ኢያሱ 16:1-10

  • የዮሴፍ ወንዶች ልጆች ርስት (1-4)

  • የኤፍሬም ርስት (5-10)

16  ለዮሴፍ ዘሮች+ በዕጣ የተሰጣቸው ምድር+ በኢያሪኮ አጠገብ ካለው ከዮርዳኖስ አንስቶ ከኢያሪኮ በስተ ምሥራቅ እስካሉት ውኃዎች ድረስ ሲሆን ከኢያሪኮ ሽቅብ የሚወጣውን ምድረ በዳ አቋርጦ እስከ ተራራማው የቤቴል አካባቢ ድረስ ይዘልቃል።+ 2  እንዲሁም በሎዛ ከምትገኘው ከቤቴል አንስቶ በአጣሮት እስካለው የአርካውያን ወሰን ድረስ ይሄዳል፤ 3  ከዚያም በስተ ምዕራብ ወደ ያፍለጣውያን ወሰን ቁልቁል በመውረድ እስከ ታችኛው ቤትሆሮን+ ወሰንና እስከ ጌዜር+ ይደርሳል፤ ባሕሩም ጋ ሲደርስ ያበቃል። 4  ስለሆነም የዮሴፍ ዘሮች+ ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸው የሆነውን መሬት ወሰዱ።+ 5  የኤፍሬም ዘሮች ወሰን በየቤተሰባቸው የሚከተለው ነው፦ በስተ ምሥራቅ በኩል የርስታቸው ወሰን አጣሮትዓዳር+ ሲሆን እስከ ላይኛው ቤትሆሮንም+ ይደርሳል፤ 6  ከዚያም እስከ ባሕሩ ድረስ ይዘልቃል። ወሰኑ በስተ ሰሜን ሚክመታት+ ሲሆን በስተ ምሥራቅ በኩል ዞሮ ወደ ታአናትሺሎ ይሄድና በስተ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ያኖአህ ይዘልቃል። 7  ከያኖአህ ተነስቶም ወደ አጣሮትና ወደ ናዕራ ቁልቁል በመውረድ ኢያሪኮ+ ይደርስና ወደ ዮርዳኖስ ይዘልቃል። 8  ከዚያም ከታጱአ+ ተነስቶ በስተ ምዕራብ በኩል እስከ ቃና ሸለቆ በመዝለቅ ባሕሩ ጋ ሲደርስ ያበቃል።+ የኤፍሬም ነገድ በየቤተሰቡ ያገኘው ርስት ይህ ነው፤ 9  የኤፍሬም ዘሮች በምናሴ+ ርስት ውስጥም የተከለሉ ከተሞች ነበሯቸው፤ ከተሞቹ በሙሉ ከነመንደሮቻቸው የእነሱ ነበሩ። 10  ሆኖም በጌዜር+ ይኖሩ የነበሩትን ከነአናውያን አላባረሯቸውም፤ ከነአናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በኤፍሬም መካከል ይኖራሉ፤+ የግዳጅ ሥራ የመሥራት ግዴታም ተጥሎባቸዋል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች