን።  9  ይሖዋ ሆይ፣ እጅግ አትቆጣ፤+በደላችንንም ለዘላለም አታስታውስ። እባክህ ተመልከተን፤ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነንና። 10  የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል። ጽዮን ምድረ በዳ፣ኢየሩሳሌምም ጠፍ ምድር ሆናለች።+ 11  አባቶቻችን አንተን ያወደሱበትየቅድስናና የክብር ቤታችን*በእሳት ተቃጥሏል፤+ከፍ አድርገን እንመለከታቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ ፈራርሰዋል። 12  ይሖዋ ሆይ፣ ይህ ሁሉ ሆኖ እያለ እርምጃ ከመውሰድ ትታቀባለህ? ዝም ብለህስ ታያለህ? ደግሞስ ከልክ በላይ እንድንጎሳቆል ትፈቅዳለህ?+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እሱን በትዕግሥት ለሚጠባበቁት።”
ቃል በቃል “እንድንቀልጥ።”
ወይም “ያበጀኸንም አንተ ነህ።”
ወይም “የውበት ቤተ መቅደሳችን።”